Page 1 of 1

ስልጣኑን ልቀቅ ተብለሃል የ4ኪሎው መሓይም

Posted: 11 Jun 2022, 14:11
by መይሳው-ካሳ
ሰኔ 2 ቀን 2014 ዓ.ም.

በስመ ሕግ ማስከበር ዘመቻ በአማራ ህዝብ ላይ የተከፈተው መንግስታዊ ሽብር በአስቸኳይ ይቁም!!!

ለ ጠ/ሚ አብይ አህመድ

እኛ በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ የምንኖር ትውልደ ኢትዮጵያ አማራዎች በአሁኑ ሰዓት በአገራችን በመንግስት የሚደረገው ወከባ በተለይ አማራው ላይ ያነጣጠረው ኢ-ሰብአዊ ድርጊት እጅግ በጣም አስቆጥቶናል። እርስዎ ወደ ስልጣን ከመጡ ጀምሮ የ18ኛው ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ተደግሞ በሚያሳዝን ሁኔታ አገሪቷ ወደ ዳግማዊ ዘመነ መሳፍንት እየሄደች ነው።

ከብዙ በጥቂቱ ምልክቶችን ለመጥቀስ፦
  • ማህበረስቡን በዘርና በጎጥ እንዲከፋፈል እየተደረገ ያለው አካሄድ
  • አንድ ክልል ከሌላው ክልል ጦርነት ውስጥ እንዲገባ በገሃድም ሆነ በስውር የሚሸረበው ሴራ
  • መከላከያውንና የፖሊስ ሰራዊቱን እንደ አገራዊ ተቋም እንዳይቆሙ አሽመድምዶ በተጨማሪም በአንድ ዘር ቋት ለማስገባት መሞከር። ለምሳሌ አዲስ አበባ ፖሊስ እና ፍርድ ቤትን በኦሮምማ መተካት ብሎም ድምበር ዘሎ የኦሮሞ ክልል ልዩ ሃይል በአማራ ክልል ውስጥ የሚያካሂደው የንጹሃን ጭፍጭፋ
  • በሰሜን እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ ትህነግ የክህደት ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት በቂ የሆነ ወታደራዊ መረጃን ተጠቅመው ሰራዊቱ እራሱን እንዲከላከል ባለማዘጋጀትዎ በደረሰው እልቂት ተጠያቂ ነዎት። በተለይም የአማራ መኮንኖች ተለይተው ተረሽነዋል፤ የተረፉትም ባዶ እግራቸውን አገር ጥለው ሸሽተዋል። በተጨማሪም ትህነጎች በአገሪቱ አሉ የተባሉትን የጦር መሳርያዎች በእጃቸው እንዲገባ አድርገዋል።
  • የአማራውና የአፋሩ መሬቶች የጦር አውድማ ተደርገዋል: እየተደረጉም ይገኛሉ
  • ጦርነቱ በተካሄደበት ቦታ ብቻ ለምሳሌ እንደ አማራ ክልላዊ መንግስት ዘገባ ከ300 ቢልዮን ብር በላይ የሚያወጣ የህዝብና የመንግስት ንብረት ወድሟል
  • የመከላከያው ሰራዊት እየሸሸ እና መሳርያውን ለጠላት እያስረከበ በወጣበት ሰዓት ማህበረሰቡ እራሱን አደራጅቶ በፋኖ በኩል ወረራውን መክቷል። እውነታው ይሄ ሆኖ እያለ እርስዎ በመጨረሻ ብቅ በማለት የድሉ ባለቤት ሆነው ለመታየት ሞክረዋል
  • አሁን ደግሞ ትህነግ ወልቃይትና ራያ ላይ ጦርነት እያወጀ ባለበት ሰዓት ፋኖንና ልዩ ሐይሉን ለመበተንም ሆነ ማህበረሰቡ ውስጥ ያሉትን የአማራ ልሂቃንና አንቂዎችን በመግደል፣ በማፈን፣ በማሳደድ እና በማሰር ላይ በመንግስትዎ መሪነት በሚደረገው እንቅስቃሴ የአማራው ሕዝብ እራሱን እንዳይከላከል እድርገዋል፡ እያደረጉም ነው።
  • የአገሪቱን ምጣኔ ሀብት በጥቂት የኦሮሞ ባለሃብቶች እንዲጠቀለል፣ የህዝብ ንብረት በጽንፈኞች እንዲዘረፍና እንዲወድም አስደርገዋል። ከብዙ በጥቂቱ ለመጥቀስ ያህል፦ አጣዬ፣ ወለጋ፣ መተከል፣ ሸዋሮቢት፣ ምንጃር፣ ሻሸመኔ ወድመዋል
  • በተለይም የአማራውንና የትግሬውን ምጣኔ ሐብት እንዲደቅ ካደረጉ በሗላ በጥቂት ጽንፈኞች ስር ያለ የኦሮሞ ክልል ምጣኔ ሐብትን አሳድጋለሁ የሚል ቀቢጸ ተስፋ ውስጥ መገባቱ ለአገር መፍረስ ዋናው ምልክት ነው
  • በተጨማሪ በደቡብ ኢትዮጵያ ባሉት የተለያዩ ማህበረሰቦች ላይ፡ ለምሳሌ እንደ ኮንሶ፣ ወላይታ፣ ጋሞ፣ ጉጂ፣ አማሮ ተመሳሳይ ጥቃት በመሰንዘር በኦሮሞ ጽንፈኞች ማፈናቅልና መጠቅለል ሲደረግ ይታያል።
  • የአፋር ህዝብን ብቻውን ከትህነግ ጋር እንዲጋፈጥና ህይወትና ንብረቱ እንዲጠፋ ተደርጓል
  • በተመሳሳይ መልኩ የሶማሌ ክልል ወደ ብጥብጥና ብሎም ክፍፍል እዲያመራ ያላሰለሰ ጥረት እየተደረገ ነው
  • የአፋርና የሶማሌ ክልል እርስ በእርሳቸው እንዲተላለቁ ያላሰለሰ ጥረት በመንግስትዎ ሲደረግ ይታያል
  • በኦርቶዶክስ ሃይማኖት ላይ መዋቅራዊ ጥቃት ማድረግ እናም ለዘመናት በእስልምናና በኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች መካከል የነበረውን ተከባብሮ የመኖር ታሪክ እሴት ለማፈራረስ እና ለማበላሸት መንግስትዎ ተግተቶ እየሰራ ነው
  • በቅርብ ግዜ በመገናኛ ብዙሃን እንደተነገረው መፈንቅለ መጅሊስ በሚያስመሰል መንገድ ደንብን ባልተከተለ መንገድ ምርጫ ተካሂዶ በመንግስት የሚፈለጉ ሰዎች መሾማቸው
  • ዋና ከተማችን አዲስ አበባን በጉልበት በኦሮሞ ክልል ለመሰልቀጥ እየተደረገ ያለው አስነዋሪ ሂደት አገሪቷ በአሁኑ ሰዓት ትተዳደርበታለች በሚባለው ሕገ መንግስት እንኳን እንደማትመራ በግልጽ ያሳያል። እንዲሁም በከተማዋ ውስጥ ያሉ በታሪካዊ ቅርስነት የተመዘገቡ እሴቶችም በፍጥነት እየወደሙ ይገኛሉ
  • ትልቅ የአገር ክፍል (ጎንደር) በሱዳን ተወሮ መንግስት ምንም አይነት እርምጃ ባለመወሰዱ ተጠያቂ ያደርግዎታል
  • ፋኖው በስሜኑ በነበረው ጦርነት ላይ የከፈለው መስዋዕትነትና መከላከያንም ከጥቃት ማዳኑንና ድል መቀዳጀቱን እራስዎ በመገናኛ ብዙሃን አወድሰዋል አሁን ደግሞ ውለታ ቢስ በሆነ መልኩ ፋኖን ለማጥፋት ዘመቻ እያካሄዱ ነው
  • በአሁኑ ሰአት በማህበራዊ አንቂዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የታሪክ ምሁራን፣ የጤና ባለሙያዎች፣ ወታደሮች እና እውነትን የሚናገሩ ሁሉ ዜጎችን በጅምላ ማሰር ዋናው የመንግስትዎ ተግባር ሆኗል

ባጠቃላይ በአገሪቱ ውስጥ መረጋጋትና ሰላም እንዳይኖር ሕዝብ እርስ በእርሱ እንዲባላ ማድረግ የስርአቱ ዋና ተግባር ሆኗል። ኢመደበኛ ሰራዊት በኦሮሞ ክልል ኦነግ ሸኔ በሚል የቅጽል ስም እንዲደራጅ አመቻችተው አማራን ሲገድልና ንብረቱን ሲያወድም፡ እያወቁ ምንም እርምጃ አለመወሰዱ መንግስትዎ ሕዝብን መካዱን በግልጽ ያሳያል።
ከተፈጸሙት እልፍ አእላፍ የግፍ ተግባሮች በጥቂቱ ለማሳየት ሞክረናል ለዚህም ዋቢ ለመጥቀስ በቅርቡ በTime Magazine ከመቶዎቹ ዐሉታዊ ገጽታ ካላቸው የአለም መሪዎች ውስጥ አንዱ ሆነው ተመዝግበዋል።

ይሄ ትውልድና የሚመጣውም ትውልድ ስምዎትን ከነሂትለር፣ ሙሶሊኒ፣ ፖል ፖትና ቦካሳን ከመሳሰሉ ሌሎች ክፉና እኩይ የአለም መሪዎች ጋር መዝግቦ ሲኮንንዎት ለዘመናት ይኖራል።

ስለሆነም ይሄንን ሁሉ ተገንዝበው ሕዝብን ከዚህ የላቅ የእርስ በእርስ እልቂት ለማዳን ይቻል ዘንድ በአስቸኳይበኢትዮጵያ ህዝብ ስም ስልጣንዎትን እንዲለቁ እንጠይቃለን!!!

ኢትይዮጵያ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!
ሁላችንም ፋኖ ነን!


በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ የምንኖር የትውልደ ኢትዮጵያ አማራዎች ስብስብ