Page 1 of 1

ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 02:37
by Horus
ይህን ኦንታ የታሪክና የቋንቋ ሊቃውንት ያውቁታል ። እኔ የሃረሬ ቋንቋ መዝገበ ቃላት ፈትሼ 35% የቃላት ተመሳሳይነት እንዳላቸው አውቃለሁ ። ዛሬ ከዚህ በታች ያለውን ቪዲዮ ሳይ ገረመኝ ።

ይህ ሃረሬዎች ሹዋል የሚሉት በአል በጉራጌ አዳብና ከሚለው ጋር አንድ ነው ፣ ነገር ግን የሃረሬው ቃል ሹዋል በጉራጌ ሸቫል ወይም ሸባል እንለዋለን። በጉራጌ የሰርግ በዓል ማለት ነው ። ወንድና ሴት መፈቃቀሪያ አዳብና ከሰርጉ እና ቸግ ከሚባለው የሽማግሌ መላኪያ (ፍጥምጥም) ከሰርግ በጣም ቀድሞ የሚሆን ነው። ግን ሹዋል የሚለው የሃረሮች ቃልና ሸባል የሚለው የጉራጌ ቃል አንድ ናቸው ።

ያ ብቻ አይደለም። ከቪዲዮ ሰር የምታዩት 'ኑግዳችን' የሚለው ሃረሬ ቃል ጉራጌ (ክስታኔ) 'ነግዳኛ፣ ነግዳችን፣ ' የሚለው ሲሆን 'እንግዳችን' ማለት ነው። ስለዚህ 'ነግዳ' በሃረሬም በክስታኔም አንድ ቃል ነው ። ሹዋል እና ሸባል እንዲሁ አንድ ቃል ነው ። እንድ ቀን ሃረሬ ጥንታዊ ባህሉን እንደ ሚመልስ ተስፋ አለን! ለምሳሌ ከሰርግ በፊት የሴት ሙሽሮች እንሾሽላ ባህል። የስልጤ ልጃገረዶች እየመለሱት ነው !

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ

Posted: 14 May 2022, 02:42
by Union
እንተ ዘረኛ ጉራጌ የጨነቀህ እራስህን እንደ ጉድ እያፈላለከው ነው። አንዴ ሱዳን አንዴ ኤርትራ አንዴ አማራ አንዴ ሀረር ተንከራተትክ እኮ።

እኛም መቼ ነው አኮብኩበህ የምታርፈው እያልን ተሰቃየን ኢአር ላይ። በዛ ላይ አርጅተህ መሞቻህ ደርሷል። ምን ይሰራልሀል ሀረሬ ጎራሬ ምናምን አርፈህ ከመካነ እየሱስ በጌታ ስም ብላ ጌዳውን የምትለውን አንዷን ይዘይ ገብተህ አትረጋጋም :lol:

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 02:51
by Horus
ይህ በጉራጌ መስቀል ላይ አዳብና የምንለው ነው ። በሃረሬ ሹዋል አዋቂዎችም አሉበት፣ የወጣቶቹን መተዋወቅና መጣብስ አዎንታ ለመስጠት ማለት ነው። እኛ ጋ ከዚህ ቀጥሎ ሽማግሌ ይላካል፤ ቸግ ይባላል ። ቅልጥ ያለ ድግስ ነው !

የስልጤ ሴጦ፣ የጉራጌ እንሾሽላ !

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 03:11
by Horus
አንዲት ልጅ ከሰርጓ 3 ቀን ሲቀር በዚህ መልክ በወላጆቿና ዘመዶቿ የዎሬ ነሽ ገረ (ይህ ያንቼ ግዜ ነው፣ ይህ ያንቺ ወራት ነው) እየተባለች ተዘፍኖላት አንሶስላ ታስራለች !!!

ይህ ሃረሮች በኢድ የሚያደርጉት ሹዋል ጉራጌ በመስቀል እስከ ጥቅምት አቦ የሚያደርጉት አዳብና ነው ። የወጣቶች መፋቀሪያ ባህል ማለት ነው !!

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 03:35
by Horus
ባዳብና ሎሚ ተዋግተው የተፋቀሩት ወጣቶች ጉዳይ ወደ ሽማግሎች ሄዶ የቸግ (ፍጥምጥም/ኢንጌጅመንት) በዓል ይሄዳል !!

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ

Posted: 14 May 2022, 03:38
by Union
:lol:
union wrote:
14 May 2022, 02:42
እንተ ዘረኛ ጉራጌ የጨነቀህ እራስህን እንደ ጉድ እያፈላለከው ነው። አንዴ ሱዳን አንዴ ኤርትራ አንዴ አማራ አንዴ ሀረር ተንከራተትክ እኮ።

እኛም መቼ ነው አኮብኩበህ የምታርፈው እያልን ተሰቃየን ኢአር ላይ። በዛ ላይ አርጅተህ መሞቻህ ደርሷል። ምን ይሰራልሀል ሀረሬ ጎራሬ ምናምን አርፈህ ከመካነ እየሱስ በጌታ ስም ብላ ጌዳውን የምትለውን አንዷን ይዘይ ገብተህ አትረጋጋም :lol:

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 03:55
by Horus
ዘመናት ተሻጋሪው የሰርግ ዘፈን 'የዎሬ ነህ፣ የዎሬ ነሽ ' በወለኔኛ !!

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 11:04
by Ethoash

አንዳንዴ አቶ ሆረር የመኒዎችን ከስልጤዎች መለየት አቃተህ እንዲህ እነዚህ ሴቶች ቅላታቸው ከየመን የተስደዱ እና የሶሪያ የመጡ አረቦች ናቸው እንጂ ስልጤዎች አይደሉም በደንብ ቅላታቸው ያስታውቃል ፈረንጅ ነው የሚመስለው ፊታቸው ። ትንሽ ውሽት ህንም እወነት ለማስመስል ሞሞከር አለብህ እንደው የጉራጌ ጠበቃ ነህ ስትባል የየመኖችንና የሶርያን ሴቶች ስልጤዎች ማለት ጀመርክ እንዴ ። መቼም ውሽት ህን ማጋለጥ እዳዬ ነው።

Re: ድሮ ሃረሬ (ሃደሬ) እና ጉራጌ አንድ ጎሳ ነበሩ !! ሸባልና ነግዳ፤ ሹዋልና ኑግዳ !

Posted: 14 May 2022, 14:04
by Horus
ኢትዮአሽ
እንዳማረህ ይቅር!! ኤላው አንተን መስልኮ ማሞ ካቻ ጎንደሬ ነው እያለ ነው!! የማንም ለማኝና ምቀኛ ጉራጌ ባይኖር ደስታው ነው!!! ምቀኝነት ይባላል!! አው ትክክል ነህ የጎራጌ ሴቶች ውብ ናቸው!! ብልህ ናቸው? አንተ ፈሶ የጉራጌ ሴት ሴተኛ አዳሪ ሰምተህ አይተህ ታውቃለህ? ውብ ብቻ ሳይሆኑ ክቡር ናቸው? ጉራጌ ወንዱ አይለምን፣ ሴቷ አትሸረሙጥ!! It is the culture, stupid!!!