Page 1 of 1

ሱሊማን አብደላ፤ የአቢይ አህመድ መንግስት ከውድቀት ለመዳን ማድረግ ያለበት 4 ነገሮች

Posted: 12 May 2022, 00:00
by Horus
አንድ፣ ብሄራዊ ምክክር
አለ የሚባለው ብሄራዊ ምክክር ምን እንደ ሆነ በግልጽ ለህዝብ ማሳወቅ ብቻ ሳይሆን አሁን ለዚህ ሁሉ ቀውስና መከራ ምንጭ የሆነውን የዘረርና የጎሳ ጨረባ ተስካር በመሰረቱ የሚለውጥ ሃሳብና እቅድ ለህዝብ በማቅረብ ህዝባዊ አመኔታና ድጋፍ ለማግኘት አስቸኳይ መራርና ቆራጥ ፕላን ላገሪቱ ማቅረብ አለበት ።

ሁለት፣ የኑሮ ውድነት
በቁጥር አንድ የተጠቀሰ ችግር መፍታት ከቻለ መንግስት የኑሮ ውድነቱ ላይ የህዝብ ትብብር በመጠየቅ አዳዲስ የኗኗር ስልቶችን ህዝቡ እንዲጠቀም ለማድረግ መሞከር።

ሶስት፣ የጦርነት ዝግጅት
ይህ አዲስ የጦርነት ዝግጅት ሊሳካና በትግሬ ወያኔ ላይ ብሄራዊ አንድነት መንግስት ሊያገኝ የሚችለው በቁጥር አንድ የተጠቀሰው ብሄራዊ ሪፎርም በሕዝቡ ተቀባይነት ካገኘ ብቻ ነው ።

አራት፣ ከትህነግ ጋር የሚደረግ ድርድር
ይህ መንግስት ትህነግ ድርድር ሊሳካ የሚቻለው መንግስት በአገርም ውስጥና በዲያስፖራ የነበረውን ድጋፍ መልሶ ለማግኘት ከቻለ ብቻ ነው ። መንግስት በተከታታይ የሰራቸውን ስህተቶች በግልጽ እና በቅንነት ለህዝብ ነግሮ በቁጥር አንድ ያለውን የብሄራዊ ሪፎርም ፕላን አጥጋቢና ህዝብ በሚቀበለው ጥልቀት ካቀረበ ብቻ ነው ።



Re: ሱሊማን አብደላ፤ የአቢይ አህመድ መንግስት ከውድቀት ለመዳን ማድረግ ያለበት 4 ነገሮች

Posted: 12 May 2022, 00:47
by Halafi Mengedi

Re: ሱሊማን አብደላ፤ የአቢይ አህመድ መንግስት ከውድቀት ለመዳን ማድረግ ያለበት 4 ነገሮች

Posted: 12 May 2022, 07:22
by Right
Way too late.

People are desperately trying to rescue the leaky boat they are on board.

Basically this is the same advise we gave generously when all this started.