ፊደል ምን ማለት ነው?
Posted: 02 May 2022, 02:03
ኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ሕዝብ አላት ። አንድ መቶ አመት ከመሆኑ በፊት ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ሰው ይኖራታል። ማለትም ዛሬ የተወልደ/ች ልጅ የ95 አመት ሰው ሲሆን/ስትሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር 1 ቢሊዮን ይሆናል ። እነዚያ ህዝቦች ሁሉም በሚባል ደረጃ በግዕዝ ፊደል ይጽፋሉ፣ ከቋንቋ እስከ ፊዚክስ፣ ከሮቦቲክስ እስከ ኒዩሮሎጂ በግዕዝ ፊደል ይጽፋሉ።
ኢትዮጵያዊያን በአለም ላይ ካሉት ጥቂት የራሳቸው ፊደል እና የግዜ መቁጠሪያ ካላቸው ሕዝቦች አንዱ ናቸው ። ያ ልዩ ሕዝብ ያደርጋቸዋል። በፊዚክስ ውስጥ አራት አይነት ግዜዎች ቢኖሩም ትልቁ የግዜ አይነት የግዜ ካርታ፣ የግዜ ማፕ የሚባለው ቀን መቁጠሪያ ወይም ካላንደር ነው። ኢትዮጵያ የራሷ የመሬት (የቦታ) ካርታ ብቻ ሳይሆን የግዜ ካርታ ያላት አገር ነች ። ያ ልዩ አገር ያደርጋታል።
ሌላው የግዕዝ ፊደል ነው ። ፊደል የድምጽ፣ የቋንቋ ካርታ፣ የድምጽ ማፕ ነው። ቋንቋ የማሰቢያ ብቸኛ መሳሪያ ሲሆን የቋንቋ ካርታ የሰው ልጅ ሃሳብ፣ እውቀትና ትውስታ መያዣ፣ ማስታወሻ፣ ማከማቻ፣ማስተላለፊያና መቀመሪያ ነው ። የሰው ልጅ ከፈጠራቸው ጥቂት እጅግ ግዙፍ ከሚባሉት ፍልሰፋዎች አንዱ ቋንቋና ጽሁፍ ናቸው ።
ኢትዮጵያ እንደዚሁ የራሷ ፊደል እና የራሷ ጽሁፍ ካላት ጥቂት አገሮች አንዷ ናት ። ያ ልዩ ያደርጋታል ። በአንድ ቃል ኢትዮጵያ የራሷ ስልጣኔ ያላት አገር ናት ። በትክክለኛ አነጋገር የኢትዮጵያ ስልጣኔ የሚባል ነገር አለ። ልክ የግሪክ፣ የግብጽ፣ ያውሮፓ ስልጣኔ እንደ ሚባለው የኢትዮጵያ ስልጣኔ አለ። ምንም እንኳ በውል እና በፈርጁ ተመርምሮና ተዘግቦ የታወቀ ባይሆንም ።
ይህ ሁሉ መንደርደሪያ ያመጣሁት ‘ፊደል ማለት ምን ማለት?’ ለሚለው ጥያቄ ተገቢውን ክብደት ለመስጠት ነው። እዚህ የፎረም ሃረግ ላይ የ’ፊደል’ ስረቃልና ስነቃል ትንተና ዝርዝር ለማቅረብ አልሻም። የብያኔው (ዴፊኒሽን) እና መደምደሚያው ማስረገጫ (ኤቪደንስ) እዚህ መደርደር አልሻም ። ብቸኛው ቁም ነገር ብቻ እነሆ። ይህን ትርጉም እኔ ሌላ ቦታ አይቼውም ሰምቼም አላውቅም ። የምታውቁ ካላችሁ እስከነምንጩ ከግርጌ ለጥፉልን ።
ፊደል ማለት ልሳነ እግዚአብሄር፣ ልሳነ ፈጣሪ፣ የፈጣሪ አፍ ወይም አፈ እግዚአብሄር ማለት ነው። ቃለ እግዚአብሄር ማለት አይደለም። ቃል የተባለ፣ የተነገረ ቃል ማለት ነው ። አፍ ወይም ልሳን ማለት መናገርያ አካል ወይም ኦርጋን ማለት ነው ። የፈጣሪ ድምጽ ወይም ቃል መግለጫ መሳሪያ ማለት ነው ። ፊደል አፈ እግዚአብሄር ነው። እግዚአብሄር ለማትሉ አፈ ፈጣሪ ማለት ነው።
ኬይር ዬሁን !
በ.አ. (ሆረስ)
ሜይ 1 2022