https://ethiopianreporter.com/article/25364
አሊባባ ከአቶ ኤርሚያስ አመልጋ ጋር ያደረግኩት ስምምነት የለም አለ
1 May 2022
በጋዜጣዉ ሪፓርተር
በአሸናፊ እንዳለና ብሩክ ጌታቸው
የቻይናው የበይነ መረብ ግብይት ቴክኖሎጂ አሊባባ ግሩፕ፣ ከኢትዮጵያዊው የሥራ ፈጣሪ ኤርሚያስ አመልጋ ጋር ምንም ዓይነት የሥራ ስምምነት አልተፈራረምንም ሲል አስታወቀ፡፡
በጥር ወር 2014 ዓ.ም. አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ከአሊባባ ጋር መፈራረማቸውንና በስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ግዙፍ የበይነ መረብ ግብይት ድርጅት ሥራ ለማስጀመር ዝግጅት እያጠናቀቁ መሆናቸውን ለሪፖርተር ገልጸው የነበረ ቢሆንም፣ ዜናው በሚዲያ ከወጣ በኋላ ግን አሊባባ ለሪፖርተር በላከው የኢሜይል መግለጫና የስልክ ልውውጥ፣ እንዲህ ዓይነት ስምምነት እንዳልገባና ዕቅድም እንደሌለው ገልጿል፡፡
በአሊባባ የዓለም አቀፍ ኮርፖሬት ግንኙነት ኃላፊ ሉይሻ ማክ፣ ‹‹ምንም ዓይነት የኢኮሜርስ ቢዝነስ ስምምነት ከኤርሚያስ ጋር አላደረግንም፤›› ብለዋል፡፡
የአሊባባ የአፍሪካ፣ የመካከለኛው ምሥራቅና የአውሮፓ ቢሮ የኮርፖሬት ጉዳዮች ኃላፊ ማጃ ሀውኬ በበኩላቸው፣ አሊባባ በቅርቡ ኢትዮጵያ ውስጥ የበይነ መረብ ግብይት የማስጀመር ዕቅድ እንደሌለው ገልጸዋል፡፡
የአሊባባን ምላሾች መሠረት በማድረግ ለሳምንታት ሪፖርተር ጉዳዩን ለሁሉም አካላት በመላክ የማጣራት ሙከራ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ስለጉዳዩ በድጋሚ የተጠየቁት አቶ ኤርሚያስ፣ ‹‹ስምምነቱን የፈጸምኩት ከአሊባባ የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ነው፤›› ቢሉም፣ የተባሉት ሰዎች ግን ለሪፖርተር ምንም ዓይነት መረጃ መስጠት አልቻሉም፡፡
በድጋሚ ከሪፖርተር በተላከላቸው ደብዳቤ ስለስምምነቱ መረጃ እንዲያቀርቡ የተጠየቁት አቶ ኤርሚያስ፣ ‹‹ስምምነቱ ከዌል ክላውድ ጋር ነው የተፈጸመው፡፡ ዌል ክላውድ የአሊባባ የራሱ ድርጅት ነው፤›› ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ በዚህኛውም ላይ የስምምነቱን ዶክመንት አሳያችኋለሁ ካሉ በኋላ፣ ያሳዩት ግን የአሊባባና የዌል ክላውድ ሎጎ (ምልክት) ያለበት የኮምፒዩተር ጽሑፍ (Slide Presentation) ነበር፡፡
ስለጉዳዩ ድጋሚ የተጠየቁት ሉይሻ፣ ‹‹ማንም ሰው የእኛን ሎጎ እንደዚያ ሊያደርግና ሊጠቀም ይችላል፣ ግን በፍፁም ስለዚህ ዶክመንት አናውቅም፡፡ ዌል ክላውድ የገባው ስምምነትም ከሆነ እንደ አሊባባ ተደርጎ ሊወሰድ አይችልም፤›› ብለዋል፡፡
አቶ ኤርሚያስ ለሪፖርተር ‹‹አሊባባን ወደ ኢትዮጵያ ላመጣው ነው›› ብለው ከተናገሩ በኋላ ግን፣ ከተለያዩ የንግድ ድርጅቶች ጋር ለመሥራት ንግግር እያደረጉ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይሁን እንጂ ከአሊባባም ሆነ ከቻይናው ዌል ክላውድ ጋር አለኝ ስላሉት ስምምነት፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ኃላፊዎችም እንደማያውቁ ገልጸዋል፡፡
‹‹አቶ ኤርሚያስ ከየት አምጥተው እንደተናገሩ አላውቅም፡፡ ደፍረው የተናገሩ ይመስለኛል፡፡ እስከማውቀው ድረስ አሊባባ ኢትዮጵያ ውስጥ መጥቶ እንዲሠራ የሚያስችል የሕግ ማዕቀፍ የለም፡፡ ብሔራዊ ባንክም አሊባባ ቢመጣ በብር ይሁን በዶላር እንዴት መገበያየት እንዳለበት ሕግ አላወጣም፤›› ሲሉ በሚኒስቴሩ የዲጂታል ቴክ ከባቢ ልማትና ቁጥጥር ኃላፊ ካሊድ አህመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡
የኢኮሜርስ ድርጅት ከሚኒስቴሩ የብቃት ማረጋገጫና ከንግድ ሚኒስቴር ደግሞ የንግድ ፈቃድ ማግኘት አለበት፡፡
‹‹እስካሁን ከአሊባባም ሆነ ከአቶ ኤርሚያስም እንዲህ ዓይነት ጥያቄ አልቀረበልንም፤›› ሲሉ በሚኒስቴሩ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ አቤል ሰለሞን (ዶ/ር)፣ ከካሊድ (ዶ/ር) ጋር ተመሳሳይ ሐሳብ ለሪፖርተር አጋርተዋል፡፡
ስለዚህኛውም ጉዳይ የተጠየቁት አቶ ኤርሚያስ፣ ‹‹ሚኒስቴሩን የሚመለከት አይደለም፡፡ ግብይቱ የሚካሄደው በብር ነው፤›› ብለዋል፡፡ የሪፖርተር ዘጋቢዎች ጉዳዩን ለሳምንታት በሚያጣሩበት ጊዜ አቶ ኤርሚያስ በበቂ ሁኔታ ለማናገር ካለመፈለግም ባሻገር ጋዜጣውን እንደሚከሱ በማስጠንቀቅ አስፈራርተዋል፡፡
በ2011 ዓ.ም. የአሊባባ መሥራች ጃክ ማ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የተፈራረሙት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ኢንጂነር) ጋር ሲሆን፣ ስምምነቱም የኢትዮጵያ ምርቶች በቻይና በበይነ መረብ ሽያጭ እንዲቀርቡ የሚያስችል (eWRP) (Electronic World Trade Platform) ይሰኛል፡፡ በቅርቡ የኢትዮጵያ ቡና በዚህ ከመሸጡ ውጪ ለሌሎች ምርቶች መጠቀም እንዳልተቻለ ተገልጿል፡፡
‹‹eWTP በሁለት ዓመታት ዘግይቷል፡፡ በቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ላይ መድረስ አልቻልንም፤›› ሲሉ ካሊድ (ዶ/ር) አስረድተዋል፡፡
Re: አሊባባ ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ምንም ውል እንደሌለው ተገለፀ
በመጀመርያ ደረጃ ማነው ለሪፖርተር ፍቃድ ሰጥቶት ይህን ያጣራው? ወይስ ምንድነው የቆረቆራቸው? ሪፖርተር የወያኔ ዜና ምንጭ በመሆኑ የሆነ ነገር ይኖራል የሚል ግምት አለኝ::
ግን በዚህም በዚያ እያሉ ሰውየውን አላሰራ ያሉት ለምንድነው?
እነዚህ የ*ርሙጣ ልጆች የዚህ አገር ነቀርሳዎች ሳይሆኑ ይቀራሉ?
ኤርምያስ የሚያደርገውን ባብዛኛው እየተከታተልኩት ነው: መጥፎ ነገር :አላየሁበትም:
ከዚህ በፊት ለውጭ ድርጅት/ኢንስቲዩት/ ካምፓኒ ለሆነ ጉዳይ ዶላር ጠይቀውኝ በኢንተርናሽናል ክሬዲት በመቀበላቸው ሳልከፍል ቀርቻለሁ:: ባንካችን ይህንን ቢያሙዋላልን ኖሮ ጥሩ ነበር: ካልሆነ ደግሞ የውጭ ባንክ አገራችን ቢኖር ችግሩን ያቃልለው እንደነበር ፅፌ ነበር:: አሁን የውጭ ባንኮች ሊገቡ እንደሆነ እየተነገረ ነው:: ከተፈፀመ ጥሩ ነው:: ግን ይህንን የሚቃወሙም አይጠፉም::
አሊባባን እኔ በጣም በጣም ነው የምፈልገው:: በጣም የምፈልጋቸውን እቃዎች በ online መግዛት አልቻልኩም:: እናም በጣም አስፈላጊ ነው:: ምኑ እንዳብከነከናቸው አላቅም::
ምንም ሆነ ምን አሊባባም ሆነ አማዞን አገራችን ውስጥ በቀላሉ ተደራሽ መንገድ መከፈት አለበት::

Ermias Amelga is a crook, a con artist, who swindled 2000 Ethiopians out of their hard earned money by promising a deal too good to be true. He pocketed 1 Billion Birr from 2000 individuals by claiming he would build and deliver houses in six short months. Six years passed without delivering a single unit. In those six years, he was running an elaborate ponzi scheme. He finally run out of people buying into his scheme and began writing bad checks for angry customers who wanted to have his head. My cousin is one of his victims. Those hot checks landed him in jail during Hailemariam Desalegn premiership.. He should have stayed there for a minimum of 20 years.
Re: አሊባባ ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ምንም ውል እንደሌለው ተገለፀ
I think he has response for this allegations. But there is also enough space and time to fulfill that. He said that they removed him from his leadership lest he could solve partially the problem. I think he should be given an opportunity to have the case. The government should hands-off from such kinds of scenarios.Bashu wrote: ↑01 May 2022, 09:57Ermias Amelga is a crook, a con artist, who swindled 2000 Ethiopians out of their hard earned money by promising a deal too good to be true. He pocketed 1 Billion Birr from 2000 individuals by claiming he would build and deliver houses in six short months. Six years passed without delivering a single unit. In those six years, he was running an elaborate ponzi scheme. He finally run out of people buying into his scheme and began writing bad checks for angry customers who wanted to have his head. My cousin is one of his victims. Those hot checks landed him in jail during Hailemariam Desalegn premiership.. He should have stayed there for a minimum of 20 years.
Re: አሊባባ ከኤርምያስ አመልጋ ጋር ምንም ውል እንደሌለው ተገለፀ
In a functional country by now Amelga would have been in jail counting his years of a 25 yrs sentence.
In Abiye Ahmed, the Amelga’s and the Berga’S has found a perfect partner in looting.
They are now belittling the role of the Amharas in safeguarding Ethiopia in behalf of Abiye. Can anyone believe that?
I mean they are milking this beautiful country dry with out giving anything back. While the Amharas and Oromos bleed to protect it.
There will be a time when these pests will be dragged on the street to vomit what they loot.