አፋን ኦሮሞ ብቻ ተናጋሪን ሴቄ የሚል ቃል ፍፁም የኦሮሞ ቃል ነዉ ቢባል ስህተት ነዉ የሚል ኣይመስለኝም። ኣማርኛ ብቻ ተናጋሪን ሳቀ የሚል ቃል ፍፁም አማርኛ ቃል ነዉ ቢባል ስህተት ነዉ የሚል ኣይመስለኝም።
ሁለቱንም ቋንቋዎች ተናጋሪን ሁለቱ ቃላት ለምን ተመሳሰሉ ብለህ ብትጥይቀዉ ኣንዳንዱ ተወራርሰዉ ነዉ ይላል። ኣንዳንዱ መሠረታቸዉ ኣንድ ሆኖ ነዉ ይላል። ትክክለኛዉ መልስ የትኛዉ እንደሆነ ለኣጥጪዎች መተዉ ይቻላል።
ቃላት መወራረስ ያለ ነዉ። መሠረታቸዉ ኣንድ መሆንም ያለ ነዉ። እዚህ ያጻፍኳቸዉ ቃላት ለምሳሌ ያህል ነዉ።
እነዚህ ቃላት መሠረታቸዉ ኣንድ ከሆነ በተፈጥሮ የተቀራረቡ ናቸዉ ማለት የሚቻል ይመስለኛል። በተፈጥሮ የተቀራረቡትን ደግሞ የበለጠ ማቀራራብ እንጂ ማራራቅ ያስፈልጋል? ነብዮች መወለዳቸዉ እና የነሱ ትምህርት በሰፊዉ መሰበካቸዉ ኣንዱ ቋንቋ ሌላዉን ቋንቋ ቅኝ ገዛ እስከማለት የምያደርስ ኣይመስለኝም።
ኣንዱ ከሌላዉ ጥርት ብሎ የተለየ ነዉ ለማለት ሌላ አከባቢ በቅርብ ጊዜ የተፈጠሩትን ቃላት ኣለመጠቀም እየተለመደ ነበር። ለምሳሌ ካልተሳሳትኩ መኪና በቅርብ ጊዜ ከታወቀዉ ማሽን የሚል ቃል የመጣ ይመስለኛል።
መኪና ኣማርኛ ዉስጥ የተለመደ ቃል ነዉ። አፋን ኦሮሞ ዉስጥም እንጠቀም ነበር። በሁዋላ አማርኛዉ ከሚጠቀመዉ ለመራቅ ነዉ ማለት በሚቻል ኮንኮላታ የሚል ቃል ተሰጠዉ። ኮንኮላታ ማለት ተንከባላይ ማለት ነዉ። አንድ ተንደባለልሽ የሚል ዘፈን ቪድዮ ዉስጥ የሚታያዉ ተንከባላይ ኣይነት። የዚህ ቃል ችግር የሚገልጸዉ ቁስ ተንከባላዪን ጎማ ብቻ ነዉ። የመኪና ትላልቅ ፈጠራዎች ከጎማዉ በላይ ያሉ ናቸዉ።
ቃሉ በሚገልጸዉ ላይ ስምምነት ካለ ለማንኛዉም ቁስ የተፈለገ ቃል መጠቃም ኣይቻልም ማለት ኣይቻልም። ይህ ቃል በተለምዶ ከሚታወቀዉ ጋር ሲናሳ የኣዲሱን ቁስ የዉስጥ ውስብስብነት የምያቃል ነዉ።
ሌላ ምሳሌ ሮጵላ ስንል የነበረዉ ነዉ። በአማርኛ ኣይሮፕላን የተባለዉ። የሁለቱም ቃላት መሠረት የእንግሊዘኛዉ ኤሮፕሌን ነዉ። ሮጵላ የምንለዉ ተረስቶ በጠያረ ተተካ።
የዚህን ቃል መሠረት ኣላዉቅም። ከምስራቅ ከሶማልኛ ቋንቋ፣ በምዕራብ ከጉሙዝ እና አኙዋክ ተወራራሽ የሆኑ ቃላት መኖራቸዉን እገምታለሁ። በሁሉም ኣቅጣጫ የሚመሳሰሉ ቃላትን የበለጠ ማቀራራብ መልካም ነዉ። በቅርብ ጊዜ እሩቅ ሃገር የተፈጠሩትን እንደ መኪና፣ ኣይሮፕላን፣ ቴሌቭዥን፣ ቪድዮ የሁሉም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች መጠቃም ተመሳሳይ ቢሆኑ ተገቢ ኣይዴለም፧