የአብይ ንግግሮች አራምባ የአብይ ተግባሮች ቆቦ
Posted: 28 Apr 2022, 21:30
የአብይ የሰጠው አንዳንዶቹ ገለጻዎች ጥልቀት ያላቸው ሌሎቹ ደግሞ ማንም ቅን አሳቢ ሰው ሊገልጻቸው የሚችል በሰፊው የሚገልጹ በተለመዶ የሚዘዋወሩ እውቀቶች ናቸው ፤ ባጠቃላይ ጥሩ ሀሳቦች ናቸው በዚህ በኩል ምንም ብዙ ሂሶች ማቅረብ አይቻልም ፤ የአብይ ትልቁ ዲፊሲት ተግባር ላይ ነው በተለይ ደግሞ በጎሳ ትብታብ ውስጥ ገብተው ትክክል ማየት ላቃታቸው የጎሳ እውሮች ይህንን መደስኮሩ ፤ ይህንን ቁምነገር ሳይገነዘቡት ቀርተው ሳይሆን ያላቸውን ቦታ በእውቀት ሳይሆን በጎሰኛነታቸው ያገኙት ስለሆነ አሁን የሚያደርጉትን የማግለልና የማሰወገድ ዘመቻ ልክ እንደ ስራ ዋስትና ስለሚቆጥሩት አሁን ስብሰባው ጨርሰው ሲሄዱ የዛው የወንጀል ስራቸው ላይ ነው የሚዘፈቁት ፡፡
አብይ በዋናነት የሚያሰወግዳቸው ነገሮች እነዚህ ናቸው ፤ አንደኛ የፌደራል ስርአት አረዳዱ በጣም የተንሸዋረረ ነው፤ የፌደራል መንገስቱ ጣልቃ አይገባም 100% ማለት ምን ማለት ነው? ፌደራል ማለት ኮንፌደሬት ማለት አይደለም፡፡ የፌደራል መንግስቱ የኢትዮጵያዊን ዜጋዎች ላይ ጥቃት ከደረሰ የተባለው የፌዴሬሽኑ ስቴት የኢትዮያዊን የመከላከል ፍላጎት ወይም ችሎታ ከሌለው የፌደራል መንግስቱ የመግባት ግዴታ አለበት፤ በአሜሪካን ፌደሪሸን ህግ በተለያዩ ስቴቶች ማህከል የሚካሄዱ ንግዶች ነጻ እንዲሆኑ ሀላፊነት ተስጥቶታል ፤ ስለዚህ አንድ ስቴት ንግዱን የሚያስተጓጉል ህግ ቢያወጣ ፌዴራል መንግስቱ ወደ ፌዴራል ፍርድ ቤት ወስዶ ህጉ እንዲወድቅ ያደርጋል ፤ ለምሳሌ የደቡብ የአሜሪካ ስቴቶች ትምርትቤቶች ጥቁር ተማሪዎች ከነጮች ጋር አብረው ይማራሉ ብሎ የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሲወስን ተቃውሞ ሲያደርጉ የፌደራል ወታደሮች ገበተው ነው ህጉ እንዲፈጸም ያደረጉት ፤ ስለዚህ በፌደራል አደረጃጀት 100% የሚባል ነገር የለም ፤ ይህንንም አብይ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም ፤ ለምን እንዲህ እንደሚል ግን የአራት አመት ስራው በማየት መረዳት ይቻላል ፡፡
ሌላው ደግሞ ህግን ማስከበር ላይ ያለው በጣም መሰመር የለቀቀ ወንጀለኛ በሚያሰደርገው ደረጃ ያለው አመለካከት ነው፤ በየአካባቢው የሚደረጉት ህገ ወጥ የመንገስት የጸጥታ አስከባሪዎችን ስራ ከማውገዝና እንደ ጠቅላይ ሚኒስተር ሁሉም አስተዳደሮች ህግ የማስከበር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የሞራልም ፤ የአስተዳደርም መመሪያ ከመስጠት ወንጀል የሚያበረታታ አመራር የሚስጥ ነው የሚመስለው ፤ እኔ ሀላፊነቴን እንደጠቅላይ ሚንስቴር እየወጣሁ ነው በአካባቢ ያሉት” “ሚሊሻዎች መሪ አይደለሁም” ፤ “ ተመልከቱኝ እኔ የምኖርበት በተመንግስት አካባቢ የሚኖሩትን እያፈናቀልኩ አይደለም “ በአጭሩ በየአካባቢው ያሉ የጸጥታ አስከባሪዎች ህግን የማስከበር ሀላፊነትም ግዴታም አለባቸው ብሎ ሊተወው ይችል ነበር ፤ መሪዎች ሁሉም ቦታ መገኝት የለባቸውም ግን ያላችውን ጠንካራ አቋም መግለጽ ለሁሉም የመንግስት ስራ አስኪያጆች ትክክለኛና የማያወላዳ መልከት መላኩ በቂ ነው ፤ ግን እንደዚህ አይነት ፎሽፋሻ መልክት በመላክ በመንግስ ውስጥ ያሉ ዱርዬዎች ወንጀላቸውን እንዲቀጥሉ አርንጓዴ መብራት እያሳየ ነው ያለው፤
ሌላው ደግሞ በአማራና በኦሮሞ መሀከል ጉልበት የለሽ ገላጋይ መስሎ የሚቀርብበት ዘይቤ ነው፤ እንደ ኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስተር ሁሉም ግዛቶች ላይ የበላይ ቦታን ይዞ እየመራ ያለ ሰው ነው ፤ ሁሉም ላይ ተጸእኖ አለው ፤ ስለዚህ ማተኮር ያለበት ምን ፕሪንሲፖል ኢትዮጵያዊያንን መምራት እዳለበት፤ በዚያም መሰረት እንዲተባበሩ ተጽእኖ ማሳደር ነው፤ እርግጥ ነው ኢትዮጵያ የሁለቱ ብቻ አይደለችም ግን ሁለቱን በፕሪንሲበል ተባብረው እንዲሰሩ ካላደረገ መርከቧ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊረጋ አችልም ፤ ስለዚህ ምንም ችሎታ እንደለለው ከመመሰልና ሲያሰኘው ደግሞ መወገኑን በግጽ እያሳየ ጉልበት እንደሌልው ሆኖ መቅረግ ተገቢ አይደለም ፤
የህግ የበላይነትን ማስከበር 50% በላይ የኢትዮጵያን ችግር ያሰወግዳል ፤ የህግ አስፈጻሚው ከፖለቲካ ነጻ መሆኑን በህዝቡ ዘንድ ታእማኔነት እስካገኝ ድረስ ፤ ለምሳሌ ብዙ ችግሮች ቢኖሩትም የአለፈው ምርጫ ተቀባይነት ያገኝበት ምክንያት ታእማኔ ሁኔታዎችን መፍጠር ስለተቻለ ነው ፡፡ አብይ ተግባር ፤ እስካሁን የተናገርካቸውን እሩቡን እንኳን ተግባር ላይ በታውል ትልቅ የተሳካለ መሪ መሆን ይችል ነበር ፤ ግን ንግግሩና ተግባሩ _ ፊየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲ ሆኖ ህዝቡ አመኔታ ካጣ ቆይቷል፡፡