Page 1 of 1

ኤትኖክራሲ የፖለቲካ ስርዓት እንደ ሌለው ሁሉ የኢኮኖሚ ስርዓት የለውም! የኢትዮጵያ ችግር ያ ነው!!

Posted: 26 Apr 2022, 15:33
by Horus
አሁን ልብ ብላችሁ ብትሰሙ ሰው ሁሉ አንድ ነገር የሚመኘው፤ ያም የእርሻው መስክ ዘምኖ ቴክኖሎጂ በቴክኖሎጂ ቢሆን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ቀውስና ሊፈነዳ የደረሰው የድህነት ወላፈን የሚጠፋ ይመስላቸዋል። ያ ፍጹም ስህተት ነው ። የመሬት ባለቤት የጎሳ ቢሮ ከበርቴ እስከ ሆነ ድረስ ከፊውዳሉ ስርዓት የሚለየው ነገር የለም።

የመጀምሪያ የእርሻው መስክ ችግር መፍትሄ የመሬት ስሪት ነው ፣ መሬትን ከጎሳ የፖለቲካ ነጋዴው የዘር ከበርቴ ማላቀቅ ነው ።

ሌላው በክልል እስር ቤት የታጠረው የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እስትራክቸርና የገበያ ሲስተም ነው ። በመሰረቱ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ለህዝብ የሚበቃ ሽንኩርት፣ ዶሮ፣ በግና በሬ ጠፍቶ አይደለም ዶር በ1500 ብር የሚሸጠው። ዘፋኟ ጂጂ እንዳለችው ባሌ ያረሰውን ሲዳማ ካልገዛ፣ ጎጃም ያረሰውን ሱማሌ ካልገዛ ብሄራዊ ኢኮኖሚ ቀልድ ነው የሚሆነው ።

በሌላ አነጋገር የክልል እስር ቤቶች ፈርሰው ኢትዮጵያ አንድ የኢኮኖሚ ሲስተምና አንድ የገበያ ፍሰት እስካልሆነች ድረስ ያቺ አገር የማምረት ብቻ አይደለም ገበያ አይኖራትም ። ድሮ በ1500 የሚሸጠው ሌባ የሰጠው ምክንያት ዶር ካገር ጠፍቷል አላለም፤ ሰላም ስለሌለ ማጓጓዝ አልቻልንም ነው ያለው ።

ሰላማዊ ብሄራዊ ገበያ የሌለው የትግሬ ወያኔ ባቆመው የጎሳ ኤትኖክራሲና የአቢይ መንግስት በተራው በተቀመጠበት የዘር የክልል ኤትኖክራሲ መንግስትና ኢኮኖሚ ስርዓት ሳቢያ ነው ።

አሁን በስልጣን ላይ ያለው የኢትዮጵያ መንግስትና ኢኮኖሚ ስርዓት ለጎሳ ከበርቴ፣ ለጎሳ ደላላና ለጎሳ ሌቦች እንዲያገለግል፤ በክልል መንግስት ስም 100 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ድሃ ሕዝብ ለመበዝበዝ የቆመ ስርዓት ነው ። ለዚህ ነው ይህ ቆሻሻ የጎሳ ጨረባ ተዝካር እንዳይሻሻል፣ እንዳይለወጥ ጥርስ ነክሰው የሚከላከሉት !

ዝሆኑን በስሙ ጥሩት! የጎሳ ስርዓት ይባላል!!!


Re: ኤትኖክራሲ የፖለቲካ ስርዓት እንደ ሌለው ሁሉ የኢኮኖሚ ስርዓት የለውም! የኢትዮጵያ ችግር ያ ነው!!

Posted: 26 Apr 2022, 16:28
by Abere
እራሷ ዶሮዋ ተሸክማው መሄድ የማትችለውን ብር ሺ ብር ተሸጠች ሲባል እኮ ተናግሬ ነበር - በዓይነት መቀያየር(bartering)። :mrgreen: አንድ ሳህን ሽንኩርት ለመግዛት፤ አጋማሽ ገብስ መስጠት፤ አንድ ዶሮ ፤ለመግዛት ቤዶ ጤፍ መስጠት ወዘተ። :lol: ወረቀት ብር መሬት ላይ የሌለ ኢኮኖሚ መተመን አይችልም - ኢኮኖሚ ስለሌለ። የጎሳ ኢኮኖሚ የለውም ፤ፓለቲካ የለው። ጎሳ band of hunter and gather herd ነው። It is not a rational community, in other words, it is a headless entity and is a reflexive one. The sad thing is, the prime minster himself is an ardent advocate of ጎሳ as political party. ወያኔዎቹ እና ኦነጎቹ የብር ማባዣ ገዝተው ሲያባዙ ነው የሚውሉት። በተጨማሪም አሁን ብር ጋሸበ ለሚባለው ተጨማሪ ምክንያቶች የመንግስት ባንኮች በኦነግ ተዘርፈው ኦነጎች ብር በብር ናቸው። ወያኔም እንድሁ የነበረውን ባንክ በሙሉ ዘርፈዋል - በአውሮፕላን አብይ ጭኖ አዳዲስ ብር አሸክሟቸዋል። ያንን ለማካካስ ደግሞ ዐብይ አህመድ እንደ ጉድ አባዝቶታል። ገበያው ብር ብር በውሸት ብር ተሞልቶል - ምርት የሚያመርት ግን የለም። አምራች የሆኑ አካባቢዎች ወይም በጦርነት ደቀዋል ወይም ከተማ ሄደው መሸጥ አልቻሉም በኦነግ-ብልጽግና ምክንያት። ለምሳሌ ብዙ ጊዜ የእርድ ከብት እና በግ የሚመጣው ከሰሜን ሸዋ (መንዝ) እና ከደቡብ ወሎ ነበር። አሁን ይህ መስመር ተዘግቷል - መንግስት እና ህግ ስለሌለ። የእህል ገበያም የሚጠግበው በተለይ ከሶስት ክፍለ-ሀገር በሚመጥ እህል ነጋደ ነው - ከሰሜን/ምዕራብ ሸዋ፤ጎጃም እና ደቡብ ወሎ አሁን ችግር አለ። ብር ምግብ አይሆን። የጎሳ ስርዐት በአራዊት ደንብ የተሰራ ስለሆነ ሁከት እና ትርምስ ነው እንደ አውሬዎች - ተስማምቶ መኖር አይቻል። What kind of economy can one talk about for a society of herds.