የመጀመሪያው የፌደራሉ መንግስት የባህር ሀይል አቋቁሟል። የባህር ሀይሉ ቢሾፍቱ ወይም ጣና ሀይቅ ላይ እንዲዋኝ ተፈልጎ አይደለም። የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን የያዘ ወይም በጦርነቱ የባህር ሀይል እንደ ወታደራዊ አማራጭ እንዲኖር ስለተፈለገ ነው።
ሁለተኛው ሻቢያ ከተመታ በኃላ በኤርትራ አጠቃላይ ያለውን ነገር የሚቆጣጠረው ወይም የአሜሪካን ወኪል በመሆን ሚና የሚኖረው የኢትዮጵያ መንግስት ነው። ሲቀጥል ሱዳን ናት። ኤርትራ ከድህረ ጦርነት በኃላ የሚኖራት እንቅስቃሴ በዋነኝነት በሁለት ሀገራት ላይ ጥገኝነቱን ይሰራል።
ምስራቅ አፍሪካ ላይ ሰሞኑም የወታደራዊ ስምምነቶች ፣ ከሀገራት መሪዎች ጋር እየተደረገ ያለው ሽርጉድ .. ወርቅነህ ገበየው ቀጠናው ላይ ተፍተፍ የሚለው ወይም የጎረቤት ሀገራት ዲፕሎማሲ ከወታደራዊ ስምምነት አንፃር ተያይዞ አምባሳደሮች ሲሾሙ ወይም ማጠንጠኛው ግልፅ ሲወጣ ..
በተለይ የሰሞኑ የአምባሳደሮች ምድባን ጠለቅ ብለህ ስትመለከተው ይህንን የአስመራ መንገድ መጥረጊያ ነው። የፌደራሉ መንግስት በእነዚህ አራት ወራቶች ውስጥ ያደረጋቸው ቀጠናዊም ሆነ አለምአቀፋዊ እንቅስቃሴዎች ወደኃላ መለስ ብለህ ከተመለከትከው አስመራ ላይ አጥር እየሰራ እንደሆነ ትገነዘባለህ።
አጥሩ ጊዜያዊ ሲሆን የተጠናና የተዘጋጀ አጀንዳ ማስፈፀሚያ ነው። ይህንን በአምባሳደር ባጫ ደበሌ ሹመት መገንዘብ ትችላለህ
የሆነው ሆኖ TDF እና የፌደራሉ መንግስት በዚህ ሰአት ታክቲካል አሊያንስ ሲሆኑ የጋራ ወታደራዊ ዘመቻ ብሎም ቀጠናዊ ፖለቲካው ላይ የሚያደርጉት ወሳኝ እንቅስቃሴ አለ። ፒራሚዱ ደግሞ ምዕራብ ትግራይ ፣ ሱዳን እና ፊንፊኔ ናቸው። ባሻዬ እየጠጣህ
Finfinne Timea
Please wait, video is loading...
Why wasn't Eritrea included in this regional military alliance?
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት በጋራ ለመሥራት ተስማሙ
********************
(ኢ ፕ ድ)
የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት በጋራ በድንበር፣ በሳይበር፣ በማህበራዊ ሚዲያ ዙርያ፣ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በአካባቢ ጥበቃ፣ በወጣቶችና ሥራ አጥነት በሌሎችም ጉዳዮች ለመሥራት ተስማምተዋል።
አሸባሪዎችንና ፀረ ሠላም ኃይሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ሰነድም ተፈራርመዋል።
በቀጠናው ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ዙርያ ሲመከሩ የቆዩት የምስራቅ አፍሪካ ወታደራዊ መረጃ ተቋማት ኢትዮጵያ ለፎረሙ መሳካት ላደረገችው አሰተዋጾኦ አመስግነዋል።
የምክክር መድረኩ ከደህንነት ጉዳዮች ባለፈ በዘርፉ የልምድ ልውውጥን ያካተተ ሲሆን የመከላከያ ዋና መሥሪያ ቤትን፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነትን እና የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተሊጀንስ ኢንስቲትዩት መስሪያቤቶችን ጎብኝተዋል።
ኢትዮጵያን ጨምሮ ጁቡቲ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን፣ ታንዚያና፣ ኡጋንዳ በመድረኩ መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የምስራቅ አፍሪካ የመከላከያ ወታደራዊ መረጃ መድረክ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በአዲስ አበባ የተካሄደ ሲሆን ቀጣዩን የምክክር መድረክ ኡጋንዳ እንደምታዘጋጅ ተጠቁሟል።


Please wait, video is loading...