ሰሚ ያላገኘው የአባ ባሕርይ ምክር
Posted: 22 Apr 2022, 13:28

*
*
Achamyeleh Tamiru
April 22 2022
ሰሚ ያላገኘው የአባ ባሕርይ ምክር
የጋሞ ብርብር ማሪያሙ መነኩሴ አባ ባሕርይ፣ ወራሪው የኦሮሞ የገዢ መደብ በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያን በወረረበት ወቅት ከባሌ በታች ተነስቶ በየስምንት ዓመቱ በሚያካሂደው ወረራ ሀገራችንን ሲያጠፋና የሬሳ ክምር ሲያደርግ በዐይናቸው ያዩ የታሪክ ምስክርና ሀገራችን በኦሮሞ የገዢ መደብ የጠፋችበትን ምክንያት አጥንተው መጪው ትውልድ ይማርበት ዘንድ የጥናታቸውን ውጤት ቀለም በጥብጠው፣ ብራና ፍቀው ጽፈውልን ያለፉ ታላቅ ሊቅ ናቸው።
ሰሚ ያላገኘውን የአባ ባሕርይ ምክር ከማቅረቤ በፊት ስለ ኦሮሞ የገዢ መደብ የተወሰነ ነገር ልበል። ከዚህ በፊት እንዳልኩት የገዳ ሥርዓት በየስምንት ዓመቱ ወረራ የሚካሄድበት ጽልመታዊ ወታደራዊ አደረጃጀት ነው። በዚህ ወታደራዊ የገዳ ሥርዓት መሠረት የኦሮሞ ገዢ መደብ የሚኾነው በገዳ እርከን ስድስተኛው መደብ ላይ የሚገኘው ሉባ የሚባለው የወታደር መደብ ነው። ሉባ እድሜያቸው ከ41-48 የኾኑ የተመሰከረላቸው ገዳይና ወራሪ ወታደሮች ስብስብ ነው። የሉባው መሪ አባገዳ ይባላል። ከሉባ መደብ በፊት ያለው የገዳ እርከን ራባ ዶሪ ይባላል። ራባ ዶሪ ከ33-40 የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ጎረምሳ ወታደሮች መደብ ነው።
የገዳ ሥርዓት ባጠቃላይ ዐሥር መደቦች ያሉት ሲኾን ደበሌ (ከ0- 8 ዓመት )፣ ጋሜ ጥጥቆ (ከ9- 16 ዓመት)፣ ጋሜ ጉርጉዶ (ከ17- 24 ዓመት)፣ ኩሳ (ከ25- 32 ዓመት)፣ ራባ ዶሪ (ከ33- 40 ዓመት)፣ ሉባ (ከ41- 48 ዓመት)፣ ዩባ (l) (ከ49- 56 ዓመት)፣ ዮባ (II) (ከ57- 64 ዓመት)፣ ዮባ (III) (ከ65- 72 ዓመት) እና ጋዳሞጂ (ከ73- 80ዓመት) ናቸው።
በበላኤ ሰብዕ ዐቢይ አሕመድ የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ዘመን ስለ ገዳ ባካሄደው ጥናት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት የተሰጠው ኤርትራዊው ፕሮፌሰር አስመሮም ለገሰ እ.ኤ.አ. በ1973 ዓ.ም. «Gada: Three Approaches to the Study of African Society» በሚል ባሳተመው መጽሐፍ ገጽ 8 ላይ የራባ ዶሪ መደብ ወደ ሉባ ወይም ገዢ መደብ ለመሸጋገር ሊከውናቸው ከሚገቡ ወታደራዊ ተግራባት መካከል ዋና ዋናዎቹ ሲጠቅስ «ሥልጣን ተረካቢው መደብ ሥልጣኑን ከመረከቡ በፊት ቀደምት ትውልዶች ያልወረሩትን አካባቢ በወረራ መያዝ አለበት። ይህ ለየት ያለው ጦርነት ቡታ ይባላል። ቡታ በየስምንት ዓመቱ ሳይስተጓጎል የሚደረግ ጦርነት ነው» ብሏል።
የኦሮሞ ብሔርተኛው ፕሮፌሰር መሐመድ ሐሰንም እ.ኤ.አ. በ1990 ባሳተመው «The Oromo of Ethiopia: A History 1570-1860» በሚለው መጽሐፉ ገጽ 14 ላይ በራባ ዶሪ እርከን ያሉ የአንድ መደብ አባላት ወደ ሉባ መደብ ተሸጋግረው የመደቡ መሪ ወይም አባ ገዳ ለመኾን ከሚጠበቅባቸው መስፈርቶች መካከል ዋናው፣ ቀደምት ትውልዶች ያልወረሩትን አካባቢ ለመውረር በሚደረገው የቡታ ጦርነት የሚያሳዩት ወታደራዊ ጀግነትና በወታደራዊ መስክ ጀግንነታቸውን በተግባር ያስመሰከሩ መኾናቸውን ግዳይ ማቅረብ መኾኑን ጠቅሰዋል።
ራባ ዶሪና ሉባ መደብ ብቻ ሳይኾን የገዳ ሥርዓት ባጠቃላይ ከእድሜ ደረጃ አወጣጥ ጀምሮ እያንዳንዱ የሥርዓቱ ደንቦች የተቃኙት ወታደራዊ የበላይነትን ለማስገኘት ነው። የራባ ዶሪ እድሜውን ጨርሶ ሉባ መደብ የሚገባ ወታደር መሪ ኾኖ የሚመረጠው ሰው ከእድሜ አቻዎቹ ብዙ የገደለው ነው። በራባ ዶሪ ዘመኑ ሰውን አድኖ ገድሎ ለመረጃነት ይዞ ያልተገኘ ሉባ ሲኾን መሪ ወይም አባ ገዳ ኾኖ አይመረጥም። በገዳ ሥርዓት አንዱ የሉባ ወታደር ከጓደኞቹ መካከል በልጦ ለመገኘት በተለይ ወንዶችን፣ በእናት ማኅጸን ውስጥ ያለ ጽንስን ጨምሮ ገድሎ እንደ ሽልማት ይዞ መቅረብ የሥርዓቱ አንድ አካል ነው።
Read more
Please wait, video is loading...