Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42934
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ትልቁ የኢትዮጵያ ትምህርት ስርዓት ችግር ነጻ መሆኑ ነው

Post by Horus » 18 Apr 2022, 13:31

ዛሬ ኢትዮጵያ 120 ሚሊዮን ሕዝብ አላት፤ ከዚያ ውስጥ 30 ሚሊዮን ተማሪዎች ናቸው ። ይህም ማለት ያገሪቱ 25% ማለት ነው። ይህ ቁጥር እያደገ እንጂ አይቀንስም፤ ማለትም በየገጠሩ ት/ቤቶች በተገነቡ ቁጥር ወደ ት/ቤት የሚሄደው የሰው ቁጥር እየጨመረ እንጂ እየቀነሰ አይመጣም።

ስለሆነም ኢትዮጵያ free universal K-12 and higher education (BA, BS, MA, MS, PhD & MD) በመስጠት መቀጠል አትችልም። ይህ የሚቀጥል ከሆነ የትምህርት ጥራትም ሊሻሻል አይችልም ፤ ተማሪውም ለእውቀት የሚሰጠው ዋጋ ሊሻሻል አይችልም። በነጻ የተገኘ ነገር ሁሉ ያለው ዋጋ ዝቅተኛ ነው ።

ስለዚህ በሚቀጥሉት 5 እስከ 10 አመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ወደ ከፍሎ መማር የትምህርት ስርዓት መለወጥ አለባት ። ይህም ሲሆን እያንዳንዱ ወላጅ በአመታዊ ገቢው መጠን የተለያየ ክፍያ ማድረግ አለበት ። ከዚህ ከወላጆች በሚገኘው ገንዘብ አለም አቀፍ ደረጃ ያለው የጠራ ምርጥ ትምህርትና እውቀት መስጠት ያስፈልጋል ።

ነጻ የትምህርት እድል የሚሰጣቸው በሌላው አለም እንደ ሚደረገው ሁሉ በትምህርትና ችሎታቸው እጅግ የላቁ ነገር ግን በድህነት ምክንያት መክፈል ለማይችሉ ብቻ መሆን አለበት ።

ለኢትዮጵያ ትምህርት ውድቀት ቁጥር አንድ ምክኛት 30 ሚሊዮን ሕዝብ ከK-PhD/MD በነጻ ለማስተማር መሞከር ነው ። የሚያስተምሩትን ትምሀር ተፈትነው ያላለፉ አላዋቂዎች አስተማሪ የሚሆኑትም እራሱ የትምህርት ሰርዓቱ የድህነት ኢንዱስትሪ ስለሆነ ነው። በውቀት የላቁ መምህራን በተመጣጣኝ ደሞዝ የሚቀጥር ሲስተም ፈጥሮ ደንቆሮ አስተማሪዎችን ማሰናበት ያስፈልጋል። ማለትም አገሪቱ አንድ እርምጃ ወደ ፊት ትራመድ ከተባለ።