Finfinne Times
Is Home & Away Fixtures ደርሶ መልስ in Amharic?
እንደዚህ ያለኝ ልጅ .. ከመጀመሪያው ትግራይ በመከላከያ በአማራ ልዩ ሀይል በኤርትራ በሶማሊያ ወታደሮች በዱባይ ድሮኖች ስትደበደብ የህግ ማስከበር ዘመቻ ነው ብሎ ሲጨፍር ነበር።
ለማንኛውም የTDF ዘመቻ ውጤት የሆነው የመንግስት የተሳሳተ አካሄድ ውጤት ነው። ጦርነት ለአንተ ወገን ፍትሀዊ ሆኖ ለሌላው ሀጢያት የሚሆንበት ምክንያት የለም። ትግራይን አድቅቀህ ስትወጣ ጥፋቱ ለአንተም እንደሚደርስ መገመት ነበረብህ።
ጦርነቱ ጓዳህ ሲገባ ማልቀስ ከጀመርክ የወገንተኝነትህ በትር ነው እንድታለቅስ ያደረገህ እንጂ የጦርነቱ አስከፊነት ታውቆህ አይደለም። መቀሌን በሻሻ አድርገናል ሲል ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አጨብጭበህ .. የእኔ ዩኒቨርስቲ ወድሞብኛል ብለህ የምታለቅስበት አግባብነት የለም።
በሁሉም ወገኖች ላይ የደረሰው ውድመት ካስተማረህ የጦርነቱን ቀጣይነት አውግዝ። ጦርነቱ ከዚህ በላይ ዋጋ እንዳያስከፍለን ለሰላማዊ ድርድር ፣ ለሰበዓዊ እርዳታ የምትችለውን አድርግ። አይሆንም ካልክ አንተ ወደ ትግራይ በድጋሚ ገብተህ የሚቆም ጦርነት እንደሌለ እወቅ።
የጦርነቱ ሂደት ደርሶ መልስ እንደሚሆን መገመት አለብህ። ጦርነቱ መቀሌ ሲገባ እየጨፈርክ አማራና አፋር ክልል ሲገባ የምታለቅስ ከሆነ .. ለዘመናት አንዴ እየጨፈርክ አንዴ እያለቀስክ ልትኖር ነው ማለት ነው። እሱንም የምትበላው ወይም የምትኖርበት መኖሪያ ቤት የሚኖርህ ከሆነ ነው። አስብበት ባሻዬ !!
Finfinne Times
Please wait, video is loading...