የጉራጌ ክልል ግንድ
Posted: 14 Apr 2022, 01:56
ቅርንጫፍ አለ ግንድ አይበቅልም። ግንድ የሌለው አዲስ ትውልድ ሙጃ ነው። ባህል የሌለው ዘመናዊነት አባት የሌለው ወፍ አራሽ ኩበት ነው። ጉራጌ ክልል መሆኑ የመቼ ጉዳይ ነው። የጥንቱ ጉራጌ፣ የዛሬው ጉራጌም ሆነ የነገው ጉራጌ ሰብስቦ አንድ አድርጎ፣ አንድ ግዙፍ ዝግባ፣ አንድ ግዙፍ ዛፍ፣ አንድ ውብ አበባ አድርጎ የያዘውና የሚይዘው የጉራጌ ሴራ ነው። የዚህ ሴራ ፈጣሪና ጌቶች የጉራጌ ባሊቅ፣ የጉራጌ ጉርዛዘ፣ የጉራጌ ሰነቻዎች፣ የጉራጌ ሽማግሎች ናቸው ።
ዘመናዊ ጉራጌ፣ የጉራጌ ራስ ገዝነት በሉት የጉራጌ ክልል መንግስት የሚቆመው በማንኝውም የዘመኑ ፖለቲካ ካድሬ ላይ አይደለም! የጉራጌ ባሊቆች፣ የጉራጌ ጉሩዎች፣ የጉራጌ አባቶች ሴራ ላይ ነው የዘመናዊ ጉራጌ ስርዓት የሚቆመው! የመላ ጉራጌ፤ በቤተ ጉራ ያለው፣ በመላ ኢትዮጵያ ተዘርቶ ያለው፣ እና በመላ አለም የተበተነው ዲያስፖራ ጉራጌ ሁሉ እንደ አንድ ግንድ ቅርንጫፍና ቅጠል ሰብስቦ አንድ የሚያደርገው የጉራጌ ባህላዊ የሴራ ሸንጎ ነው! ያ ነው የጉራጌ ጉባኤ !! እሱም የጉራጌ ሴራ ጉባኤ ይባላል። ኬይር ዬሁን!!!