Page 1 of 1

3ቱ የኢትዮጵያ ዋና ችግሮችና ፋይዳ ቢሱ የኢትዮጵያ ሚዲያ ኢንዱስትሪ

Posted: 11 Apr 2022, 22:46
by Horus
ይህን ውይይት ስሙ! ለግዜው የጎሳ ፖለቲካ፣ የክልሎችና ሌሎች የዘር ፌዴራሊዝም ወደ ጎን ትተን መላ ኢትዮጵያዊና አለም የተስማማበት ኢትዮጵያ 3 ግዙፍ አሁናዊ ችግሮች፣ ውጥረቶች፣ ቀውሶች፣ ጭንቀቶች አሉባት ፤

እነሱም
(1) የኑሮ ውድነት
(2) የሰላም እጦት
(3) የሙስና ሌብነት መንሰራፋት ናቸው

የኢትዮጵያ ሚዲያ ተብዬ ጫታሞችና ራሳቸው ሙሰኞች የመንግስት ሚዲያ በሉት የግል በነዚህ 3 ችግሮች ላይ ትልቅና ኢንቨስቲጌቲቭ ዘገባ እንኳን ማቅረብ የማይችሉ እንከፎች ናቸው። ይህው እስከ ዛሬ አንድ ይህ ነው የሚባል የሌብነትና የሙስና ታሪክ በመዘገብ የሚታወቅ ሚዲያ የለም ። አልፎ አልፎ ፍትህ መጽሄት ካልሆነ በስተቀር!