Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

የጠቅላዩ ኢትዮጵያ የምትለው ማደናገሪያ ጭምብል ኣሁን ላይ እንዲህ ወልቃ ስናያት፥ ኦነግ

Post by Za-Ilmaknun » 11 Apr 2022, 22:12

ጠሚው የለውጥ ሃዋርያ ተደርገው ሃገሬውን ኣድርንዝዘው በሾኬ ከመጣላቸው በፊት ባለውለታችን የአብዲሳው ልጅ ሽሜ ሁሉን ባያጋልጡት ኖሮ ሳናውቀው ተሰልቅጠን ነበር፣፥

የብሄር እኩልነትን ተጠይፈው የበላይነትን ለማንበር የተጉት ትግሬዎች ዛሬ ላይ ትላንትን በጸጸትና በናፍቆት ቢመለከቱ ፥ ነገር ላይመለስ ተቀየረ። ዛሬም ከስግብግቡና ዘር አጥፊው ትህነግ ስህተት መማር ያልቻለው የኦሮሞ አገዛዝ የጅብ ችኩል ሆኖ ቀንድ መንከሱን ቀጥሎበታል።

የሚፈሰው የንጹሃን ደም ህዝብ ከዳር አንስከ ዳር እያስቆጣ፥ መፈናቀሉ ድርብርብ ችግር እየወለደ፥ ሌብነቱና ስራፈትነቱ የኑሮ ውድነቱን ሽቅብ እያጎነው ፥ ጭምብላሙ ጠቅላይ ሃገርና ህዝብ መምራቱን ችላ ብሎ ማሳ ለማሳ ሲንቀዋለል ታየዋለኽ።

አሁን ላይ ስለተባነነበት መልሶ፥ የትህነግን ጥላ ቢመኝ ባያስገርመንም መጨረሻው ግን ከነሱ የከፋ ለመሆኑ ትንቢት ነጋሪ መሆን አያሻም!!