Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Amnesty and HRW Joint Report reveals the annexation of WolQayit and Raya by TPLF forces in 1992 and the Amhara genocide

Post by Za-Ilmaknun » 07 Apr 2022, 17:15

Despite the slanted reporting by the Amnesty and HRW recent report, there are important facts that came to light. The report undisputedly affirms that the Tigre people are recent comers to the area and they committed genocide against the indigenous people of Amhara to control the lands. The report details the waves of settlements of Tigre people who were brought from Sudan and the proper Tigray province after 1992. The report however, skips how the war between TPLF and the Federal gov't started. The same report intentionally avoids mentioning the over 1,600 Mai-Kadra genocide victims murdered by Tigre Samri militants while mentioning the 60 Tigre who were claimed to have been murdered by Ethiopian forces based on testimonies by the same Samri militants.

https://www.amnesty.org/en/latest/news/ ... ara-towns/

Za-Ilmaknun
Member
Posts: 4487
Joined: 15 Jun 2018, 17:40

Re: Amnesty and HRW Joint Report reveals the annexation of WolQayit and Raya by TPLF forces in 1992 and the Amhara genoc

Post by Za-Ilmaknun » 07 Apr 2022, 18:21

የነጭ ነጭ ውሸት

የውጭ ጉዳይ፣ የፌደራል መንግስት፣ የአማራ ክልል መንግስት የውጭ ተቋማትን የሚያጋልጡበት መልካም እድል አግኝተዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናልና ሂውማን ራይትስዎች በወልቃይት ጉዳይ ዛሬ የጋራ ሪፖርት አውጥተዋል። ይህ የሁለቱ ድርጅቶች ሪፖርት HR6600 ጋር አብሮ እንዲሄድ የተዘጋጀ መሆኑ ከወር በፊት መረጃ ወጥቷል። የሁለቱ ተቋማት ሪፖርት የተመድ ተቋማት ሪፖርት ጋር ቃል በቃል የሚጋጭ፣ ነጭ ውሸት ላይ የተመሰረተ ነው።

OCHA የተባበሩት መንግስታት አካል የሆነ ድርጅት ነው። ይህ ተቋም ከጦርነቱ በኋላ ለትህነግ ቢወግንም ከዛ በፊት በይፋ ያወጣቸው ሪፖርቶች አሉ። ለአብነት ያህል በፈረንጆቹ 2017 ትህነግ "ምዕራብ ትግራይ" ብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረውን አጠቃላይ ሕዝብ ቁጥር በሪፖርቱ አስፍሯል። በኦቻ ሪፖርት መሰረት በወቅቱ በወልቃይት ጠገዴ የሚኖረው (አማራም ትግሬም) ሕዝብ ቁጥር 467 ሺህ 890 ነበር። ይህ ራሱ ትህነግ አካባቢውን በያዘበት ወቅት የተደረገ ሪፖርት ነው። አምነስቲና ሂውማን ራይትስዎች በዛሬው ሪፖርታቸው በዚህ አጠቃላይ 467890 ሕዝብ ይኖርበት በነበረው አካባቢ ስንት ሰው ተፈናቀለበት ብለው መግለጫ አወጡ? 723 ሺህ ሕዝብ‼ ወልቃይት ጠገዴ በዚህ ወቅት ምንም ሕዝብ ባይኖርበትና ሁሉም የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ተፈናቀለ ቢሉ እንኳ 255, 110 ሕዝብን ለሀሰት ሪፖርታቸው መበደር ሊኖርባቸው ነው። ወደ ትግራይ ተፈናቀለ የሚባለው ሕዝብ አጠቃላይ ወልቃይት ጠገዴ ይኖራል ከተባለው ሕዝብ በ255 ሺህ 110 ይበልጣል። ይሄ በትህነግ በኩል ነጮቹ የሰሩት ነጭ ውሸት ነው! ተበድረው አፈናቀሉ ማለት ነው። ነጭ ውሸት!

ይህ እንደማሳያ እንዲሆን እንጅ እጅግ በርካታ ውሸቶች የታጨቁበት ሪፖርት ነው። የድርጅቶቹ ሪፖርት ምን ያህል በሀሰት የታጨቀ ስለመሆኑ ይህ ነጭ ውሸታቸው ማሳያ ነው። የሌለ ያልኖረ ሕዝብ ተፈናቀለ የሚሉ ናቸው። ወልቃይት ጠገዴ ከሚኖረው አማራም ሌላውም ሕዝብ በላይ 255 110 ከየት መጥቶ ይፈናቀላል?

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር፣ የፌደራል መንግስት፣ የአማራ ክልል መንግስት ይህን ነጭ ውሸት መስመር በመስመር ማጋለጥ አለበት። ይህ የሀሰት ሪፖርት እንደ መልካም አጋጣሚ መቆጠር አለበት። ከኖረው ሕዝብ በግማሽ የሚበልጥ ሕዝብ ተፈናቀለ ብሎ የሚሰራ ተቋምን ከዚህ በላይ ማጋለጫ አይገኝም። ይህን እድል መጠቀም ይገባል።

በሀሰት ሲዘመትባት የከረመችው ኢትዮጵያ ይህን እድል ልትጠቀምበት ይገባል። በሀሰት ሲዘመትባት የከረመችው ኢትዮጵያ ለወዳጆቿ ይህን መረጃ አጋርታ ከጎኔ ስለቆማችሁ አላፈራችሁም ማለት አለባት። ውሸታቸውን ተቃውማችሁ ያጋለጣችኋቸው የምዕራባውያንን ተቋማት በእጅጉ የሚያጋልጥ መረጃ እኔው ጋር አለ ብላ ልትጋብዛቸው ይገባል። ኢትዮጵያ በዛሬው ሪፖርት ነጥብ የጣሉትን በመረጃ ማሳደድ አለባት።
ምዕራባውያን በራሳቸው በመስቀለኛ ጥያቄ ወድቀዋል።
መከተል፣ማጋለጥ ይገባል!


via Getachew Shiferaw

Post Reply