በአቶ ስብሃት ነጋ ላይ የዘር ማጥፋት ክስ ተመስርቶበት በእስር ቤት እንድቆይ ማድረግ ይገባል። 59,000 በላይ ለጠፋ ነፍስ ያልጠየቀ መንግስት እራሱን ተጠያቂ ያደርጋል።
ስብሃት ነጋ ከፍተኛ የሆነውን ወንጅል በምስራቅ አፍሪካ በጎንደር ክፍለ-ሀገር ወልቃይት ሁመራ አማራ ህዝብ ላይ የፈጸመ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ጥቁር ሂትለር ነው። ይህ ጥቁር ሂትለር በዘረፈው ገንዘብ እየተጦረ በነጻነት ያለስጋት እንድኖር የሚፈቅድ አገር እና መንግስት ሊኖር አይገባም። በዜጎች ህይወት መቀለድ እና መጫዎት ነው - ይህን የሰው ደም የበላ ሰው በአደባባይ እንደ ሰው ቁሞ እንድሂድ መፍቀድ። ስለዚህ ተመልሶ እስር ቤት ያለምንም የዋስትና መብት በማስገባት የፈጸመውን ወንጀል በማጣራት ተገቢው ህጋዊ እርምጃ ሊወሰድበት ይገባል። ስብሃት ነጋ በአለም አቀፍ ፍርድ ቤት ቁሞ የወንጀሉን ዝርዝር መስማት አለበት። ይህ አማራ እና ኦርቶዶክስ ክርስትና አጥፍቸዋልሁ እያለ ይሚፎርክር ጥቁር ሂትለር በኢትዮጵያ ምድር እንድኖር ሊፈቀድለት የማይገባ እኩይ ወንጀለኛ ነው። ለትውልድ የመቀጣጫ ትምህርት ይሰጥ ዘንድ በድጋሜ ወደ እስር ቤት መግባት አለበት። እንደዚህ አይነት ወንጀለኛ ከዕድሜው በላይ ባጠፋው ነፍስ ብዛት የ 1000 አመት ፍርድ ሊፈረድበት የሚችል ፍጡር ነው።