Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
TGAA
Member+
Posts: 5747
Joined: 07 Apr 2019, 20:34

ይገርማል ይደንቃል የአብያችን ገድል ሰው እየነቀለ ችግኝ የሚተክል

Post by TGAA » 01 Apr 2022, 00:42

በቅርብ በሸዋ ስለተደረገው ጭፍጭፋ ሲናገር ፤ አታጋግሉት ፤ ኦሮሞ አማራ ነው የገደለኝ ይላል አማራ ኦሮሞ ነው የገደለኝ ብሎ ይጮሀል እባካችሁ አታጋግሉት ብሎ ሲማጸን መስማት አቅመ ቢስ ሁለቱም ጋር ጸጥታ ማስከበር አቅም የሌለው ደካማ ችሎታው ውጭ የሆነ አድርጎ ነው የቀረበው ፤ አብይ ቢፈልግ ሁለቱንም ክልሎች እንዲተባበሩ አድርጎ እንደዚህ ያለውን ጭፍጨፋ ማስቆም ይችላል ፤ ድሮም ቢሆን ገበሬ ማህበር ነው የአካባቢውን ጽጥታ የሚያስጠብቀው ፤ መንግስት እርዳታ ካስፈለገ ብቻ ነበር የሚገባው ፤ በወያኔም ግዜ ቢሆን በደርግ ግዜ በዚያ መንገድ ነበር ጸጥታ የሚጠበቀው ፤ አሁን ሙሉ በሙሉ አብይ በትቆጣጠረው ኦሮምያ ቀበለው በኦነግ ይመራል ፤ በገሀድ ያሰለጥናል፤ በገሀድ ያስመርቃል ፤ በጋሀድ ከአካባቢው የሉትን ይጨፈጭፋል ፤ ከራሱ ክልል አልፎ ሌሎች አካባቢዎችብ ያጠቃል ፤ የአብይ መልስ ህግ ይከበር ሳይሆን አንተ እንዲህ ብለህ ትጮሀለህ ፤ ያ ደግሞ እንዲህ ብሎ ይጮሀል የትኛውን ልመን ? ሬሳውን መቅበሪያ ግሬደር ለመላክ ፤ ጋዜጠኞች ሄደው ሪፖርት እንዳያደርጉ ግን መከልከሉ ላይ ግን በብቃት እየሰሩ ነው ፡፡