Page 1 of 1
Horus, Pls listen to this wonderful video by Aster Bedane!! I think you will be proud her!!
Posted: 25 Mar 2022, 07:48
by Wedi
Horus, listen to this wonderful video by Aster Bedane!! I think you will be proud her!!
Re: Horus, Pls listen to this wonderful video by Aster Bedane!! I think you will be proud her!!
Posted: 25 Mar 2022, 12:32
by Horus
wedi,
አስቴር በዳኔ የምታስታውሰኝ አንድ ሕዝብ አሉ። ሶዶ ጂዳ ብለው ራሳቸውን ይጠራሉ። የጉራጌ ኦሮሞ ድብልቅ፣ ጉራጌኛ ኦሮምኛም አማርኛም ጥርት አድርገው የሚያቁ፣ አብዛኞቹ እንሰት ተክለው ቆጮ በክትፎ የሚበሉ፣ አብዛኞቹ እንደ ማንኝውም ጉራጌ ነጋዴዎች የሆኑና ትግሬ አዲስ አበባ ገብቶ ኦነግ ኦነግ እየተባለ እስከ ተዘፈነበት 1990 ድርስ እራሳቸውን ጉራጌ ብለው የሚገልጹ ህዝብ ናቸው ዛሬ ሶዶ ጂዳ የሚባሉት የሰፈራችን ጉራኦሮሞች ። እነዚህ ጉራኦሮሞ ወይም ኦሮጉራጌዎች ከቀረው ኦሮሞ የሚለያቸው አንድ እጅግ ትልቅ ነገር አለ ። እሱም ራሳቸውን ኦሮሞ ይበሉ እንጂ ፍጹም ኢትዮጵያዊ (ልክ እንደ ጉራጌ) ናቸው ። በኦሮሞ ብሄረተኝነትም ሆነ ጭቁንነት ሲንጫረሩ አትሰማቸውም ። እኔ ሁልግዜ አስቴር በዳኔ ሳያትና ስሰማት ፊቴ ላይ ድቅን የምትለው አንዲት የሶዶ ጂዳ አክቲቪስት ነው! ስለእሷ ወላጆች ምንነት ምንም አላውቅም ። ስለዚህ ባለችው ነገር ምንም አልገረምም። ያለችውም ባብዛኛው ትክክል ነው፤ መደመር የልሂቃን መለጠፊያ ታክቲክ እንጅ መሰረት ያለው ቲኦሪ እንዳልሆነ ደጋግሜ ያልኩት ነገር ነው ። አንድ የሃሳብ ፍሬምወርክ እንጂ ምንም ሳይንሳዊ መቆሚያ ያለው ሶሺያል ሳይንስ አይደለም። አቢይ ኢህአዴግ ለመሆኑ እራሱ በአፉ ለውጡ ኢህአዴጋዊ ነው ብሎ ነበር ገና ሲጀምር ። ያ አይደለም ቁም ነገሩ። ፖለቲካ ሂደት ነው፣ ኢቮሉሽንም ሬቮሉሽንም ነው ። ዛሬ ያሉት የፖለቲካ አሰላለፎችና የትግሬ ወያኔ ዘመን የነበረው ለየቅል ነው። የዛሬና የወያኔ ዘመን ሃይል ሚዛን አንድ አይደለም ። በያዝነው ዘመን የኢትዮጵያን ብሄራዊ ፖለቲካ አንድ ፓርቲ ፒፒ ብቻውን ሊቆጣጠር አይችልም ። ለዚህ ምስክሩ ዛሬ ያለው የሃይል አሰላለፍ ነው ። አሜሪካ ተሳስቶ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ነጻነት ላይ አደጋ ሲያመጣ ሕዝብ አቢይን በነቂስ ደገፈ፣ እጅግ ትክክል ነበር። ግን ደደብ ብልጽግና ያ ድጋፍ ለሱና ለጎሳ አገዛዝ የተሰጠ ምስሎት እብሪትና ገነንነት ዳዳው። በአንድ ቅጽበት ያን የድጋፍ ጎርፍ ደረቀበት ። ታሪክ የሚሰራ ሕዝብ ነው ። መንግስት ህዝብን ካላከበርና ሕዝብን ካልፈራ ይጠላል፣ ይወድቃል። ይህ የታሪክ ሕግ ነው ። ግን ሁልግዜ አንድ የፖለቲካ ሰው ነኝ የሚል ማወቅ ያለበት ነገር አለ! ፖለቲካ ፍልስፍና እና ቲኦሪ መሰረቱ ቢሆንም እጅግ ወሳኝ ፍሬ ነገሩ ፕራክቲስ ነው፣ ማህበረሰብ ማደራጃ፣ ማንቀሳቀሻ ብልሃት፣ ስልትና ተግባር ነው ። የሞቀ ወምበር ላይ ተቀምጠው ማናባዊ ትችትና ቅዋሜ ብቻ የሚያስተጋቡ ባዶ ጋን ናቸው። ፖለቲካ እልፍ አእላፍ የጥቅም ቡድኖች ለስልጣን ሃብት፣ ዝና፣ ክብር፣ አላማ እና ራዕይ የሚፏከቱበት ጌም ነው ። ስለሆነም ማንኛውም ፖለቲከኛ የኢትዮጵያን አጀንዳ ሲያራምድ እደፍፋለሁ፣ ከኢትዮጵያ አጀንዳ ሲወጣ አምርሬ እነቅፈዋለሁ ። አንተም ብትሆን ፖለቲከኞችን በግል ከመጥላት ወጥተህ መለኪያህን የኢትዮጵያ አጀንዳ አድርግ አላለሁ!