Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7435
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቦረን ሰገል፣ ገበሮ ሰገልተመ

Post by Naga Tuma » 24 Mar 2022, 19:21

ኣንድ አፈታሪክ ያለዉ ሶዱ ህዳ የተባለ ሰዉ ነዉ በሁዋላ ሶዶ ጅዳ የተባለዉ። ህደ ማለት ስር ማለት ነዉ። ሶዱ ህዳ ስር ያላመደ ሰዉ ነዉ ይላል ኣፈታሪኩ። በእንግሊዘኛ ፕላንት ዶመስትኬሽን የተባለዉ ማለት ነዉ። ይህ ኣፈታሪክ ያለዉ በኢትዮጵያ ታሪክ ዕፅዋትን ማላመድ የጀመረዉ ሶዱ ህዳ ነዉ።

ጀርምስ፣ ገንስ፣ ኤንደ ስቲል የተባለ መጽሓፍ ጽፎ ያሳተመዉ ጃሬድ ድያመንድ ኢትዮጵያ ዕፅዋትን ማላመድ ከተጀመረባቸዉ ሃፈራት ኣንዷ ናት ይላል። ማላመድ የተጀመረዉ ደግሞ ከኣስር ሺህ ኣመታት በፊት ነዉ ይላል።

ይህ ሶዱ ህዳ መቼ የኖረ ሰዉ ነዉ የሚለዉን ጥያቄ ያስከትላል።

የሰዉ ልጅ በጎሳ ጎራ መተዋዋቅ የጀመረዉ መቼ እንደሆነ ኣላዉቅም። ጥንታዊ ይመስለኛል።

ቦረን ሰገል፣ ገበሮ ሰገልተመ የተባለዉ መቼ እንደሆነም ኣላዉቅም። ቦረና ዘጠኝ ነዉ፣ ገበሮ ዘጠና ነዉ ማለት ነዉ። ምናልባትም ከግራኝ መሃመድ ጊዜ በሁዋላ ነዉ ብዬ ኣስባለሁ።

የዛን ጊዜ ከቦረና ወደ መሃል ሃገር እና ሰሜን ድረስ የዘመቱ ነበሩ የሚባል ሰምቻለሁ። ለምሳሌ ወልሶ አከባቢ ደርሶ ከዛም ያለፈ ሊበን የሚባል የቦረና ሰዉ እንደነበር ከልጅነት ጀምሮ ሰምቻለሁ። በቅርቡ ደግሞ ራያ ድረስ የደረሰ ሞሮዋ የሚባል የቦረና ሰዉ ነበር ማለትን እዚሁ መድረክ ላይ ኣዳምጫለሁ።

ገበሮ የተባሉት እነ ሊበን ወልሶ ሳይደርሱ በፊት እዛዉ በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ ናቸዉ። ይህ ማለት እንደእነ ጥላሁን ገሰሰ ወይ ከቦረና፣ ወይ ከገበሮ፣ ወይ ደግሞ ተግባብተዉ ከተወለዱት የተወለዱ ናቸዉ።

ድሮ ሰዉ ከቦታ ቦታ መሄድ የነበረ ነዉ። ሌላ ኣፈታሪክ የሚለዉ ኦርቶዶክስ ሸዋ ዉስጥ የተጀመረ ዘመን አበይ ባቦ የተባለ ከነሶዱ ህዳ ሃገር አከባቢ ወደ ቦረና ሄደዉ ነበር ነዉ።

ይህ ሁሉ አፈታሪክ የሰማሁዋቸዉ እንጂ ትክክለኛ መሆናቸዉን ኣላዉቅም። የምያዉቁ ወይም ማጥናት የሚችሉ ማስተካክል ወይም ኣጥንቶ ማረጋገጥ ይችላሉ። ቦረና ዘጠኝ ነዉ፣ ገበሮ ዘጣና ነዉ የሚለዉ መሻሻል የስፈልገዋል የሚባለዉን የኢትዮጵያ ኣስተዳደሮች ለማሻሻል የሚረዳ ይመስለኛል። ገበሮን ኦሮሞ ዸ ጄናን ቦረን ለክ ዮ ጄዼ ገበሮ ቶሌ ጄዸ። ትርጉሙም ገበሮ ኦሮሞ ነዉ ከተባለ፣ ቦረና ኣይዴለም ካለ ገበሮ እሺ ይላል ማለት ነዉ።