Page 1 of 1

የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 14:18
by Horus
ሆረስ ቃላት አይፈልጥም፤ ባጭሩ ጉዳዩ እንዲህ ነው!

አንደኛ፣
ኢትዮጵያ በጎሳና የዘር ፖለቲካ፣ የክልልና የጎጥ ፍልስፍና በፍጹም አንድ አትሆንም። በጎሳ የቅዠት ቀመር የተሸነሸኑት ክልሎች ሁሉም በሚባል ደረጃ ፍርስርሳቸው እየወጣ ነው። ከትግሬ እስከ አማራ፣ ከኦሮሞ እስከ ደቡብ፣ ከደቡብ እስከ ሱማሌ፣ ከቤኒ ሻንጉል እስከ አፋር እያንዳንዱ ክልል ተብዬ የማያባራ ቀውስ እያስተናገደ ነው።

ኢትዮጵያ ዛሬ በሁለት ብሄራዊ የማይታረቁ ሰንደቅ አላማዎች የተከፋፈለች እና በአስር አስራ አምስት የክልል ባንዲራዎች የተበጣጠሰች አገር ናት ።

በመላ ኢትዮጵያ አንድም ቦታ መረጋጋት፣ ሰላም፣ ሰርዓት፣ ሕጋዊነት እና ተጠያቂነት የለም። ስለምና ደህንነት በጎሳዎች ፉክቻና እርስ በርስ ጦረነት ውስጥ በፍጹም ሊኖር አይችልም። ኢትዮጵያ ሰላም የምታገኘው የጎሳ መንግስትና የጎሳ ክልሎች ሲፈርሱ ብቻ ነው ።

የኢትዮጵያ የጎሳ መንግስት እጅግ ደካማ መንግስት ነው ። በሚታሪ፣ ፖሊስ፣ ጸጥታም ሆነ ሌሎች የአገር ጥንካሬ መለኪያ መንግስት እጅግ ደካማ ስለሆነ ሕግ ማስከበር ያልቻለ፣ አማጺያንን ማስወገድ ያልቻለ፣ ሌቦችን ለፍርድ ማቅረብ ያልቻለ፣ የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ የማይችል ደካማ መንግስት ነው ያለን!

ሁለተኛ፣
የጎሳ አገዛዝ (ኤትኖክራሲ አምባገነነት) በሰፈነባት ኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ደብዛ መጥፋት ማረጋገጫው ኢትዮጵያዊ ዜጋ አለመኖሩ ነው ። ሰንደቅ አላማ ይዞ መንግስት መተቸት በእስር የሚያስቀጣ፣ ብሎም የሚያስገድል ወንጀል ነው ። ዜጋዎች በነጻነት የማይቀሳቀሱበት፣ የማይሰሩበት፣ የማይናገሩበት እና ፍትህ በጉቦ፣ በሙስና፣ በገንዘብ የሚሸጥበት የሚገዛበት የጎሳ ሲስተም ነው የኢትዮጵያ ማህበረሰብ።

ሶስተኛ፣
ብልጽግና በኢትዮጵያ ግዙፍ ቀልድ ነው ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ምግብ መግዛት አይችሉም፤ ልብስ ወድ ነው ፣ ቤት የላቸውም፣ ኪራይ መክፈል አይችሉም፣ ባንድ ቃል ኢትዮጵያዊያን በድህነት የደቀቁ የምግብና መጠለያ ዋስትና የሌላቸው ድሆች ናቸው ።

የኢትዮጵያ ትምህርት 100% ከመውደቁና ከመጨቅየቱ የተነሳ አንድ ተማሪ እንኳ ኮሌጅ ማስገባት የማይችሉ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ያሉባት አገር ነች ። በጎሳ የሚገዛ አገር ዘመናዊ ትምህርት ሊኖረው በፍጹም አይችልም።

ትምህርቱ የወደቀ ሕዝብ ማምረት አይችልም፣ ማሰብ አይችልም፣ ችግር መፍታት አይችልም፣ ጤንነቱን ሊጠብቅ አይችልም ። ከሰው በታች ከንስሳ በላይ የሚኖር የድንቁርና ሰለባ ሆነዋል የኢትዮጵያ ግለሰቦች ።

አራተኛ፣
የኢትዮጵያ ካልቸር፣ ስልተ ህይወት፣ ባህል የፈጠራ፣ የፍልሰፋ፣ የወንድማማችነት፣ የፍቅር፣ የመረዳዳት ባህል ሳይሆን የጥላቻ፣ የወንጀል፣ የጦርነት፣ የአመጽ፣ የመጠፋፋት፣ የመጋደል፣ የቅናንትና የበቀል ካልቸር ሆኖዋል ። የጎሳ ስርዓት ባለበት የፍቅርም ሆነ የመረዳዳት ጤናማ ስልተ ህይወት ፈጽሞ ሊኖር አይችልም።

በዚህም የውድመትና የጥላቻ ካልቸር ሳቢያ ያገሪቱ አጠቃላይ ኢኮሎጂና ኮስሞሎጂ ወደ ውድመት እንጂ ወደ ልማትና ማበብ የማይሄድ ይሆናል ።

በጎሳ ድንቁርና የሚያምን ካልቸር ባለበት ህብረተሰብ የሚኖረው ጤነኛ በአንድ ፈጣሪ ማመን ሳይሆን፣ ዘላለማዊ በሆኑ የስነ ምግባርና ሞራሊቲ ሕግጋት መታነጽና በነሱም መገዛት ሳይሆን በጎሰኝት በተጨማለቁ ሃይምኖቶች ተከፋፍሎ በጎሳ ፖለቲካ ውስጥ የገነነውን የዘር ጦርነት በሃይሞኖት መሃል ማፋፋም ነው የተያዘው ። ሁለቱም ፖለቲካም ሃይማኖትም የስልጣን፣ የገንዘብ፣ የዝናና የክብር፣ የስታተስ ምንጮች ስለሆኑ ።

በአንድ ቃል ብልጽግና የሚባለው የጎሳ ከበርቴዎችና የጎሳ ሌባዎች ስብስብ የኢትዮጵያን ብሄራዊ አጀንዳና የኢትዮጵያን ሕዝብ ህልውና፣ ጥቅም፣ እድገትና ስልጣኔ ሊሸከም፣ ሊያራምድ፣ ሊያሳካ በፍጹም አይችልም።

በዛሬይቱ ኢትዮጵያ መደረግ ያለበት ብቸኛ ዳያሎግ ይህ ነው!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 14:37
by Right
Horus,
Good point. You deserve credit for this analysis.
Organize it as an article and put it for a larger audience.
Good journalists in Ethiopia will gladly put it out on their news out let.
For your age and experience this is what you should be doing. Instead of crowning the 7th king “ataturk”. I believe you sensed that he is finished.

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 14:43
by Horus
ውድ አንባቢዎች እስቲ ከላይ ያሉት አራት የኢትዮጵያ አጀንዳ ቁም ነገሮች ይዛችሁ በመላ አገሪቱ ውስጥ የሚካሄዱት ነገሮች፣ የሚደረጉት የሕዝብ እሮሮዎች፣ የሚባለው የሚጻፈው፣ የሚሰበከው ሁሉ ከነዚህ አራት አጀንዳዎች ጋር አስተያዩአቸው! የትግሬ ሕዝብ ወደ አማራ መሰደድን ጀምሮ እስከ ሯጮች የጎሳ ንትርክ፣ ከቦረና ድርቀት አንስቶ እስከ 12ኛ መልቀቂያ ፈተና ፣ ከብልጽግና ሌቦች እስከ እስከ ዘይት ሌቦች ሁሉም የ30 አመት የዘር አገዛዝና የዛሬ ተረኞች መክሸፍ ማረጋገጫ ነው። ነገም የሚሆነው ይህ ነው! ይባስ እንጂ እየተሻለው አይመጣም ። ይህ ሁሉ መሻሻል የሚጀምረው ዛሬ ዛሬውኑ የዎያኔን ስርዓት በኦሮሞ መቀጠል ሳይሆን ይህን ቆሻሻ ሲስተም መለወጥ ስንጀምር ብቻ ነው!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 15:52
by Lovetarik
Dear Horus,

As I said it before, you are the only sane person in this forum. All are gone insane because nausating hatred for fellow citizens who do not belong to their ethnicity. Ethnic hatred is like an opium addiction most retards here cannot get out of.

No amount of training will change their mind. The only way Ethiopia can go forward is for this retards to die off and then we can start from a clean slate. Look at halafi leflafi, he is incorrigible and may soon die with his hate in his bossom. The root cause of ethnic violence is inferiority complex. The subject may not realize it, but its inferiority complex playing on his/ her mind

It amazes me why people cannot see beyond ethnicity. An average Ethiopian may live to be 55. Why people cannot enjoy their limited time on earth in peace instead of bitching about their ethinic is especial is beyond me.

But as to you, dear Horus, you are above the crowd.

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 18:51
by Horus
Lovetarik wrote:
24 Mar 2022, 15:52

Lovetarik,
አመሰግናለሁ፤ አው ኢአር በጣም አሰልቺ ጥቂት ሰዎች ተመሳሳይ ብሽሽቅ የሚደጋግሙበት መደንቆሪያ ፎረም ነው። አልፎ አልፎ ድብርቱን ለመስበር እንሞክራለን።

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 19:50
by sun
Lovetarik wrote:
24 Mar 2022, 15:52
Dear Horus,

As I said it before, you are the only sane person in this forum. All are gone insane because nausating hatred for fellow citizens who do not belong to their ethnicity. Ethnic hatred is like an opium addiction most retards here cannot get out of.

No amount of training will change their mind. The only way Ethiopia can go forward is for this retards to die off and then we can start from a clean slate. Look at halafi leflafi, he is incorrigible and may soon die with his hate in his bossom. The root cause of ethnic violence is inferiority complex. The subject may not realize it, but its inferiority complex playing on his/ her mind

It amazes me why people cannot see beyond ethnicity. An average Ethiopian may live to be 55. Why people cannot enjoy their limited time on earth in peace instead of bitching about their ethinic is especial is beyond me.

But as to you, dear Horus, you are above the crowd. :lol: :lol: :lol:

Really?
:P :P
The above the crowd baboon king of kings. Even king baboons keep their chest pumping bragging when trying to display that they are above the crowd. That means that he is above the ordinary monkey crowds like you. So keep dancing at king baboons fake drumming. Okay? Okay!
:lol:

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 24 Mar 2022, 20:36
by Horus
የትግሬ ዘረኞች በተወዳጇ የኢትዮጵያ ዕንቁ ደራርቱ ቱሉ ላይ ዘመቻ ከፈቱ!! የትግሬ ጎሳ ፖለቲካ የመጨረሻው ዝቅጠት!!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 00:27
by Wardoffa
Maybe you missed this? Do you want to change this? “ሶስተኛ፣ ብልጽግና በኢትዮጵያ የዝንጀሮ ቀልድ ነው ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች…”. Real ahadawis use “የኢትዮጵያ ሕዝብ…” in the singular not “ሕዝቦች” in the prular 😩 "Fake it till you make it", eh?

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 01:35
by Horus
Wardoffa wrote:
25 Mar 2022, 00:27
Maybe you missed this? Do you want to change this? “ሶስተኛ፣ ብልጽግና በኢትዮጵያ የዝንጀሮ ቀልድ ነው ። የኢትዮጵያ ሕዝቦች…”. Real ahadawis use “የኢትዮጵያ ሕዝብ…” in the singular not “ሕዝቦች” in the prular 😩 "Fake it till you make it", eh?
'ሕዝቦች ማለቴ ግድፈት ነው እታረማለሁ! በሰዋስም ሰው (ሰብ) ነጠላ፣ አህሰብ፣ አህዛብ (ሕዝብ) የብዙ ስም ነው። አመሰግናለሁ ! ፤ብልጽግና የዝንጀሮ ቀልድ ነው ያልኩት ፖለሚክስ ነው። ብልጽግና ፓርቲውን ማለቴ አይደለም፣ ባለ ጸጋ ፣ ሃብታም። ዲታ መሆን ማለቴ ነው ። ሰፊው ሕዝብ ከሚኖርበት ድህነት ጋር ሲነጻጸር እጅግ ግዙፍ ቀልድ ነው ለማለት ነው የሞከርኩት! ዘንጀሮች ሲስቁ ድዳቸው በሰፊው ከፍተው ስለሆነ ያን እንደ ሜታፎር መጠቀሜ ነበር ። ሶስተኛው የኢትዮጵያ አጀንዳ በመሰረቱ የሚያካትተው የሕዝብ ብልጽግና ፣ ትምሀርትና ጤንነት ናቸው ብዬ ስለማምን ነው። ኬር!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 02:35
by Horus
ብልጽግና የራሱን የቀበሌ አባልት ሰብስቦ የማስመሰል ህዝባዊ ውይይቱን ትቶ ያገር ችግር ለመፍታት በተግባር ማሳየት ነው ያለበት! የአዲስ ከተማን ድሃ ሕዝብ እንዴት ዘይት መቆጠብ እንዳለበት መስበክ ሕዝቡን መናቅ ነው !

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 12:53
by Horus
ዘውዱ ሾው የረሳው አንድ ነገር አለ። ብልጽግና እራሱ ባዘጋጀው እሮሮ መስሚያ ውይይት ላይ ሺ ግዜ ተደጋግሞ ሕዝብ የጠየቀው ጥያቄ ሄችሻር 6600 ማስቆም አይደለም። ሕዝብ ሺ ግዜ የጠየቀው የዘር አገዛዝ እንዲፈርስ፣ የኢትዮጵያ ብቸኛ ሰንደቅ አላማ ይከበርልን ነው ያሉት! ሕዝብን አለማክበር፣ ሕዝብን አለመፍራት እብሪት እና ገነነንት ይባላል።

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 14:57
by Horus
ከንቲባ አዳነች ቀድሞ ነገር ደፍራ ኮልፌ ቀራንዮ አልሄደችም። ሌላው ቀርቶ አዲስ ከተማ መርካቶ እንኳ መሄድ ፈርታ የቱሪዝም ሚኒስቴሯን ነበር የላከችው። የቱሪስት ሚኒስትሯ ቀደም ሲል በመርካቶ አካባቢ ስለ ምትወደድ ማለት ነው

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 15:50
by DefendTheTruth
Lovetarik wrote:
24 Mar 2022, 15:52
Dear Horus,

As I said it before, you are the only sane person in this forum. All are gone insane because nausating hatred for fellow citizens who do not belong to their ethnicity. Ethnic hatred is like an opium addiction most retards here cannot get out of.

No amount of training will change their mind. The only way Ethiopia can go forward is for this retards to die off and then we can start from a clean slate. Look at halafi leflafi, he is incorrigible and may soon die with his hate in his bossom. The root cause of ethnic violence is inferiority complex. The subject may not realize it, but its inferiority complex playing on his/ her mind

It amazes me why people cannot see beyond ethnicity. An average Ethiopian may live to be 55. Why people cannot enjoy their limited time on earth in peace instead of bitching about their ethinic is especial is beyond me.

But as to you, dear Horus, you are above the crowd.
We repeatedly said before in here that we do understand the side effect of የጎሳ ስርዓት and also appreciate the fact that a medicine is taken to cure the illness, even when one is aware of its side-effects.

Now a brilliant mind will suggest a replacement to the side-effect causing medicine to treat the illness before trying to just start to curse the medicine currently in use.

Short of that is just keep repeating the same old claim again and again without any prospect for a breakthrough, in my view.

Why was it needed in the first place? just out of luxury or an abuse on the part of just few?

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 16:48
by Abere
Talking about the death of ethnic/tribal party and federation is just talking the same obvious thing over and over again. In me, I more than 100% confident ethnic federation and ethnic party is going to be locked in its burial coffin. It is moribund and is on an absolute death track. Simply some paid OLF or TPLF thugs littered this forum with childish level explanations does not mean, ethnic politics is not dying. The so-called ውታፍ ነቃይ are simply here to nurse the dying TPLF -OLF tribal politics, because it is their means of living.

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 17:00
by Horus
DTT
ሌሎች ሰዎች ማንበብ እንዲችሉት ሃሳቤን በአማርኛ ልጻፈው ። ዲፊን ዝ ትሩዝ ስለ ብሄር ጥያቄ እንዴት እንዲህ ትላለህ? እኔ ቁምጣ ሳልለብስ ጀምሮ በዚህ ጥያቄ አይ ያልተደረገ ጥናት፣ ያልተደረገ ምርምር፣ ያልተደረገ ክርክር፣ ያልተደረገ የጦርነት አይነት የለም ። የራስ እድል እስከ መገንጠል የሚለው የማርክሲስት ሌኒኒስት ዶግማ በሁለተኛ ደረጃና የኮሌጅ አንደር ግራዷተ ደመ ሞቃት ስሜታዊ 17 እስከ 23 አመት ወጣቶ የበላይ ሆኖ የትውልዱ አይዲሎጂ ከመሆኑ በፊት ሪጅናሊዝም የሚባል የሰከነ የዛሬን ቀውስ ሲያሶግድ ይችል የነበረ ሃሳብ ቀርቦ ነበር፣ በሰል ባሉት ሁለተኛ ዲግሬ ተማሪዎች ፣ ተሸነፉና ያ ሃሳብ ውድቅ ሆነ። ዋለልኝ የእስታሊንን ትንሽ መጽሃፍ 'ኦን ዘ ናሽናል ቆሽችን የምትል ተርጉሙ አላንዳች ያገር ውስጥ ምርምር፣ አላናዳች የኢትዮጵያ ነባርዊ እውነታ በወረደ ውጠን ይህው እስከ ዛሬ በማይሰራ ፎርሙላ ላይ እየሞትን አለን።

የኔ ወንድም፣ ማንኛው ነገር ትክክለኛ ዲዛይን አለው፣ ማናኛውም ስኬታማ ነገር ኢፌክቲቨ እና ተገምቢ የሚያደርገው ትልልከኛ ፎርሙላ፣ አልጎሪዝም፣ ዲዛይን፣ ስልት፣ ብልሃት አለው ። የኢትዮጵያዊያን የቋንቋና የጎሳ ብዝሃዊነት ችግር መፍትሄ በብሄር ጥያቄ አለመሆኑ ይህው የ50 አመት ልምድ አረጋግጦታል ። የጎሳዎች ጥያቄ መሰልጠን፣ ማደግና ቁንቋቸውን መጠቀም ነው ። ዛሬ በብሄር ጥያቄ የሕዝብ አንድነትና ትብብር አፍርሰን አገር የዘላለማዊ ጦርነት ሜዳ ከማድረግ ባለፈ አንድም ሌላ ፋይዳ አለፈጠረም ። ዛሬ ያሉት ኢንዱስትሪያል ፓርክና ኩታ ገጠም እርሻዎች ከብሄር ጥያቄ አንድ የኢያገናኛቸው ነገር የለም። አንድ ጎሳ በራሱ ቋንቋ ራዲዮና ጋዜጣ ማውጣት ከጎሳ ፌዴሬሽን ወይም ክልል ጋር ምንም አያገናኘውም።

ስለዚህ አንተ ሜዲሲን ወይም የበሽታ መድሃኒት ያልከው ፈጽሞ አግባብ የሌለው ሎጂክ ነው። የብሄር ጥያቄን ይዘን የዘፈነንው አንዳችም ያገር በሽታ መርመራ ሳናደርግ ነው ። ከዲያኞሲስ በፊት የተጻፈ ፕሪስክሪፕሽን ነው ። ስለዚህ በኢትዮጵያ ውስጥ አንድ ጎሳ ባህሉን እንዴት ያሳድጋል? ቋንቋውን እንዴት ያሳድጋል/ይጠቀማል? አንድ ጎሳ እንዴት ከረሃብ ይወጣል? ለሚሉት ጥያቄዎች ሁሉ መልሱ የብሄር ጥያቄ አይደለም !!1 ይህ ነው ብሬክስሩ ወይም ሰብሮ ወጪ አመለካከት!

ኢትዮጵያ ውስጥ ተዘዋውረህ በኢኮኖሚ የበለጸጉ፣ በባህል፣ በቋንቋና በቴክኖሎጂያቸው ያደጉ የተሻሉ ጎሳዎች ለምን ያን ስኬት ላይ ደረሱ ብለው ጠይቅ! በብሄር ጥያቄ ወይም በጎሳ ንትክር አይደለም! ያን ያደረጉት በመሰረቱ በትምህርትና በኢኮኖሚ ታታሪነት ነው። ያልተማረ ጎሳ ባህሉንም ሆነ ቋንቋውን ሊያሳድግ አይችልም፣ አይጽፍም፣ አይፈላሰፍም፣ አይፈጥርም፣ አይስልም ፣ አይመራመርም! በሌላ በኩል አንድ ጎሳ በትምህርትና ኢኮኖሚ ባድገ ቁጥር የብሄር ጥያቄ አላስፈላጊ ግዜ ማባከኛ ጉንጭ አልፋ መሆኑን ይገነዘባል!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 17:14
by Abere
እግዜር ሆረስን ይባርከው - ዕድሜ ይስጥህ።

በዜግነት ስሜት ብቻ በነጻ ተነሳስቶ እኮ ነው ዖፈ ሰማያት የኦነግ እና የወያኔ ካድሬ ተሃዲሶ አስገብቶ ሌክቸር የሚሰጣቸው - ከዚህ ፎረም ላይ። በርካታ ምሁራን በኮሌጅ እየተከፈላቸው ከጎሳ እንቁላል እባብ ይፈለፍላሉ። ሆረስ ግን ከቀላል እስከ ከፍተኛ ኮርስ እያስተማረ ነው በዚህ ፎረም ላይ - ችግሩ ወያኔዎች እና ኦነጎች ከብዷቸው ሲወድቁ ነው የምናየው። ምናልባት ተስፋ ይኖር ይሆን? ማን ያውቃል? ቅዱስ ያሬድ 7 ጊዜ ትምህርት አልገባው ብሎ ወድቆ በስምንተኛው አልፏል ይባላል። ወያኔ እና ኦነጎች ይህ የድድብና ድድብና ገብቷቸው ከለቀቃቸው - ሆረስ ዘርቶ ቃመ ማለት ነው:: ያ ካልሆነ አብዮት ማዕበሉ ጠራርጎ ያሽረኛል።

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 17:48
by DefendTheTruth
Horus,

in my view there is a reason for adopting this form of administration, so identifying that reason and rectifying the pitfalls it caused is the responsibility of the intelligentsia.

Here it is important to differentiate between two cases:
1- Was there a reason for adopting የጎሳ ስርዓት and address that, in case there was one.

2- Irrespective of any reason that might have led to the adoption demanding just the demolition it are different in my view. Our demands and actions should always be based on reason.

We don't necessarily need የጎሳ ስርዓት, especially in light of what it caused in the last few years in our country, including a devastating war, we should demand to get rid of it. But how?

We can discuss and propose an alternative, short of any proposal that could challenge the unity and territoria integrity of the nation, any sort of withering the age old fraternity between the people of Ethiopia should be condemned by all sides. Ethiopia is for all Ethiopians, Ethiopians are diverse, we have to acknowledge that, understand ourselves for what we are. If we realize ourselves for what we are then we will not be tempted to take on anything that is made for us on the basis of one-size fits all. Ethiopia's speciality should be taken into consideration in our exercises.

I don't think I have anything against education, not only for any group of people in Ethiopia, but also for anyone anywhere in this world. My motto is that education changes many things, if not everything.

No one should be denied that right in his/her own country, if we wish to have the great Ethiopia we all dream for.

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 25 Mar 2022, 20:25
by Horus
አበረ፣
ምስጋና አታብዛብኝ፣ በኋላ ደሞ አዋቂ ነኝ ማለት እንዳልጀምር !!!! አመሰግናለሁ።
ዴፌንድዘትሩዝ፣
ደጋግመህ መፍትሄ አምጣ ትለኛለህ? ስንቴ ለመልስ?
(1) የጎሳ ሰርዓት ሕገ መንግስትና መንግስት የሆነው የጎሳ ፍልስፍና ትክክል ስለሆነ አይደለም ወያኔና ሻዓቢያ የሚባሉ ተገንጣዮች በመላ አረብና አሜርካ ተደግፈው ታጥቀው የኢትዮጵያን መንግስት አፍርሰው በሃይል አገሪቷን ስለተቆጣጠሩ ነው ። ያ ከጎሳዎች መብት፣ እድገት፣ ምናምን ጋር አንድም ሎጂካል ትስስር የለውም ።
(2) ዛሬ በኢትዮጵያ ያለው የመሬት ጥያቄ እንጂ የብሄር ጥያቄ የለም ። ጎሳዎች ሁሉ የሚታገሉት የኢትዮጵያን ብሄራዊ መሬት የኔ የኔ ብለው በክልል ከፋፍለው መሬት ለመቆጥጠር እንጂ የቋንቋም የባህልም የሃይማኖትም ጥያቄ አይደለ።

ብቸኛው ሃቅ መሬት ላራሹ ሳይሆን መሬት ለጎሳ የሚል ሆኖ ያ ደሞ የያንዳንዱ ጎሳ ከበርቴ መነገጃ መክበሪያ መዝረፊያ ስልተ ሌብነት ስለሆነ ነው ። የኢትዮጵያ መሬት ከፊውዳል ባላባት ወደ ጎሳ የመሬት መሳፍንት ነው የተሸጋገረው። የነገሩ ሁሉ ቁልፍ ማግኘት ከፈለግህ ሃቁ ይህ ነው ። የመሬት ክፍፍል ትግል ነው የሚካሄደው!
(3) ወደ ፊት እንዴት እንሂድ ለሚለው፤
(ሃ) አለ ምንም ቅድመ ዝብዝብ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሰንደቅ አላማውን እንዲያውለበልብ ዛሬውኑ በአንድ መስመር ቀጭን ፖሊሲ ማወጅ ። የድሮ ባንዲራ አልፈልግም የሚል ማንኛውም ሰው የፈልገውን ቀለም ይዞ ይውጣ። አይ እኔ የሆነ ጭቁን ጎሳ ነኝ ና ጉራጌ አረንጓዴ ቢጫ ቀል ሰንደቅ መያዝ የለበትም ፣ እኔ ነጻነት የሚሰማኝ የሌሎችን መብት ስገፍ ነው የሚለው የከብቶች ሎጂክ ነው ።

(ለ) ከዚያ ባለፈ መላ ኢትዮጵያ ሳይካፈልበት ሳይወከልበት በትግሬ ሽዝፍቶች በላያችን ላይ የተጫነው ሕገ መንግስት፣ የኔ ክክልነትና የዘር ፌድሬሽን ለሕዝብ ውሳኔ አውጥቶ ማንጠፍ ነው ። ሕዝቡ መልስ አለው !!!

Re: የኢትዮጵያ የጎሳ ስርዓት መፈራረስና የብልጽግና ፓርቲ ውድቀት

Posted: 27 Mar 2022, 11:59
by Horus
ስለ ጎሳ ሰርዓት ውድቀትና መፈራረስ እኔን ካላመናችሁ ይህን ውይይት ስሙ!