እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞችን ያስደመመው ግን ‘ስልጡኑ ጋዜጠኛ’ ወንድማገኝ፡ ሎንደን ላይ ተቀምጠህ ለመዝራት የሞከረው እንክርዳድ ነው።
“እንደሚታወቀው ፋሺስቷ ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የሮማው ጳጳስ የፋሽስቱን ሰራዊትና መድፍ ባርከው እንደላኩ የሚታወቅ ሆኖ . . . ” በማለት፤ ልትረጨው የሞከርከው የውሸት ታሪክ፡ ኢትዮጵያዉያን ካቶሊኮች ሰምተው እንዳልሰሙ ቢምሩህም፤ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች ግን እንዲህ ዓይነቱ ምንጭ-ኣልባ የውሸት ታሪክ፡ በዚህ ክፍለዘመን እንደማይሰራ ስንነግርህ በኤርትራዊ ካቶሊካዊ ጭዋነትና ኩራትም ጭምር ነው።
ወዳጃችን ወንድማገኝ፡ የታላቁን ኢትዮጵያዊ የታሪክ ተመራማሪ የአምባሳደር ዘውዴ ረታ “የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት” በሚለው ዳጎስ ያለ የታሪክ መጸሐፋቸው በምዕራፍ ፲፮ ከ ገጽ 295-315 “የቫቲካን ኣቋም በኢትዮጵያ ጉዳይ” በሚል ርእስ ስር የግዜውን ታሪክ ቁልጭ አድርገው አስፍረውታል። ያንተው ምንጭ-አልባ ውንጀላም በታሪክ ዓይን ሲታይና ሲፈተሽ ፉርሽ መሆኑን ገልጸውልናል።
እንዲህ ይላሉ ኣምባሳደር ዘውዴ ረታ ታሪኩን እንደወረደ ሲዘከዝኩ
ኣምባሳደር ዘውዴ ረታ፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት" በሚል መጸሓፋቸው በገጽ 295-315 wrote:የመላው ዓለም ካቶሊኮች ኣባት ቅዱስ ፒዮስ 11ኛ፤ ዱቼ ሙሶሊኒ ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት ለመያዝ የሚያደርገውን ጦርነት መደገፋቸውንና ተዋጊዎቹን ወታደሮቹን እንዲሁም መሣሪያዎቻቸውን መባረካቸውን የሚያመለክት አንዳች መረጃ አለመገኘቱ በድጋሚ መታወቅ አለበት። በዚህ ጉዳይ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ያላቸው አስተያየት ምን እንደሆነ የዚህ መጽሐፍ ደራሲ በሮም አምባሳደራቸው በነበረበት ጊዜ ላቀረበላቸው ጥያቄ፤ ጃንሆይ የሰጡትን መልስ ከዚህ ቀጥሎ ለአንባቢዎቹ ያቀርባል . . . ።”
ፒዮስ 11ኛ ነሐሴ 27. 1938- ሞሶሎኒን ሲጋፈጡና ወረራን ሲኮንኑ ዱቼው አፍንጫ ስር ሆነው እንዲህ ነበር ያሉት ያላንዳች ፍርሃት
ፒዮስ 11ኛ ነሐሴ 27. 1938- ሞሶሎኒን ሲጋፈጡ እንደ አምባሳደር ዘውዴ ረታ ትረካ ገጽ 298 wrote:“. . . ዛሬ በጣልያን መንግሥት የሚዘጋጀው ጦርነት ዓላማው ግዛትን ለማስፋፋት ከሆነ፤ በማያጠራጥር መንገድ ፍትሐዊ አይደለም። ይህም ከሆነ አሳዛኝነቱን ለመግለጽ ቃላት የማይገኝለት አስከፊ ነገር ነው . . .”
ታድያ በምን ሒሳብ ነው አንተና አንተን የመሰሉ ‘ምንጭ-አልባ ጋዜጠኞችና የቦለቲካ ተንታኞች’ በመገናኛ ብዙሃን ሰውን ለማደናገር ያልሆነ ታሪክ የምትናገሩት? ነዉር ኣይደለም እንዴ? የሮማው ሊቀጳጳስ ዱቼው አፍንጫ ስር ሆነው አቋማቸውን በሰለጠነ መንገድ የገለጹ መሆናቸው በታሪክ ቁልጭ ተደርጎ ተጽፎ እያለ አንተና መሰሎችህ ደግሞ ስማቸውን ለማጠልሸት ታሪክ የምትፈበርኩት ለምንድን ነው? ወይም ያልተጣራ ወሬ የምትበትኑት ለምንድን ነው? ይህ ስህተት መታረም አለበት አሊያም ምንጭ መጥቀስ ይገባሀል፡ ጐበዝ በህዝብ ገንዘብ በቆመ ሚዲያ ያልሆነ ነገር ማቀርሸት ትልቅ ስህተት ነው።
ጎበዝ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች እንደናንተ እንውረድ ካልን እኮ፡
ብለን መገገም እንችላለን።"ኢትዮጵያ ላለፉት 60 ዓመታት በኤርትራ ህዝብ ላይ ግፍና በደል የፈጸመችው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሪዎች በፓትሪያርኮቹ ቡራኬም ጭምር ነው፡ በመሆኑም ቤተክርስትያኒቱ ለኛ ለኤርትራዉያን ይቅርታ መጠየቅ ኣለባት"
ግራም ነፈሰ ቀኝ፡ ኢሳት ላይ የተናገርከው ጭብጠ-ቢስ ክስና ውንጀላ፡ ለወደፊቱ አንተም ሆንክ ሌሎች ጋዜጠኞች ታስቡበት ዘንድ ይህን ጽፈንልሃል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች። እንዲህ አይነቱን ያልተጣራ ወሬ ማናፈስ እንዲቀርም፡ “የኢሳት ቦርድም ሊያስብበት ይገባል”፤ ብለን ለመምከር ሲዳዳን ደግሞ፤ “ከኢሳት ተለዬን” የሚል እንጉርጉሯቹን ሰማን። በምን ምክንያት ሲባል “በገንዘብና ባስተዳደርና አደረጃጀት ድክመት ወዘተ” ሲባል ሰማን። እኛ መቼም “ውሾች የሚጣሉት ጅብን ካባረሩ በኋላ ነው” ብለን በተረትንባችሁ ነበር፡ ነገር ግን “የምስራቅ አፍሪካዉን ነቀርሳ፡ ወያኔን” በመደምሰስ ረገድ እንደ ሲሳይ የመሰሉ ጋዜጠኞች ያበረከቱትን ገንቢ ሚና ግምት ውስጥ በማስገባት፡ እንዲያ ማለቱን ኣልመረጥንም።
በሄዳችሁበት ሁሉ፡ ነጻነታችሁን ጠብቃችሁ፡ በእውነተኛ የጋዜጠኛነት ስሜት ትጓዙ ዘንድ ግን መልካሙን ሁሉ ተመኝተንላችኋል፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች።