Meleket wrote: ↑07 Mar 2019, 02:14
የሚከተለው ታሪክ “ዝኽርታት ሓመድ ድበ ናደው” ማለትም “የናደው ቀብር ሲዘከር” በሚል ርእስ “ሕድሪ’” የሚባለው አሳታሚ ድርጅት ካዘጋጀው መጸሐፍ የተጨለፈ ታሪክ ነው። ታሪኩ የኤርትራ ህዝብና የነጻነት ታጋይ ልጆቹ ታሪክ ነው። ታሪክ እንዳይሰረቅ ከትውልድ ወደ ትውልድም ይሸጋገር ዘንድ በመጸሐፉ መጀመሪያ ክፍል ያለውን ይዘት እንዳለ ኣቅርበነዋል። ይህን ብርቅ ታሪክ የፈጸሙትም ኤርትራዉያን እንደመሆናቸው መጠን፣ ለታሪክ ተመራማሪዎች “የኤርትራዉያንን እይታ” ይገነዘቡ ዘንድ ይህን ‘ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ አኹሪና ብርቕ ታሪክ እዚህ በተወላገደው አማርኛችን እዚህ አቅርበነዋል። መልካም ንባብ!!! በዚያን ግዜ ሕወሓት የኤርትራ ነጻነት ታጋዮችን በማንቋሸሽና በማጥላላት ዘመቻ ተጥዳ ፖለቲካዊ መጨማለቕ ታሳይ ነበር፣ ኤርትራዉያን ታጋዮች ደግሞ ጥበብ በተሞላበት ቅልጣፌን በተካነ ሁኔታ የጥቃት ፕላናቸውን እንዳገባደዱም፣ እንደ ደርጉ ሁሉ ሕወሓትም አራ፣ አፍራና ተደናብራ ነበር ምክንያቱም ይሆናል ብላ ያልጠበቀችው ተአምር ነበርና! ከድሉ ማግስት ግን ወያኔዎች ጅራታቸውን እየቆሎ “እንኳን ደስ አላችሁ! ጀግኖች ወዘተ” የሚል መግለጫ ለማውጣት ተሽቀዳድመው ነበር። ከዚህ ታሪክ እስከ ዛሬ ድረስም ሕወሓት የተማረች አትመስልም፣ በኤርትራ ህዝብና በትግሉ ታዝላ ዝንተዕለት ለመኖር ትሻለች፣ የኤርትራ ህዝብ ግን “በቃ” ብሏታል፣ አሁንም ያለምንም ማንገራገር ከኤርትራ ልዑላዊ ግዛት ብትወጣና ለህግ የበላይነት ብትገዛ አይበጃትም ትላላችሁ?
የናደው እዝ ቀብር ሲዘከር
መግቢያ
“. . . ህዝባዊ ግንባር፡ የናቅፋ ግንባር ድሉን የሚመዝነው፡ በረዢሙ የኤርትራ ህዝብ ትጥቅ ትግል ተጋድሎና በተለይም ባለፉት አስር ኣመታት ውስጥ በታየው ወታደራዊ ክስተቶች ኣዃያ ነው። የሰነዘርነው ጥቃት ኃያል፣ ቅጽበታዊና ትልቅ ጠባሳ ጠላት ላይ እንዳሳረፈ ኣይካድም። ኢትዮጵያዉያን ኤርትራን በኃይል ከያዙበት ግዜ ወዲህ፡ ለመጀመሪያ ግዜ በአእምሯቸው ውስጥ፡ “ለመሆኑ ኢትዮጵያ ኤርትራን ማስተዳደሯን (‘መግዛቷን’) ትቀጥላለች ወይስ ኣትቀጥልም?” የሚል ጥያቄ አፋጣኝ ምላሽን የሚሻና ፋታ የማይሰጥ ብርቱ ጉዳይ እንዲሆን ያስደረገ ወታደራዊ ጥቃትን ፈጽመን ነው ድልን የተጎናጸፍነው። . . . “ታጋይ ኢሳይያስ አፈወርቅ የህ.ግ.ሓ.ኤ. ዋና ጸሃፊ፡ በሳግም መጽሔት ቁ.14)
በመጋቢት ወር 1988 ናቅፋ ግንባር ላይ መሽጎ የነበረውንና “ናደው እዝ” ተብሎ የሚጠራዉን ግዙፍ የኢትዮጵያ ሰራዊት ክፍል፡ በፍጹም ከበባ ውስጥ በማስገባት የተካሄደ ደምሳሽ ቀለበታዊ ጥቃት፡ በወርቃዊ ድሎች ባሸበረቀውና በተመላው የኤርትራ ህዝብ የተጋድሎ ታሪክ ውስጥ እንደ የአዲስ ምዕራፍ በር ከፋች ሊጠቀስ የሚችል፣ ትልቅ ስትራቴጂያዊ ጥቅም የነበረው ፍጻሜ ነው።
ናደው እዝን የደመሰሰው ወታደራዊ ድላችን በነጻነት ትግላችን ውስጥ ጎልቶ የሚታይ ይሁን እንጂ፡ የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ሰራዊት፡ ወደዚህ ግዙፍ ስትራቴጂያዊ የማጥቃት እርምጃ ለመሸጋገር፡ አስቀድሞ ያሳለፋቸው ፋታ የማይሰጡ ተደጋጋሚ ውጊያዎች፡ እጅግ ረዢም ትዕግስትና ብርቱ ጽናት የሚጠይቁ ነበሩ። ስለሆነም የናደው እዝ መደምሰስ፡ አስቀድሞ ለአስር አመታት በቋሚ ሰንሰለታዊ ምሽጎች ናቕፋ ሰሜናዊ ምስራቕ ሳሕልና ባርካ ላይ የተካሄዱት ብርቱ ውጊያዎች ፍሬ ወይ ምርት ነው። በተጨማሪም በጠላት ወረዳ ውስጥ በደፈጣ ውጊያ በፈንጅ ቀበራና በመሳሰሉት የተቀነባበሩ እረፍት የማይሰጡ ውጊያዎች ታግዞ፡ የኢትዮጵያ ሰራዊትና አጋሮቹ መቆሚያና መቀመጫ እስኪያጡ ድረስ የተካሄዱ ተደጋጋሚ ውጊያዎች ፍሬ ነው።
አጭር ቅድመ ታሪክ
በ1977-1978 አምስት ተከበው ከቀሩ ከተሞች በስተቀር፡ መላው ኤርትራ በኤርትራዉያን ታጋዮች ቁጥጥር ስር ሆኖ ነበር። የደርግ ስርዓት ኤርትራዉያን ታጋዮች በሚሰነዝሩበት ጥቃት ብቻ ሳይሆን፡ ከሶማሊያ ጋር ያካሂደው በነበረ ውጊያ ወተሃደራዊ ኣቅሙ እጅግ ተዳክሞ ነበር። የኤርትራ ህዝብ ከዛሬ ነገ ነጻነቴን እጎናጸፋለው ይል በነበረበት ወቅት ግን፡ በወታደራዊ የኃይል አሰላለፍ ሚዛን የሚያዛባ መሰረታዊ ለውጥ ያስከተለ የልዕለኃያሏ ሃገር የሶብየት ህብረት እጅ ቀጠናችን ውስጥ ገባ። ደርግም የሶቭየት ህብረትን ግዙፍ ድጋፍ ኣግኝቶ፣ ባጭር ጊዜ 300,000 ዘመናዊ መሳርያ የታጠቀ፡ በጥቁር አፍሪካ ውስጥ እጅግ ብርቱውን ወታደራዊ ኃይል አንጾ፣ ከመቅጽበት ከተከላካይነት ወደ አጥቂነት ተሸጋገረ።
በ1978 አጋማሽ፡ ደርግ በሶማሊያ ሃይሎች ላይ እጅግ ግዙፍ ጥቃት ከፈተ። በሳምንት ውስጥም የሶማሊያን ጦርነት በድል አገባዶ፡ “የምስራቅ ድል በሰሜን ይደገማል!” በሚል መፈክር ታጅቦ፡ ወደ ሰሜን በማቅናት የኤርትራን ህዝብ ትግል “ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ” ብሎ በሰየመው ጥቃት ለመደምሰስ እጅግ ግዙፍ ወረራን ጀመረ። ጦርነቱ “በጉንዳንና በዝሆን” መካከል እንደሚደረግ ኣይነት ግጥሚያ ነበር። ስለሆነም ህዝባዊ ግንባር አቅሙንና ብቃቱን ገምግሞ ይህን እጅግ ግዙፍ የሆነ ወራሪ ሰራዊት በተራዘመ ውጊያ ለማዳከም፡ ነጻ አውጥቷቸው ከነበሩ ቦታዎች ደረጃ በደረጃ እያፈገፈገ፡ የጠላትን ኃይል በአመቸው ቦታና ግዜ እየገጠመ፡ ስትራቴጂያዊ ማፈግፈግ ለማድረግ ወሰነ። በዚህ መሰረትም፡
በመጀመርያው ወረራ፡ ህ.ግ. ከደቡባዊና ምስራቃዊ ኤርትራ ሲያፈገፍግ
በሁለተኛው ወረራ ከሰሜናዊ ግንባር አፈገፈገ
በሶስተኛው ወረራም፡ ከከረንና አፍዓበት አካባቢ በማፈግፈግ ቋሚ ምሽጉ ይሆን ዘንድ ወደ መረጠው የናቅፋ ተራራዎችና ሰሜናዊ ምስራቅ ሳሕል አቀና።
(የህዝባዊ ሰራዊት ስትራቴጅ ቀድሞም ቢሆን እያፈገፈግክ በሚመችህ ቦታ ጠላትን ድባቅ መምታት መሆኑ የሚያውቅ ነው ሚያውቀው።)
የህዝባዊ ግንባር ሰራዊት በተመቸው ስፍራ ሁሉ ብርቱ ተቃውሞ እያደረገ እያጓራ በመጣበት ጠላት ላይ ከባድ ኪሳራን እያከናነበ በየካቲት 1979 ናቅፋ አካባቢ ደረሰ። በናቅፋ መግቢያ በርም በግራና ቀኝ “እምባ ደንደን” በተባለ ተራራ ላይ መሸገ። ይህ ስፍራ የመጨረሻ የመከላከያ መስመር ይሆን ዘንድ አስቀድሞ በጥናት የመረጠው ቦታ ነበር። ሆኖም የናቅፋ ግንባር ልክ በዚህ ሁኔታና ግዜ ነበር የተመሰረተው። መጀመሪያ ላይ የግንባሩ ስፋት እጅግ ውሱንና ጠባብ ነበር። የጠላት ሰራዊት በተወሰነ ቦታ ጥሶ ወይ በስቶ ለማለፍ የሚያደርጋቸው ተከታታይና ተደጋጋሚ ጥቃቶች ውጤት አልባ ሲሆኑበት ግዜ፡ በቀጣይ ወረራዎቹ ማለትም (በ4ኛ 5ኛና 6ኛ) ወረራዎቹ ወቅት፡ ሆን ብሎ የወገንን ኃይል ሚዛን ለማሳሳትና ለማራራቅ፡ በግንባሩ ሁለት ክንፎች የሰራዊቱን ይዞታ እየለጠጠ ሰፊ ቦታ ለመሸፈን ብርቱ ጥረት አካሄደ። ከናቅፋ ግንባር በተጨማሪም የሰሜናዊ ምስራቅ ሳህል ግንባርና የሓልሓል ግንባርም በተመሳሳይ መልኩ ይዞታቸው እየሰፋ በመሄዱ በመጨረሻ ሶስቱም ግንባሮች እርስ በርስ ተሳስረው ነበር ለማለት የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተደረሰ። በዚህም ለአስር ዓመታት ያህል ያለማቋረጥ በተደረገ ብርቱ የምከታ ውጊያ፡ ሁለቱም ተጻራሪ ወገኖች ምሽጋቸውን የማደላደል ስራ በቀጣይነት ይተገብሩ ስለነበር፡ በሁለቱም ወገኖች መካከል በፈንጅ የታጠረ የ667 ኪሎሜትር ርዝመት ያለው ብርቱ ምሽግ ተፈጥሮ ነበር።
(የኤርትራ ህዝብ የሕወሓትን አካሄድና የድንበር ብይንን አፈታት በተመለከተም ተመሳሳይ ስትራቴጂ የተከተለ ይመስላል፡ ከብርቱ የእልህ ምከታ በኋላ ድንበሩን የሚያስከብርበትና ልዑላዊ ግዛቱን በጠቅላላ ያለአንዳች መሸራረፍ የሚያስተዳድርበት መድረክ ላይ ከትናንት ይልቅ ዛሬ ይበልጥ ተቃርቧል ለማለት ይቻላል።)
ከ1978 አጋማሽ እስከ 1988 ለአስር ዓመታት የቀጠለ ብርቱ የመረባረብ ውጊያ ከተካሄደ በኋላ፡ ያ ልዕለ ኃያል በሆነችው የሶቭየት ህብረት እጅግ ግዙፍ በሆነ ወታደራዊ፣ ገንዘባዊና ቴክኒካዊ ምክር እየተለገሰለት፡ የኤርትራን ህዝብ ትግል ላንዴና ለመጨረሻ ግዜ ለመደምሰስ የተነሳው ወራሪ የኢትዮጵይ ሰራዊት፡ ከባድ ሰብአዊና ቁሳዊ ጉዳቱን ተሸክሞ፡ ከማጥቃት ወደ መከላከል ስትራቴጂውን እንዲቀይር ተገዷል። ውጊያም ያለ እረፍት በመቀጠሉና ስለተራዘመበትም፡ የኢትዮጵያ ሰራዊት መጨረሻ ላይ ተስፋ እየቆረጠ፣ የመዋጋት ወኔው እየጠፋበት ሞራሉ እየላሸቀ ሂዷል።
እጅግ ረቂቅና ውስብስብ የስለላ ጥናት በማድረግ፡ የጠላት ሁኔታ፡ ከዕለት ወደ ዕለት በትክክል ይገመግም የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ በ1987 የጠላትን ቀልብ ከቅድመ ግንባር ወደ መሃል ወይም የጠላት ይዞታ ውስጥ የሳበ፡ ተከታታይ የደፈጣና አጥቅቶ የመሰወር ተልዕኾዎችን ሆን ብሎ ተያያዘው። በግንባር ላይ የነበረውን የጠላት ሁኔታ ለመፈተሽም በታሕሳስ ወር 1987 በናቅፋ ግንባር መካከለኛ መስመር ላይ፡ በተወሰኑ አካባቢዎች መጠኑ አንስተኛ የሆነን ጥቃት በማካሄድ፡ ጠላትን በመግፋት ናደው እዝን ለመደምሰስ ለቀጣዩ ብርቱ የማጥቃት እርምጃ መረማመጃ የሚሆነውን ስትራቴጂያዊ ቦታዎችን በቁጥጥሩ ስር አዋለ።
በነዚህ ብርቱ ጥቃቶች የደነገጠው የደርግ ስርዓት መሪ መንግስቱ ሃይለማርያምም፡ በየካቲት 1988 ከአዲስ አበባ ወደ አስመራ በመምጣት፡ መላ ኤርትራ ውስጥ የነበረውን የሁለተኛ አብዮታዊ ሰራዊት ብሎ የሚጠራዉን ሰራዊት አመራሮች ጋር ስብሰባ ካካሄደ በኋላ፡ ናደው እዝ እንዲዳከም ምክንያት የሆኑት እንዲሁም በወርሓ ታሕሳስ ግንባር ናቅፋ ላይ ላጋጠመው ሽንፈት ዋንኛ ተጠያቂ ነው ያለውን፣ የግንባሩን ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ መሆኑን በመግለጽ፡ ከሰራዊት ፊት እንዲረሸን አደረገ። በደጋማው የኤርትራ ክፍል በደፈጣ ውጊያ በደርግ ሰራዊት ላይ ለደረሰው ኪሳራም የመክት እዝን ሃላፊ ብሪጋዴር ጀነራል ከበደ ጋሼን ተጠያቂ መሆኑን ኋላፊነት በማሸከም፡ ከሰራዊቱ ፊት ማእረጉን በመግፈፍ ያለ ጥሮታ እንዲባረር አደረገ። የሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት ማለትም የ‘ሁ.አ.ሰ.’ አዛዥ የነበሩት ሜጀር ረጋሳ ጂማንና ምክትሉን ሸዋረጋ ቢሆነኝን ከሌሎች ከ20 በላይ የሚሆኑ ከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችንም፡ ከኤርትራ ወደ የኢትዮጵያ ሌላ ክፍል ቀየራቸው።
በዚያን ወቅት መንግስቱ ሃይለማርያም የወሰደው የተስፋ መቁረጥ እርምጃ የሰራዊቱን ድክመት እንደገና አባብሶት ነበር። የደርግ ስርዓት፡ ከዚህ ሌላ፡ በኤርትራ ደጋማ ክፍሎች በተከታታይ ይደርስበት የነበረውን ብርቱ የደፈጣ ውጊያ ሊቋቋም ባለመቻሉ፡ ይህን ውስጣዊ መስመሩን ወይም ውስጣዊ ይዞታውን ለማደላደል ከዋና የግንባር ክፍሎች ቀስ በቀስ ሃይሉን እያመጣ በውስጣዊ ይዞታው እንዲያሰፍር ይገደድ ነበር።
ይህን ወታደራዊ ሁኔታ በትኩረት ይከታተል የነበረው የህዝባዊ ግንባር አመራርም፡ ‘ናደው እዝ’ን ለመደምሰስ አስቀድሞ ያካሂደው የነበረውን ጥናትና ይመረምረው የነበረን የማጥቃት ውጥን ተግባር ላይ የሚያውልበት የዜሮ ሰዓት እንደተቃረበ ገመገመ። የናደው እዝን የመደምሰስ ተልእኮ ከመከናወኑ በፊት ማለትም ከየካቲት 25-28 1988 የተካሄደው ሁለተኛው የህዝባዊ ግንባር ሓርነት ኤርትራ ማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባም ይህን የሚያመላክት አንድምታ ነበረው።
“ማእከላዊው ኮሚቴ . . . . ወታደራዊ ጥቃቶችን ይበልጡኑ ማበረታታትና ይዞታውንም ማስፋት የሚያስችል፡ ጠላትም ዓቅሙን እንዲያሻሽል ፋታ የማይሰጥ ወታደራዊ የስራ መደብንና ፕላንን አዘጋጅቷል።” ይላል ያኔ የወጣው የአቋም መግለጫ።
ይህን ዓላማ ለማሳካት የተመደበው የመጀመሪያ ውጥን፡ ናደው እዝን በመክበብ መደምሰስ ነበር። የህዝባዊ ግንባር አመራር ክፍል ይህን ዓይነት ትልቅና ደፋር እርምጃን ለመውሰድ የወሰነው፡ የጠላትን ኃያልና ደካማ ጎን በትኩረት የገመገመ ረቂቅ የስለላ መረጃዎችን ካጠናና ከመረመረ በኋላ፡ እንዲሁም በደጋማው የጠላት ወረዳ ውስጥ ባካሄደው ተደጋጋሚ የደፈጣ ውጊያ ጠላትን ለማታለልና የጠላትን የትኩረት አቅጣጫ ለማዛባት በመቻሉ ነው።
ከዚህ ትልቅ ወታደራዊ ኦፕሬሽን ሁለት ወር በፊት፡ የናደው እዝ ኣዛዥ ብሪጋዴር ጀነራል ታሪኩ ያይኔ፡ ለሁለተኛው አብዮታዊ ሰራዊት (ሁ.አ.ሰ.) ኣዛዥ ለጀነራል ረጋሳ ጂማ በላከው ደብዳቤ፡ ህዝባዊ ግንባር በናቅፋ ግንባር ላይ ብርቱ የስለላ ጥናት በማካሄድ ላይ መሆኑን ይህም ብርቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጀ መሆኑን የሚያመላክት እንደሆነና፡ ‘መክት እዝ’ን ለማገዝ ከግንባር ወደ ደጋማው ኤርትራ ውስጣዊ ቀጠናዎች የተሰማሩት ወይም እንዲሄዱ የተደረጉት 15ኛና 22ኛ ክፍለጦሮች ባስቸኳይ እንዲመለሱለት ጥያቄውን አቅርቦ ነበር። ይሁን እንጂ የሁ.አ.ሰ. አዛዥ የሰጠው መልስ፡ “ባለን መረጃና ግምገማ መሰረት፡ በቅርቡ ሻዕብያ ብርቱና ሰፊ ጥቃት ይፈጽማል ብለን አናምንም። ስለሆነም እነዚያ ሁለት ክፍለጦሮች ለግዜው እዚሁ በደጋማው ክፍል ውስጥ ያለንን ስጋት ለማስወገድ እዚሁ በውስጥ ቀጠና እየሰሩ ይቆያሉ። ለማንኛውም ግን ብርቱ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።” የሚል ነበር።
የሁ.አ.ሰ. አዛዦች “ሻዕብያ በናቅፋ ግንባር የመከላከያ ምሽጉን በማደላደል ላይ እንጂ የማጥቃት እርምጃ ለመውሰድ የሚያስችል አንዳችም ፍንጭ አይታይበትም” የሚል ድምዳሜ ላይ እንዲደርሱ ያደናገራችው፡ አንዴም ህዝባዊ ግንባር ጠላትን ለማደናገርና ለማታለል፡ ከስድስት በላይ ብርጌዶችን በጠላት የውስጥ ቀጠና ማለትም ብደጋው ክፍል አሰማርቶ የደፈጣ ውጊያን በቀጣይ ይፈጽም ስለነበረ አሊያም በታሕሳስ 1987 በናቅፋ ግንባር በተካሄደው መጠኑ አንስተኛ በሆነው ጥቃት የተቆጣጠራችውን አዳዲስ ስፍራዎች፡ ምሽግ በመቆፈር ይዞታውን ማጠናከር ላይ በቀጣይነት ሲንቀሳቀስ ይታይ ስለነበር ነው።
“ደርግን’ በኣፍዓበት ያሳረረ፡ ሶቭየትሕብረትን ያሳፈረ፡ ሕወሓትን ያደናበረ - ‘ናደው እዝ’ ላይ ያረፈው በትር ታሪኽ ይቀጥላል!!!