Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Ethiopia has returned to the 1980s Kebele coupon ration economy

Post by sarcasm » 21 Mar 2022, 07:33

ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች ከ አንድ ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሊትር ዘይት በላይ መሠራጨቱ ተገለፀ
******************
(ኢ ፕ ድ) Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/

ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ከአንድ ሚሊዮን 831 ሺ 93 ሊትር በላይ ዘይት በኅብረት ሥራ ማህበራት አማካኝነት መሠራጨቱን የአዲስ አበባ ከተማ ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ አስታወቀ።

በአዲስ አበባ ከተማ ኅብረት ሥራ ኤጀንሲ የግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ ደብሪቱ ለዓለም ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለፁት፣ በድምሩ 1 ሚሊዮን 831 ሺ 93 ሊትር ዘይት ለነዋሪዎቹ ተሠራጭቷል። ከተሠራጨው ዘይት ውስጥ በመደበኛ ግዢ ለሸማቾች የቀረበው 1 423 283 ሊትር ዘይት ነው።
በኅብረተሰቡ ጥቆማ በሕገ ወጥ መንገድ ከተያዙ ነጋዴዎች ለኅብረት ሥራ ማኅበራት እንዲያከፋፍሉት የተሰጠ 162 989 ሊትር ዘይት በተጨማሪነት ተከፋፍሏል።
በመዲናዋ ከሚገኙት 148 መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበራት መካከል 133 ያህሉ ዘይት እያሠራጩ ይገኛሉ። ሆኖም በዘይት ሥርጭት ረገድ መንግሥት ከፍተኛ ወጪ አውጥቶ የሚገዛው የድጎማ ዘይት በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶ በዝቅተኛ ኑሮ ውስጥ ላሉና ኩፖን ላላቸው ሰዎች ነው እየተከፋፈለ የሚገኘው ተብሏል። ይህ በራሱ የገበያውን ሁኔታ የሚያረጋጋ መሆኑ ተገልጧል።

የዘይት አቅርቦት እጥረትን ለመፍታት አገር በቀሎቹ ሁለት ፋብሪካዎች በከፍተኛ ደረጃ እያመረቱ እንደሆነ ተገልጧል። ከሁለቱ ዘይት አምራች ፋብሪካዎች ጋርም የአቅርቦት ውል ተፈፅሟል።
በዚህም መሠረት የፌቤላ ዘይት በተለያየ መጠን ምርቱን በማቅረብ ላይ ይገኛል። የወርቁ አይተነው የዘይት ፋብሪካም በከፍተኛ ደረጃ እያመረተ ነው። በግብዓት እጥረት ምክንያት ምርት ቀንሰው የነበረ ሲሆን አሁን ወደነበሩበት ሁኔታ መመለሳቸው ተገልጧል። ይህም የገበያውን ሁኔታ ያረጋጋል፤ በመጪዎቹ ሳምንታትም የተሻለ አቅርቦት ይኖራል ተብሏል። ከዚህም በተጨማሪ ከውጭ የሚያስመጡ
አስመጪዎችን መንግሥት ከፍተኛ ድጋፍ እያደረገላቸው የዘይት ምርት እያስገቡ ያሉበት ሁኔታ አለ።
ይህም በተሻለ መልኩ ገበያውን እንደሚያረጋጋው ይጠበቃል። በአሁኑ ወቅት ሦስት ሊትር ብር 285፣ ባለ 5 ሊትሩ ብር 412.15 እንዲሁም ባለ 20 ሊትሩ 1588 ብር እየተሸጠ ነው ተብሏል።
ለገበያ የዋጋ ሁኔታን ሸማቹን እንዲያማክል ከአንድ ሊትር ጀምሮ እንዲመረት ከፋብሪካዎች ጋር ስምምነት ላይ ተደርሷል።
የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት መንግሥት በፍተኛ ወጪ ወደ አገር ውስጥ እንዲገቡ ያደረገው ዘይት ለኅብረተሰቡ በምን ዓይነት መልኩ እየተሰራጨ ነው የሚለውን በከተማዋ ተዘዋውሮ መመልከት ሞክሯል።
በአራዳ ክፍለ ከተማ የመጀመሪያ ቅኝቱን አድርጓል። በወረዳው ሸማቾች ውሰጥ ዘይት ሲሸምቱ ያገኘናቸው ወይዘሮ እቴነሽ መኮንን እንደገለፁት፤ የወረዳው የሸማቾች ማህበር መንግሥት ያሰራጨውን ዘይት በፍትሀዊ መንገድ ለኅብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ ላይ ነው።
በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ሐማቾች ማህበር ተጠቃሚዋ ወይዘሮ አስካለ ታዬ በበኩላቸው በወረዳው ውስጥ ያለውን ግልጋሎት ያደነቁ ሲሆን ወረዳው የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች በፍትሃዊ መንገድ በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
እንደ ወይዘሮ አስካለ ገለፃ፤ ወረዳው መንግሥት ያሰራጨውን ዘይት በፍትሀዊ መንገድ ከማከፋፈሉም በተጨማሪ አሠራሩን ግልጽና ተጠያቂነት የበዛበት በማድረግ ረገድ ለሌሎችም ስፍራዎች ትምህርት መሆን የሚችል እንደሆነ ገልጸዋል።
በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ 10 የሸማቾች ተጠቃሚ የሆነችው ወጣት ምስክር በበኩሏ በወረዳው የዘይት እጥረት እንዳለ ትናገራለች።
የዘይት እጥረቱ ማህበረሰቡን እያጉላላው እንደሚገኝ ገልፃለች። ማህበረሰቡ በዘይት አለመኖር ምክንያት የደረሰበት መጉላላት ከግምት ሊገባ እንደሚገባው የጠቆመችው ወጣት ምስክር መንግሥት ስርጭቱን በመቆጣጠር ለኅብረተሰቡ በተገቢ ሁኔታ ሊያዳርስ እንደሚገባውም አስተያየቷን ሰጥታለች።
(ፎቶ ፋይል)
በውብሸት ሰንደቁ
Please wait, video is loading...

sesame
Member+
Posts: 8583
Joined: 28 Feb 2013, 17:55

Re: Ethiopia has returned to the 1980s Kebele coupon ration economy

Post by sesame » 21 Mar 2022, 08:49

Sarco,

The irony is that Tigray has done the same. All throughout the 1980s hundreds of thousands of Agames starved to death. And that specter is now hanging over Agames. Have these morons taken into account that within a few months their starving people would not be a able to till their fields. It is doubtful if an exhausted world will sing "we are the world" for Agames now!



Post Reply