Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15492
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ምክር ለትግራይ ህዝብ < እርባና-ቢስ የሆነውን የወያኔ የሁመራ-ወልቃይት እና ራያ ይገባኛል ጥያቄ አርግፋችሁ መተው ብቻ የዘላቂ ሰላም ተጠቃሚ ያደርጋችኋል። ከዚህ ውጭ መንገድ የለም>

Post by Abere » 12 Mar 2022, 16:51

ምክር ለትግራይ ህዝብ < እርባና-ቢስ የሆነውን የወያኔ የሁመራ-ወልቃይት እና ራያ ይገባኛል ጥያቄ አርግፋችሁ መተው ብቻ የዘላቂ ሰላም ተጠቃሚ ያደርጋችኋል። ከዚህ ውጭ መንገድ የለም>የትግራይ ህዝብ ማንኛም ወያኔ እና ኦነግ -ብልጽግና የሚያደርጉት ድርድር እና ውል በቋሚነት የሚጎዳው እንጅ የሚጠቅመው አይደለም። የትግራይ ህዝብ በኦነግ አመራር እጠቀማለሁ ብሎ የሚያስብ ከሆነ እጅግ ድንዝዝ ሁኗል ማለት ነው። ወያኔዎች ስለተጨነቁ እና በህይወት መቆየት ስለሚፈልጉ እጅ ነስተው ከኦነግ ጋር ሊደራደሩ ይችላሉ ግን የትግራይ ህዝብ በወደፊቷ የኦነግ ኢትዮጵያ ተረግጦ እና አንሶ እንደሚኖር ግልጽ ነው። የትግራይ ህዝብ አገር ሙሉ ኢትዮጵያ እንጅ ቁራጭ ጎጥ አይደለም። ለትግራይ ህዝብ ክልል አያስፈልገውም -ለሌሎች ኢትዮጵያኖችም ክልል የሚባል አያስፈልግም። የትግራይ ህዝብ ፀረ-ክልል እና ፀረ-የጎሳ ፓለቲካ የለውጥ ሃይል መሆን ይገባዋል - በጋጠ-ወጥ ሰካራም ኦነግ-ኦሮሙማ አገሩን እንድ ታወክ ማድረግ እና ለድንዝዝ ወያኔ መታዘዝ የለበትም። ድንዝዝ እና ደናቁርት መለስ ዜናዊ የትግራይን ህዝብ የሚጠቅም ምሰሎ የትግራይን ህዝብ ክብር እና ዘላቂ ኢትዮጵያዊ ጥቅም የሚያስከብረውን ማንነቱን በቅራቅንቦ የጎሳ ክልል ተክቶ ዛሬ የትግራይ ህዝብ እንድሰቃይ እና ዝቅ እንድል አድርጓል። አሁንም ቅሪት ወያኔዎች ያንኑ የትግራይን ህዝብ በዚያው ውርደት እንድኖር የሚፈልጉ ናቸው። የትግራይ ህዝብ እንደ አማራ ህዝብ ለኢትዮጵያ ልዑላዊነት ለህዝብ እና አገር አንድነት መታገል አለበት።