Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Naga Tuma
Member+
Posts: 7432
Joined: 24 Apr 2007, 00:27

ቋንቋ እና ባህል

Post by Naga Tuma » 09 Mar 2022, 11:59

ቋንቋ ባህልን ይገልጻል፣ ባህል በቋንቋ ይንጸባረቃል ማለት ይቻላል?

የዳበረ ባህል ዉስጥ ቃላት መቼ መጠቀም እና ኣለመጠቀም እንዳለብን መኖሩን ኣንድ ጊዜ ከባህል ኣዋቂ ሰምቻለሁ። እኔ ስለዚህ ባህል ጥልቅ ዕዉቀት የለኝም።

ኣንድ የማስታዉሰዉ ክዉ ኣለ ወይም ክዉ ኣለች የሚል አባባል ነዉ። ይህን አባባል ሳይገባኝ ተጠቅሜዉ ይሆናል። መደናገጥን የሚገልጽ መስሎኝ ነዉ።

በባህል ዉስጥ አባባሉ ምንን ይገልጻል? ንዴት ወይም ድንጋጤ መንስኤዉ ሊሆን ይችላል? ሰዉነት ምን ላይ ሲደርስ ነዉ ክዉ ኣለ ወይም ኣለች ማለት የሚቻለዉ?

ይህን ባህላዊ አገላልጽ የህክምና ባለሙያዎችስ እንዴት ያዩታል? መንገድ የማይቀይር ክስተት እንዲገባኝ ብቻ ነዉ። እንኳን ባህል የተጻፈዉንም መልሼ መላልሼ ሳነብ ነዉ በደንብ የሚገባኝ።