ጥልቅ ትንታኔ፡ ከአማራ ክልል የሚመጡ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት በሺዎች የሚቆጠሩ የምዕራብ ኦሮሚያ ነዋሪዎችን አፈናቀሉ - አዲስ ስታንዳርድ
Posted: 04 Mar 2022, 20:35
በምስራቅ እና በሆሮጉድሩ ወለጋ ዞኖች እየተካሄደ ያለው የእርስ በእርስ ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን እያፈናቀለ ይገኛል፡፡ ለአዲስ እስታንዳርድ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሁለቱም ዞኖች ሲደርሳት ቆይተዋል፡፡ በግጭቱ ምክንያት የተፈናቀሉ የምስራቅ ወለጋ ነዋሪዎች በነሱ አገላላፅ ‘ አማርኛ ተናጋሪ’ የታጠቁ ሀይሎች ጥቃት ምክንያት ከአካባቢያቸው ሲፈናቀሉ የአካባቢው አስተዳደር በበኩሉ የአካባቢው ፀጥታ አንዲሁም ጥቃቱን የፈፀሙ ሃይሎች በቦታው አለመኖራቸው ሳይረጋጋገጥ ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ እያስገደዷቸው መሆኑ ቅሬታ ፈጥሮባቸዋል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በሆሮ ጉዱሩ ዞን የምትገኘው አቤ ዶንጊሮ ወረዳ ነዋሪዎች ‘በፅንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች’ አማካኝነት ቅዳሜ የካቲት 5. 2014 ዓ.ም በደረሰው ጥቃት ሴቶች እና ህፃናትን ጨምሮ 30 ሰዎች መገደላቸውን ለአዲስ አስታንዳርድ በስልክ ገልፀዋል፡፡
ሆሮ ጉድሩ ዞን
እንደ ነዋሪዎች ገለፃ የአማራ ታጣቂ ሀይሎች ጥቃቱን ያደረሱት በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ውስጥ በምትገኘው ቦቶራ ቦራ ቀበሌ ሲሆን ቀኑም የካቲት 6፤ 2014 ነበር፡፡ በጥቃቱም 29 ሰዎች የተገደሉ ሲሆን ዝርፊያን ጨምሮ ከ 64 በላይ ቤቶችን በእሳት ወድመው ነበር፡፡ ስሙ እንደይገለፅ የፈለገ የአቤ ደንጎሮ ነዋሪ ለአዲስ እስታንዳርድ በስልክ “የአማራ ሚሊሻዎች ከአቤ ዶንጎሮ እና ጀርጋዳ ጃርቴ ወረዳ መጥተው ያለምንም ምህረት ከ20 በላይ ሰዎችን ህፃናትን እና ሴቶችን ጨምሮ ገድለው ሄደዋል” በሏል።
እንደ እማኙ ገለጻ ከሆነ የታጣቂዎቹ ሁለት አባላት በመጥፋቸው እነሱን ለመፈለግ ታጣዊዎቹ መሰባሰብ እንደጀመሩ ተናግሮ “እነሱ በለሊት ሲመጡ ተኝተን ነበር ወዲያው ተኩስ ከፍተው ያገኙትን ሁሉ መግደል ጀመሩ። ቤቶች ውስጥ ሰው እያለ እላያቸው ላይ እሳት መለኮስ ጀመሩ፡፡ የቻልነው ሮጠን አመለጥን ነገር ግን ያላመለጡት እዛው በእሳት ተቃጥለው ሞቱ” በማለት አብራርቷል፡፡
ምስክሩ ከሰጡት ገለፃ እሬሳቸው በአካባቢው ከተገኙ ሰዎች በተጨማሪ ብዙ ሰዎች እሳከሁን የት እንደገቡ እንደማይታወቅ እና ቁጥራቸው የበዛ ወጣት ሴቶች በጉልበት ተጠልፈው እንደተወሰዱ ለማወቅ ተችሏል።
Continue reading https://amharic.addisstandard.com/%e1%8 ... %e1%8c%a3/