በሺዎች የሚቆጠሩ የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ደሞዝ ከተከፈላቸው ከዓመት በላይ እንዳለፋቸው ለቢቢሲ ተናገሩ።
Posted: 04 Mar 2022, 17:53
መምህራኑ ምንም እንኳ የፌደራል መንግሥቱ ቅጥረኛ ቢሆኑም "ደመወዝ ስላልተላከልን የከፋ ችግር ውስጥ እንገኛለን" ብለዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር በበኩሉ ከትግራይ ክልል የወጡ መምህራንን ወደ ሌላ ተቋማት ማሸጋገሩን እና በክልሉ ላሉት ግን ምንም ማድረግ እንደማይችል ገልጿል።
በዩኒቨርሲቲው የህክምና ትምህርት ቤት ባልደረባ የሆኑት አንድ ሠራተኛው፤ የሚበሉት ሳይኖራቸው በባዶ ሆዳቸው ወደ ሥራ መጥተው ሕክምና እያደረጉ እራሳቸውን ስተው የሚወድቁ ሐኪሞች ስለመኖራቸው ያስረዳሉ።
በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ የመቀለ ዩኒቨርሲቲ 7ሺህ ሠራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው እና እጅግ አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ይህ የሕክምና ትምህርት ቤት ባልደረባ ይገልጻሉ።
የትምህር ሚኒስቴር ሚኒሰትር ዲኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) በትግራይ ላሉ ሠራተኞች ምንም ማድረግ አንችልም ይላሉ።
Continue reading https://www.bbc.com/amharic/news-60616482