Page 1 of 1
የኢትዮጵያ ቅርጸ መንግስት ፕሬዚዳንታዊ ሊሆን ነው
Posted: 02 Mar 2022, 17:51
by Horus
ይህም ማለት በመጀመሪያ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት በሁሉም ክልል ውስጥ በግለሰቦች አንድ ሰው አንድ ድምጽ ይመረጣል ማለት ነው ። ሁለተኛ ከዚህ ጋር ተያይዞ የሕግ መወሰኛው እና የፍትህ ቅርንጫፉ አመሰራረት መለወጥ ይኖርበታል ማለት ነው ። በተለይ የሕግ መወሰኛው ምክር ቤት ተወካዮችም አመራረጥ መለወጥ ይኖርበታል ማለት ነው። በሌላ አባባል አሁን ያሉት ክልልሎች ሳይፈርሱ እና የጎሳ ክልል መንግስታት ስልጣን ሳይለወጥ በዴሞክራሳዊ ምርጫ የሚቋቋም ምክር ቤት ሊኖር አይችልም። ይህም ማለት በግድ የብሄራዊ ሕገ መንግስታዊ አገር አቀፍ ሙግትና የስምምነት ኮንቨርሴሽን መደረግ ይኖርበታል ማለት ነው። እንግዲህ ይህ እውነት ከሆነ መላ ክስተቱና ሂደቱን የምናየው ይሆናል!
እኔ ከወዲሁ የየልዩ ፕሮፌሰር አኪል አማር '
እኛ ያደረጉን ቃላት' የአሜሪካ ሕገ መንግስታዊ ኮንቨርሴሽን የሚለው መጽሃፉን እያገላበጥኩ ነው ። (Akhil R. Amar, The Words That Made Us: America's constitutional conversation, 1760 - 1840. (2021) ድንቅ የሆነ የ80 አመት 800 ገጽ ጥናት ነው! ወደ ፊት ለምናደርገው የሕገ መንግስት ሙግት ይጠቅማችኋል!
Re: የኢትዮጵያ ቅርጸ መንግስት ፕሬዚዳንታዊ ሊሆን ነው
Posted: 03 Mar 2022, 02:36
by Horus
የኢትዮጵያ ቅርጸ መንግስት ፕሬዚዳንታዊ መሆኑ አቢይ አህመድ ቀደም ሲል ያመነበት ነገር ነው ። ይህ የኢዜማም አቋም ነው። በእኔ ግምት ከሞላ ጎደል ሁሉም ኢጎሳዊ የሆኑ ፓርቲዎች ይደግፉታል። እናም በጣም የሚደገፍ ጅማሮ ነው።
ነገር ግን ይህ ጉዳይና ሌሎች ግዙፍ ጉዳዎች ለምሳሌ የስራ አስኪያጅ፣ የሕግ መወሰኛ፣ እና የፍትህ መንግስታዊ ቅርንጫፎች የሚኖራቸው የሃይል ክፍፍል፣ ሚዛንና አንዱ ሌላውን ባይነ ቁራኛ መጠባበቅ በተመለከተ የሚኖረው አወቃቀርና ስዋስው ከፍተኛ የሕገ መንግስት ማሻሻል ጥያቄ ነው ።
ይህም ማለት ያገሪቱ ብሄራዊ ምክር ቤት (ፈደራል ኮንግሬስ) አደረጃጀትና ምርጫ ሲስተም መለወጥ ይኖርበታል። ለምሳሌ አሁን ያሉት የጎሳ ክልሎች እንዳሉ ሆነው መንግስታዊ ቅርጹ ፕሬዚዳንታዊ ማድረግ ትርጉም አልባ ነው ። በጎሳ ጥቅምና ሚዛን ላይ የተመሰረተ ሕግ ወጥቶ ፕሬዚዳንቱ የዚያ ሕግ አስፈጻሚ ከሆነ ያ ፕሬዚዳንት የዜጋዎች ጥቅም ሳይሆን የጎሳዎች ጥቅም አስፈጻሚ ነው የሚሆነው።
ስለዚህ በሕገ መንግስቱ ማሻሻያ ወይም ክለሳ ውስጥ ሌላው ትልቁ ረፎርም ብሄራዊ ምክር ቤቱ ነው ።
ይህ ጉዳይ አሁን ያሉት ክልሎችን አከፋፈልና ያላቸው መብት የተመለከተ ለውጥ መኖር አለበት ። ለምሳሌ ብሄራዊ ምክር ቤቱ ባለ ሁለት ክፍል ሆኖ አንድ ለዜጋዎች አንድ ለጎሳዎች ሊሆን ይችላል። ወይም አንዱ ለተራው ሕዝብ ምክር ቤትና ሌላው የሰነቻዎች (ሴናቶሮች) ሊሆን ይችላል። ብቻ በግድ የፓራማው አወቃቀር መለወጥ ይኖርበታል
ስለዚህ ይህ ሁሉ የሚቆምበት ጂኦግራፊ የክልሎች ወይም የምርጫ ዲስትሪክቶች ከጎሳ ወደ ኢጎሳዊ እንደ ገና ካርታ መነደፍ ይኖርበታል።
ባንድ ቃል የቅርጸ መንግስት ሃሳብ አንዱ ያውም ትንሹ ነው። ትልቁ ሃሳብ የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት የመከልስና የማሻሻሉ ዝሆን የሚያክለው ጉዳይ ነው~
Re: የኢትዮጵያ ቅርጸ መንግስት ፕሬዚዳንታዊ ሊሆን ነው
Posted: 03 Mar 2022, 04:27
by Horus
የኢትዮጵያ ወደ ኋላ ዝቅጠት፡ ከፊውዳሊዝም ወደ ትራይባሊዝም (ዘውጊዝም)
እኔ እዚህ ካለሁበት አቢይም ሆነ የብልጽግና ፓርቲ ምን እንደ ሚያስቡ፣ እንዴት እንደ ሚያስቡ ለመገመት ወይም ለመተንበይ አልችልም። ግን አንድ ነገር አውቃለሁ፤ እሱም ኢትዮጵያ ከዘመነ ሃይለ ስላሤ ፊዩዳሊዝም ወደ ዘመነ ወያኔ ትራይባሊዝም (ጎሳ፣ ዘውጊዝም) መሸጋገሯ ወደ ኋላ እንጂ ወደ ፊት ማደጓ አይደለም።
ስለሆነም አቢይ አህመድ ባዲሱ ንግግሩ ስለ ድህነት፣ ኋላቀርነትና ክፍፍል ያነሳው ትክክል ቢሆንም የነዚህ ሶስት ጠላቶች ምንጭ አንዱ የጎሳ ፖለቲካና እና የጎሳ ርዕዮተ አለም ነው። ጎሰኝነት የክፍፍል፣ የአመጽ፣ የኋላቀርነት እና የድህነት ምንጭ ነው።
ኢትዮጵያ የሄደችው ወደ ኋላ ነው ፣ ከፊውዳል ወደ ጎሳ ስርዓት ። ወደ ቅድመ ፊውዳል ዘመን ሄደናል። ወደ ፊት መሄድ ወይም ኋላቀር አንሁን ማለት ከፊውዳኢዝም ወደ ዜጋ ዘመናዊ ፖለቲካዊ ማህበረሰብነት ወደ ግለሰቦች ልዕልና ፣ ወደ ነጻ ሃስብና ወደ ግለሰቦች ጥረት፣ ወደ ዘመናዊ ፍልስፍና ወደ ዘመን አብርሆት መጓዝ ነው ወደፊት መሄድ እንጂ በጎሳ እስር ቤት እየማቀቁ ስለ ብልጽግና ማውራት የንቃተ ህሊና ድህነት ነው።
አቢይና ፓርቲው ከጎሳ እስር ቤት ነጻ ወጥተው ወደ ዘመነ አብርሆት ወደ ዘመነ ነጻነት እና የሰዎች ስብዕና የበላይ ወደ ሆነበት ዩኒቨርስ እንሂድ እላለሁ !
Re: የኢትዮጵያ ቅርጸ መንግስት ፕሬዚዳንታዊ ሊሆን ነው
Posted: 04 Mar 2022, 13:58
by Horus