Page 1 of 1

ከመጀመርያው በትግራይ እውቅና ያላገኙት የእርቀ ሰላም እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች ከ3 ዓመት በኀላ ፈረሱ (Ethiopia Insider)

Posted: 01 Mar 2022, 21:15
by sarcasm
ከሶስት ዓመት በፊት የተቋቋሙ የሁለት ኮሚሽኖች ንብረት እና በጀት፤ ለአዲሱ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሊተላለፍ ነው
March 1, 2022

በሃሚድ አወል

ከሶስት ዓመት በፊት የተቋቋሙት የእርቀ ሰላም እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች ንብረት፣ ቢሮ እና በጀት፤ አዲስ ለተቋቋመው የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንዲተላለፍ ተወሰነ። አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ፤ በአዲስ አበባ አሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የሁለቱ ኮሚሽኖች ቅጥር ግቢ ውስጥ ቢሮ ማደራጀት መጀመሩን የተቋማቱ ኃላፊዎች ተናግረዋል።

ከሁለት ወር በፊት በአዋጅ የተቋቋመው የኢትዮጵያ አገራዊ የምክክር ኮሚሽን፤ በኃላፊነት የሚመሩ 11 ኮሚሽነሮች በተወካዮች ምክር ቤት ሹመታቸው የጸደቀው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ነበር። በአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ መሰረት፤ ኮሚሽኑ የራሱን ጽህፈት ቤት እና ምክር ቤት ያደራጃል።

የአገራዊ ምክክር ኮሚሽን ሰብሳቢ በመሆን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ቃለ መሃላ የፈፀሙት ፕ/ር መስፍን አርአያ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ አዲሱ ኮሚሽን ከፌደራል መንግስት ባገኘው ይሁንታ መሰረት ቢሮ የማደራጀት ስራውን ጀምሯል። የምክክር ኮሚሽኑ የሚገለገልባቸውን ቢሮዎች በማደራጀት ላይ የሚገኘው፤ በአዲስ አበባው የአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው የእርቀ ሰላም ኮሚሽን እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን በሚገኙበት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

የእርቀ ሰላም ኮሚሽን ጽህፈት ቤት ባለበት ቅጥር ግቢ ውስጥ፤ የኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን “ስራ ለመጀመር የሚያስችለው ቢሮ እየተዘጋጀለት” እንደሚገኝ የጽህፈት ቤቱ ዋና ዳይሬክተር ሰብለ ኃይሉ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ማረጋገጫ ሰጥተዋል። የፌደራል መንግስት ቅጥር ግቢውን ከመስጠት ባሻገር፤ የሁለቱን ኮሚሽኖች “ንብረት እና ቢሮ” አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ እንዲጠቀመበት እንደፈቀደ የምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

ፕ/ር መስፍን “እኛ ዝም ብለን መውረስ አንፈልግም። መጀመሪያ ያላቸው ንብረት ኦዲት ተደርጎ ለመንግስት ርክክብ ካደረጉ በኋላ ወደ እኛ እንዲተላለፍ ጠይቀናል” ሲሉ በሁለቱ ኮሚሽኖች እና በአዲሱ ኮሚሽን መካከል የሚደረገውን የርክክብ ሂደት አካሄድ አስረድተዋል። ሁለቱ ኮሚሽኖች ይገለግሉባቸው ከነበሩ ቢሮዎች እና ንብረቶች በተጨማሪ ተመድቦላቸው ከነበረው በጀት ውስጥ የተረፋቸውን ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ እንዲያስተላለፉ መወሰኑን ተናግረዋል።

የእርቀ ሰላም እና የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች ለ2014 በጀት ዓመት የተመደበላቸው 47 ሚሊዮን ብር ገደማ ነው። ከዚህ 25.7 ሚሊዮን ብሩ የተመደበው ለአስተዳደር ወሰን እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሲሆን፤ ቀሪው 21.4 ሚሊዮን ብር የተበጀተው ደግሞ ለእርቀ ሰላም ኮሚሽን ነው።

Continue reading https://ethiopiainsider.com/2022/6217/

Re: ከመጀመርያው በትግራይ እውቅና ያላገኙት የእርቀ ሰላም እንዲሁም የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽኖች ከ3 ዓመት በኀላ ፈረሱ (Ethiopia Insider)

Posted: 02 Mar 2022, 08:21
by sarcasm


የኢትዮጵያ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን