Page 1 of 1
የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 27 Feb 2022, 01:40
by Horus
አንደኛ፣ ማንኛው የፖለቲካ መሪ ገፊ ፍላጎቶች አሉት ። እነሱም (1) ባለስልጣን መሆን፣ መወሰን፣ ማዘዝ መቻል፤ (2) ገንዘብ ማግኘት ወይም ያገር ሃብት መቆጣጠር፣ ባገር ሃብት ላይ ማዘዝ፤ (3) መታወቅ፣ ዝነኛ ፣ ስመ ገናና መሆን እና (4) መከበር፣ ተቀባይነት ማግኘት፣ ተፈላጊ መሆን ናቸው። አንድ ሃቀኛ እውነት ተናጋሪ መሪ እነዚህ ነጂ ፍላጎቶቹን ከህዝብ መደበቅ የለበትም።
ይልቁንም እነዚህ ነጂ ፍላጎቶቹን የሚያሳካው አገርን ታላቅ ፣ ጠንካራ፣ ውሁድ፣ ሰላማዊ እና ተፈሪ በማድረግ እንደ ሆነ በግልጽ መናገር፤ እነዚህ ነጂ ፍላጎቶቹን ለማሳካት ህብረተሰብ ዲሞክራሳዊ ነጻና ፍትሃዊ በማድረግ፤ ሕዝቡን የበለጸገ የተማረ ጤናማ በማድረግ እና የሚፈጥር፣ አረንጓዴና መንፈሳዊ ባህል እንዲያብብ በማድረግ እንደ ሆነ ለሕዝቡ ሁልግዜ በግልጽ መንገር አለበት ።
ሁለተኛ፣ አንድ ትክክለኛ መሪ የሚወዱትን ሰዎች መውደድ ማክበር መርዳት እና ለነሱም ታማኝ መሆን አለበት ። የሚጠረጥሩትን ሰዎች በመጠርጠር ግን ለነሱ ያለው ግምትና ብያኔ ሰዎቹ በሚሰሩት ተግባር መለካት አለበት ። የሚጠሉትን ሰዎች መጥላት ሳይሆን እንዲፈሩት ማድረግ አለበት ። አንድ ሕዝብ አንድን መሪ የሚከተሉት ወይም ወደውት አለያም ፈርተውት ነው። ነገር ግን አንድን ሕዝብ ለረጅም ግዜ በፍርሃት ለመምራት ወይም ለመግዛት አይቻልም።
ሶስተኛ ፣ ማየት ማመን ነው፤ አንድ መሪ የሚታመነው በሚሰራቸው የሚታዩ ጭብጥ ስራዎችና ውጤቶች ነው ። ሕዝብ የሚታይ ስራን ያምናል፤ ባፍ በወረቀት የተነገረን ነገር ይጠረጥራል። እጅግ ደካማና የማይታመን መሪ የሚናገረው እና የሚሰራው ነገር የሚጣረሱበት ነው። ሕዝብን አንድ ሁለቴ በውሸት ለማታለል ይቻላል ግ ን የኋላ ኋላ በመሪ ላይ ትልቅ ውድቀት ያስከትላል።
አራተኛ፣ በሃሳብ የሚስማሙትን እና እንደ እንደ ህጻን የሚታዘዙትን ሰዎች ብቻ የሚሾም መሪ እራሱ ደካማና በችሎታው የማይተማመን ሰው ነው ። ስለዚህ ሕዝብ የአንድን መሪ ጥንካሬ የሚለካው በሚሾማቸው ሰዎች ጥንካሬ ስለሆነ መሪዎች ታማኝ ተከታዮችን ብቻ ከመሾም መጠንቀቅ አለባቸው ።
አምስተኛውና የመጨረሻው ምክር ከሁሉም የላቀ ነው ። አንድ መሪ የህዝብ ድጋፍ ወይም ድምጽ የሚፈልገው ወደ ስልጣን ላይ ሲወጣ ብቻ አይደለም ፤ ይልቁንም ለማስተዳደርና ስኬታማ መሪ ለመሆን አንድ መሪ ያልተቋረጠ የሕዝብ ድምጽና ድጋፍ ያስፈልገዋል።
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 27 Feb 2022, 03:49
by Horus
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 27 Feb 2022, 04:28
by Horus
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 27 Feb 2022, 12:39
by Abere
ከ 1- 5 በተዘረዘሩት መስፈርቶች ሲለካ ዐብይ አህመድ በሁሉም ዜሮ ነው ያገኘው - በእኔ አስተያየት። ወድቋል ማለት ነው። እግዜር መልካም መሪ ከህዝብ ጉያ ይውለድላት -ለኢትዮጵያ።
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 27 Feb 2022, 13:29
by Horus
አበረ፣
የእኔ አላማ ደጋፊም ተቃዋሚም፣ አድናቂም ተቺም ሃሳባችንን ስንሰነዝር መሰረት ባለው መለኪያ ወይም ክራይቴሪያ ላይ እንዲሆን በማሰብ ነው ። መለኪያዎቹ የፖለቲካ መሪነትና እስቴት ክራፍት በተመለከተ ያሉት ካታጎሪዎችን ሁሉ አያካትትም፤ ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸው። መለኪያዎቹ ለሁሉም አይነት ፖለቲከኛ ይሰራሉ። ማለትም አንድ ግለሰብ ፖለቲከኛ፣ ፓርቲ ወይም ጎሳ የፖልቲካ ትግል ሲያደርግ ከላይ ባሉት ገፊ ምክንያቶች እንለካቸዋለን። ፖለቲካ አላማ አለው፣ ይህ ግለሰብ ምንድን ነው የሚፈልገው? ይህ ፓርቲ ምንድን ነው የሚፈልገው? ይህ ጎሳ ምንድነው የሚፈልገው እያልን እነዚያ ፍላጎቶች ከራሳችንና ካገራችን ጥቅም ጋር በማስተያየት ነው ድጋፍ፣ ትችት፣ ቅዋሜ ማድረግ ያለብን ። ሁሉም ስልጣን ፈላጊ ነው። አንዱ ሰይጣን ሌላው መላክ አይደለም። ደጋፊም ተቃዋሚም በረጃ፣ ፋከት እየጠቀሰ የራሱን ጥቅምና አቋም ሲያራምድ ነው ወደ ስልጡን እና ፋያዊ አለም የምሄደው ። ለምሳሌ ይህ ብዙ የሚባልለት ዲያሎግ እራሱ አላማው ያልታወቀ ድራማ ይመስለኛል ። ሰዎች ዲያሎግ አድርገው የሚስማሙት ምን ለማድረግ ነው የሚለው ስይታወቅ ነው ሁካታው ሁሉ!
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 28 Feb 2022, 18:17
by Abere
ሆረስ፥
አንተ ቅን ሰው ነህ። በእኔ ግምት ከዕድሜ ጸጋ እና ትምህርት ችሎታ የተነሳ ብዙ ስለ አለም ታውቃለህ። አገራችን ብዙ እንቁ ጥሪት ሰዎችን እንድሁ እንደዋዛ ማጣቷ ያሳዝናል። አሁን እንኳን ለአብነት የመልካም ትውልድ ቅሪት ብልህ ምክር ለማዳመጥ ፍላጎት የለም። ከበፊቱ ስህተት አለመማር ይገርማል።
አንተ የዘረዘርካቸውን አንኳር መሰረታዊ ነጥቦች ዐብይ አህመድ በደንብ ያውቃል። እርሱ እና የኦሮሞ ድርጅቱ አውቆ የተደበቀ ቢጠሩት አይሰማም ነው። አንድ ቀን ግን ይህን ባለመሳማታቸው ጆሯቸው ሲቆነጠጥ ምነው ያኔ የብልህ ምክር ሰምቸ በነበር ይላሉ። የዓልአዛር እና የባለጸጋው የመጨረሻ ዕድል ፋንታ በመጽሀፍ ቅዱስ እንደ ተጻፈው አይነት።
የብሄራዊ ዲያሎጉን ነገር እርሳው - ወንድሜ። ሰውየው ትልቁን ዳቦ ሊጥ ነው ያደረገው። ምክንያቱም ግልጽ ነው ያችው የፈረደባት የጎሳ ፓለቲካ አየር በአየር ንግድ ነው - ይከስራል። እኔ እንዳነበብኩት ከሆነ 11 አባልት ተመርጠዋል - ቢያንስ 70-80% ኦሮሞዎች ናቸው። ለምን ኦሮሞ ተመረጠ አይደለም ። የአንድ ኮሚቴ አባላት ተመሳሳይ ባህርይ (ጎሳ) እያላቸው ከ 30% በላይ ከሆኑ በቃ ምንም አይነት ድምጽ ብልጫ መስፈርት አይሰራም - የሃሳብ እና የህዝብ ጥያቄ ያለው የኦነግ ብቻ ነው:: መቸም አንተ ዐብይ አህመድን ትጠላዋለህ ትለኛልህ - እኔ ግን ስራውን ነው የምጠላ በጣም ግብዝ ሰው ነው። ምን ችግር ስለሚጥመው እንደሆነ እንቆቅልሽ ነው። የሚገርመው ደግሞ በእድሜየ ካየኋቸ መሪዎች የህዝብ ድጋፍ ግልብጥ ብሎ ያገኘው እርሱ ነው - ግን ደግሞ ግልብጥ ብሎ ህዝብ የከዳ መሪ እርሱ ብቻ ነው። ይህን ካልኩ ዘንድ አንድ ነገር አብራራልኝ:-
ጠቅላይ ሚንስትር ርዕሰ ሚንስትር ከሆነ እና የጠቅላይ ሚንስትር ሚስት ደግሞ ቀዳማ እመቤት ይላሉ በኢትዮጵያ። ለመሆኑ የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ማን ነው? ፕሬዚዳንት ወይስ ርዕሰ ሚንስትር? ቀዳማይ እመቤት ወይም ቀዳሚ ጌታስ ማን? የማን ነው የፕሬዚዳንቱ ወይም የርዕሰ ሚንስትሩ ባልደረባ (ባለቤት)?
Horus wrote: ↑27 Feb 2022, 13:29
አበረ፣
የእኔ አላማ ደጋፊም ተቃዋሚም፣ አድናቂም ተቺም ሃሳባችንን ስንሰነዝር መሰረት ባለው መለኪያ ወይም ክራይቴሪያ ላይ እንዲሆን በማሰብ ነው ። መለኪያዎቹ የፖለቲካ መሪነትና እስቴት ክራፍት በተመለከተ ያሉት ካታጎሪዎችን ሁሉ አያካትትም፤ ግን ዋና ዋናዎቹ ናቸው። መለኪያዎቹ ለሁሉም አይነት ፖለቲከኛ ይሰራሉ። ማለትም አንድ ግለሰብ ፖለቲከኛ፣ ፓርቲ ወይም ጎሳ የፖልቲካ ትግል ሲያደርግ ከላይ ባሉት ገፊ ምክንያቶች እንለካቸዋለን። ፖለቲካ አላማ አለው፣ ይህ ግለሰብ ምንድን ነው የሚፈልገው? ይህ ፓርቲ ምንድን ነው የሚፈልገው? ይህ ጎሳ ምንድነው የሚፈልገው እያልን እነዚያ ፍላጎቶች ከራሳችንና ካገራችን ጥቅም ጋር በማስተያየት ነው ድጋፍ፣ ትችት፣ ቅዋሜ ማድረግ ያለብን ። ሁሉም ስልጣን ፈላጊ ነው። አንዱ ሰይጣን ሌላው መላክ አይደለም። ደጋፊም ተቃዋሚም በረጃ፣ ፋከት እየጠቀሰ የራሱን ጥቅምና አቋም ሲያራምድ ነው ወደ ስልጡን እና ፋያዊ አለም የምሄደው ። ለምሳሌ ይህ ብዙ የሚባልለት ዲያሎግ እራሱ አላማው ያልታወቀ ድራማ ይመስለኛል ። ሰዎች ዲያሎግ አድርገው የሚስማሙት ምን ለማድረግ ነው የሚለው ስይታወቅ ነው ሁካታው ሁሉ!
Re: የሆረስ ምክር ለርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ አሊ
Posted: 28 Feb 2022, 20:14
by Horus
አበረ፣
እንደ ምታውቀው እኛ የእራሳችን ቋንቋ ሳንመረምር የሌላው የመኮረጅ አባዜ የተናወጠን ሰዎች ነን ። ቀዳማዊት እመቤት በወረደ የተኮረጀው ‘ፈርስት ሌዲ’ ከሚለው ነው እንጂ አንድ ሰው ትርጉሙን በውል ያሰበ ሰው የለም። ድንቅ በሆነው በራሳችን ቋንቋ አሃድ፣ አድ፣ አት፣ አቶ ፣አጼ ማለት አንደኛ ፤ ፈርስት ማለት ነው ። አጼ የተባዕት የወንድ ስያሜ ሲሆን ለሴት አጺትጌ ፣ የቤት አጺት፣ እቴጌ እንላለን ። ቀዳማዊት እመቤት (ቀዳሚ የቤት እማ) በኛ ቋንቋ እቴጌ ይባላል። ስለዚህ መባል ያለባት እቴጌ ዝናሽ ነው።
ርዕሰ ብሄር ማነው? ርዕሰ ብሄር የለም፣ መኖርም የለበትም። ርዕስ፣ ራስ ማለት ነው ። የብሄር ራስ፣ የአገር ራስ፣ መንግስት ነው እንጂ አንድ ሰው አይደለም። በዚህ ዘመን መንግስት ማለት በህግ ህጋዊ ሰውነት የተሰጠው ተቋም ሲሆን በመሰረቱ ሕግ ነው፣ ወይም የሕጎች ህብር ነው ። ስለሆነም ይህ መንግስት የምንለው ድርጅት የአንድ አገር ሕዝብ ራሳቸውን ለማስተዳደር የሚፈጥሩት ተቋም ነው። ድርጅት ነው። ስልጣንም የሚሰጠው በህዝብ ነው፣ ስልጣኑም የሚወሰነው፣ የሚከለከለው እንደ አገር የተሰባሰበው ሕዝብ ነው ።
ፕሬዚዳንትም ሆነ ርዕሰ ሚኒስትር የመንግስት ስራ አስኪያጅ (ኤግዘከቲቭ) ማለትም ርዕሰ መንግስት እንጂ የሕዝብም የብሄርም የአገርም ራስ የበላይ አይደሉም ። የአገርና የብሄር የበላይ፣ የመንግስትም የበላይ ሕዝብና እነርሱ የፈጠሩት (በሶሺያል ክንትራት) ሕግ ነው ። ለዚህ ነው የሕግ የበላይነት የምንለው።
በፕሬዚዳንታዊ ቅርጸ መንግስት ያ ስራ አስኪያጅ (ኤክዘከቲቭ) በያንዳንዱ ዜጋ አንድ ድምጽ ስለሚመረጥ ለግለሰብ ዜጋ ብሎም ለሕዝብ ቅርብ ነው፣ በውክልናው ማለት ነው ። ፕሪዚዳንት የሚለው ቃል ፕራይመሪ ከሚለው የመጣ አንደኛ ቀዳሚ ማለት ነው ። ስለዚህ ፕሬዚዳንት ርዕሰ መንግስት ቢባል ትክክል ነው ።
ጠቅላይ ሚኒስትር የሚለው ቃል ስህተት ነው ። ወታደሮች ጄኔራል የሚለውን የጦር አዛዥ ለማለት ነው ። ሚኒስትር ማለት አገልጋይ፣ ቄስ ማለት ሲሆን ዛሬ ሰርቨንት ሊደርሺፕ የሚባለው ነው ። ያው መንግስት የሕዝብ አገልጋይ ለማለት ነው። ይህም ሆነ ያ ርዕሰ ሚኒስትር ቀዳማዊ ሚኒስትር፣ የሚኒስትሮች ራስ ማለት እንጂ የብሄር፣ ያገር ራስ ማለት አይደለም።
በተለይ ርዕሰ ሚኒስትሩ በቀጥታ በሕዝብ የተመረጠ ሳልሆነ የመንግስቱ ስራ አስኪያጅ ክንፍ መሪ እንጂ የሕግ መወሰኛም ሆነ የሕግ ተርጓሚው የበላይ አይደለም። አቢይ አህመድ የእራሱ ሚኒስትሮች አለቃና የመንግስት ስራ አስኪያጅ የበላይ ነው።
ይህ ሁሉ የሚያሳየው የኢትዮጵያ የጎሳ ሲስተም የፖለቲካ ፍልስፍና የሌለው፣ የፖለቲካ ቲኦሪ የሌላው፣ የመንግስት ስልጣን ምንም አይነት የተፈጥሮ ሆነ ሎጂካል ተዋረድ ከሕዝብ ጋራ የሌለው ከላይ እስከ ታች በውዥንብር የተዋቀረ ቀውስ ወይም ዲሶርደር ነው ። መንግስት ተብሎ የሚታመሰው ሁሉ የጨረባ ተዝካር ነው። ለምሳሌ ...
የመንግስት ስልጣን ምንጭ ምንድን ነው? ማነው? ብሄር/ጎሳ ነው ይሉናል። የብሄር/የጎሳ ስልጣን ምንጭ ምንድን ነው? ማነው? መልስ የለም!! ይህን ነው የፖለቲካ ሲስተም ተብሎ የሚቦካው! ያሳዝናል! ያሳፍራልም!!!