ብ/ጄኔራል ተፈራ ማሞ ከፍትሕ መጽሔት ጋር የነበራቸውን ቃለ ምልልስ ጋዜጠኛ ብሩክ ይባስ ተርኮታል‼
*************
የጀንራሉ ምስጢሮች!! "የአማራ ልዮ ኃይልን ማዳከም ተፈልጓል፣ ልዮ ኃይሉ ከተወሰነ ግዜ በኋላ ያፈረሱታል፡፡ ግድቡን እየጠበቀ ያለው የአማራ ልዮ ኃይሉ ጋፋት ብርጌድ ነው፡፡" ብ/ጀንራል ተፈራ ማሞ
ያኔ ወያኔ በአማራ ላይ ወረራ ሲያካሂድ መከላከያ (እንደ ተቋም) ሲሰራው የነበረውን ሸፍጥና ደባ ስናጋልጥ "የወያኔ ናፋቂ፣ መከላከያን ለመከፋፈል፣ ሀገር አፍራሽ" እያላችሁ መዓት ስታወርዱ ለነበራችሁ ሰዎች ይሄው እውነቱ ጊዜውን ጠብቆ ወጥቷል።
የአማራ ህዝብ ሆን ተብሎ በፌደራል መንግስት በተቀናበረ ሴራና በሰርጎ ገብ የኦነግ ጄኔራሎች አሳላጭነት ነበር በዘመኑ ለአሳዛኝ ውድመትና ጥፋት እንዲጋለጥ የተፈረደበት።
"መከላከያ ሰራዊት እየሸሸ ነበር። የአማራ ልዩ ሀይል ከታጠቀው በላይ የሆነ ከባድ መሳሪያ ለወያኔ ታጣቂ እየተወ በመሸሹ የአማራ ልዩ ሀይል በወያኔ አማካኝነት በመከላከያ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ ተወግቷል"
"ሶስት ብርጌዶችን በኮማንዶ ደረጃ ልናሰለጥን ዝግጅታችንን ስንጨርስ መከላከያ ውስጥ ያሉም፣ የፖለቲካ አመራሩም ተንጫጩብን"
"የአባይን ግድብ በሙቀትና ውሃ ጥም እየተሰቃዬ የሚጠብቀው የአማራ ልዩ ሃይል ጋፋት ብርጌድ ነው"
"የአማራ ልዩ ሀይልን ማዳከም ተፈልጓል፣ ልዩ ሀይሉን ከተወሰነ ጊዜ በኋላ ያፈርሱታል"
"አብይ እና ደመቀ አድስ አበባን ለማዳን 2 በርጌድ ልዩ ሀይል በአስቸኳይ ወደ ጣርማ በር ላኩልን፣ ሲሉን ልዩ ሀይሉ ጣርማ በር ላይ ገብቶ ለማመን የሚከብድ ጀብድ በመስራት የወያኔን ግስጋሴ ገቶታል"
"ብዙ ሴራ ቢኖርም አሁን ላይ የአማራ ልዩ ሀይልን በፊት ከነበረበት በ10 እጥፍ አሳድገንዋል" he said
አሁንም ራስን በመሆን
የራስን ሀይል በማጠናከር፣ በማደራጀት፣ በማሰልጠንና በማስታጠቅ፣ የግዛት ኢ_ተነጣጣይነትን በማጉላት ተለጣፊነትን፣ አድርባይነትን፣ ይሉኝታን ካልተፋታን የነገውና የተደቀነልን ጥፋት ከዛሬው የከፋ ነው።
Please wait, video is loading...