Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ርዕሰ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ሺመልስ አብዲሳን፣ አዳነች አቤቤን እና አሁን የሚያዳምጣቸው መካሪዎቹን ካላስወገደ ወደ ግዙፍ ቀውስ እየወረደ ነው

Post by Horus » 25 Feb 2022, 23:32

ጥቂት ምሳሌዎችን እንጥቀስ ...
ኢትዮጵያዊያን መንግስት ደግፈው በመላ ኢትዮጵያ እና አለም ላይ እንደ አንድ ሰው ተነስተው የፈጠሩትን ሃይል፣ በድምጹ፣ በገንዘቡ፣ በእውቀቱ በነጻ ለአገር የተነሳውን ሕዝብ ጀርባውን በጎሳ ሳንጃ ወግተው ሰንደቅ አላማህን መያዝ አትችልም ብለው ታቦት ሜዳ አሳድረው፣ ምዕመናን ገድለው ኦርቶዶክስን አዋርደው በቀሰቀሱት የህዝብ ቁጣ አስገራሚ በሆነ ፍጥነት የህዝብ ድጋፍ እየሸሻቸው ይገኛል ።

የአሜሪካ ኮንግሬስ አዲስ የእቀባ እና ጣልቃ መግቢያ የህግ ረቂቅ 6600 ወደ ህግነት በመገስገስ ባለበት ወቅት የአሜሪካ ዲያስፖራ ጸጥ ብሏል፤ የገንዘብ መዋጮ እየደረቀ ነው፤ ሃላዋ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ጥቁር ገበያ ዞሮዋል። አለም አቀፍ ስብሰባዎች ከአዲስ አበባ ወደ ሩዋንዳ ወዘተ እየተወሰዱ ነው ፤ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ስብስብ ተወግዳለች ። በአንድ ቃል አቢይና በዙሪያው ያሉ የጎሳ መሰሪዎች መንግስትን ይዘው ገደል እየወረዱ ነው ።

በአንድ ቃል አቢይ አህመድ ባለፈው 3 ወራት ሲያማክሩት የነበሩ ጭለማ የለበሱ ዘረኞችን ባስቸኳይ ካላስወገደ አሁን የያዘው ጉዞ ቁልቁል ሩጫ እንደ ሆነ ግልጽ ነው!

ዝሆን ሲከሳ ሃብታም ሲፈሳ (ሲደሀይ) አይታወቅም ይባላል! አቢይ አህመድ የሚገኝበት የፖለቲካ ውጥንቅጥና ድክመት ምን እንደ ሚያክል የሚነገው አንድ መካሪ ይፈልጋል!

ይህን የቁልቁለት ሩጫ የሚያስቆመው እጅግ ተቀዳሚ ስራ ትህተቱን ተቀብሎ የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ መጠየቅ ነው!!