Page 1 of 1

ሳተናው ፋኖ ምሥጋንችን ሲያንስህ ነው - በሬህን ሽጠህ፥ከሌለህ መጥረቢያ ይዘህ አገርህን ታደገሃል - መንግስት ሳያስታጥቅህ ቀምተህ ታጠቅህ። ዩክሬይን ዜጋውን ኑ! ታጠቁ ሲል ትዝ አልከኝ።

Posted: 24 Feb 2022, 12:57
by Abere
ሳተናው ብርቅዬ አማራ ፋኖ ምሥጋንችን ሲያንስህ ነው - ሃብት ካለህ በሬህን ሽጠህ፥ ከሌለህ መጥረቢያ እና ዱላ ይዘህ የትግሬን ባንዳ መሳርያ ማርከህ አገርህን ታደገሃል - መንግስት ሳያስታጥቅህ ቀምተህ ታጠቅህ። ዛሬ የዩክሬይን መንግስት ዜጋውን ኑ! ታጠቁ ሲል ትዝ አልከኝ አንተ።

ስንቱ ውስጥ ጥርስ ገብተህ ነበር? አዎን ታጥቀህ እራስህን ማስከበረህ ተፈጥሮአዊ መብትህ ብቻ ሳይሆን ህጋዊ መብትህም ነው። ዩክሬይን ጥሩ ትምህርት ይሰጥሃል። መታጠቅ መብትህ ነው። ዛሬ የዩክሬይን መንግስት ጥሪ እንኳን አቅርቦ እንደምንሰማው ህዝቡ ከተማውን ጥሎ የመኪና መንገድ እያጨናነቀ ነው። ህይወቱን ለማዳን። እሳት የላሱት ጀግኖች እነ እሸቴ ሞገስ ፥ ጀኔራል ሃሰን ከሪሙ፤ የወያኔን ምሽ በፈቃደኝነት ፈንጅ ረግጠው የተሰዉትን ፋኖዎች ሳስብ የአማራ ፋኖ በባህሉ ብቻ ሳይሆን በደሙ ጭምር ነው ጀግንነቱ የተጻፈበት። ፋኖነት የፍትህ ዐርበኛ ነው።

ኮራን በፋኖ!!!