Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"እንደ ትግራይ ክልል የደቀቀ በጣም ጉዳት የደረሰበት የለም። እንዳትሳሳቱ ይሄንን። ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት አማራ አፋር ኦሮሞ ዕዳ አለብን ገና።" ጠ/ሚ አቢይ

Post by sarcasm » 23 Feb 2022, 21:01

"እንደ ትግራይ ክልል የደቀቀ በጣም ጉዳት የደረሰበት የለም። እንዳትሳሳቱ ይሄንን። ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት አማራ አፋር ኦሮሞ ዕዳ አለብን ገና።" ጠ/ሚ አቢይ

Abere
Senior Member
Posts: 15490
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: "እንደ ትግራይ ክልል የደቀቀ በጣም ጉዳት የደረሰበት የለም። እንዳትሳሳቱ ይሄንን። ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት አማራ አፋር ኦሮሞ ዕዳ አለብን ገና።" ጠ/ሚ አቢይ

Post by Abere » 23 Feb 2022, 21:17


እንደት?
---ዕዳ ካለበት የእርሱ የራሱ ብቻ ነው። ትግራይ የገባው የመንግስት ወታደር ነው። መንግስት ደግሞ መሰረታዊ ልማት በአብዛኛው አስገዳጅ ካልሆነ አያፈርስም። የእክሱም ኤርፓርትን ያፈረሰው ወያኔ ነው። በእንዝህላልነት እና በሴራ ትግራይን ጥሎ ለሽፍታ ስለወጣ ሽፍታ ወያኔ ትግራይን ሊያወድም ይችላል። ስለሲህ ዕዳው የእራሱ የትግራይ ህዝብ ነው።

---በአማራ ክልል በተለይም በወሎ እንድሁም አሁን በአፋር የደረሰውን ውድመት ማን ይክፈለው። እነኝህ ክልልሎች በመንግስት ሳይሆን የተያዙት በሽፍታ የጦርነት ህግ በማያውቅ ነው። ስለዚህ ማን ካሳ ይክፈላቸው። ሊጥ ሳይቀር ተዘርፏል።

--ይህ ንግግሩ ህዝብ ነው ያሳቀበት - ሰውዬው ትንሽ ነካ ያደርገዋል። 100 ቢልዮን ብር ለማን ሰጥቶ መጣ? ለምን 100 ቢልዮን ለወሎ ህዝብ ካሳ አይከፍልም? ሂሳብ የምንተሳሰበው የተሰረቀ ሊጥ ዋጋ ሳይቀር ተተምኖ ሲመጣብቻ ነው። ዐብይ ካወራ ምን አነሰው።

Assegid S.
Member
Posts: 950
Joined: 11 Aug 2013, 07:11
Contact:

Re: "እንደ ትግራይ ክልል የደቀቀ በጣም ጉዳት የደረሰበት የለም። እንዳትሳሳቱ ይሄንን። ትግራይ ክልልን መልሶ ለመገንባት አማራ አፋር ኦሮሞ ዕዳ አለብን ገና።" ጠ/ሚ አቢይ

Post by Assegid S. » 24 Feb 2022, 07:50

እርግጥ ነው የትግራይ ህዝብ ኢትዮዽያዊ እስከሆነ ድረስ የዛን ህዝብ ቀንበር መሸከም የጋራ ተግባር ይሆናል። እኔ እስከሚገባኝ ድረስ የኢትዮዽያውያን ፀብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ሳይሆን ከህወሃትና ህወሃትን ከጥቅም ጋር በተሳሰረ መልኩ ከሚደግፉት እፉኝቶች ጋር ነው። ምንም እንኳን "የትግራይ ህዝብ ህወሃትን ይደግፋል" የሚል ሰፊ እሳቤ ቢኖርም ሐቁ ግን ይህ አይደለም። ስለዚህ፦ የትግራይን ህዝብ ብቻ ሳይሆን በዚህ ጦርነት የተጎዱትን ኣፋርንም ሆነ ኣማራን መልሶ በእግራቸው የማቆም ተግባር የሀገር ግዴታ ይሆናል። በዚህ ሓሳብ ላይ ልዩነት ባይኖረኝም፥ ጠቅላይ ሚንስትሩ የተናገሩበት ለዛ ግን ከነባር "ልወደድ ባይነት" ስሜት የተንደረደረና እራሳቸውን "ከደሙ ንፁህ ነኝ" በሚል መንፈስ የቀረበ ስለሆነ ግብዝነት ነው ብዬ አልፈዋለሁ።

ከዚህ ባሻገር ግን፦ ጠቅላይ ሚንስትሩ በምክር ቤቱ አስቸኳይ ስብሰባ ንግግራቸው ላይ … የህዋትን እስረኞች በመፍታት ስለተገኘው በረከት ሲያስረዱ… የእጃቸውን ጣት ብር እንደሚቆጥር ሰው እያፋተሉ ብቻ ሳይሆን "በfigure አይተነዋል" ሲሉ ነበር የተናገሩት (28' – 28' 05") ። ያ ደግሞ … በሰዎቹ መለቀቅ የተገኘው (የተገዛው) መሬት፣ ነዳጅ ወይንም ብረት ሳይሆን እራሱ ብር እንደሆነ ፍንጭ ይሆናል። ይህ ብቻም ሳይሆን ... "ሰዎቹን ስንለቅ ለሀገር የሚጠቅም ተግባር አከናውንበት እንጂ በግል ጉቦ አልተቀበልንም (27' 35")" ብለው መናዘዛቸው … ለእኔ … መንግስት የሔደበት ኣንድ አለኣግባብ የሆነ መንገድ እንዳለና ያ መንገድ ደግሞ በቅርብም ይሁን ዘግይቶ ይፋ ሲሆን "ለሀገር ጥቅም" በሚል ምክንያት አዋዝተን እንድንውጠው እይያዘጋጁን እንደሆነ ይሰማኛል። እንደ እኔ ጥርጣሬ … መንግስት ስዎቹን ለመልቀቅ ወደ ግል ኪስም ባይሆን ወደ መንግስት ካዝና የሚገባ ብር ተቀብሏል። ጥርጣሬዬን በግልፅ አማርኛ ሳስቀምጠው … ሰዎቹ ከዘረፉት ብር አካፍለው ነው ከእስር የተለቀቁት።

ያ ብር ደግሞ ፍፁም ባልተለመደ መልኩ የአሜሪካ ተራዶኦ አድራጊ ድርጅት በዶላር ሳይሆን በብር ለኦሮሞና ኣማራ ክልል የሚውል እርዳታ (ድጋፍ) አደረኩ ያለው ገንዘብ ሳይሆን አይቀርም። ታሳሪዎቹ በተራድኦ ድርጅቱ አማካኝነት ለሀገሪቱ ( ለሁለቱ ክልል ) የሚውል … በልዩ ሁኔታ tag (ታግ) የተደረገ የገንዘብ ድጋፍ አድርገው ማለት ነው። ለግለሰብም ባይሆን ለመንግስት ጉቦ ሰጥተው። ጉቦ የሚበላ መንግስት በዘራችሁም አይድረስ 8)

ያም ሆነ ይህ ገንዘቡ ጥቂት አይደለም። ወጣቱን … በመደበኛ አጠራር ቄሮና ቄሪትን … ከህወሃት እስረኞች ጋር መሳ ለመሳ ከተለቀቁት ፅንፈኛ የኦፌኮ መሪዎች ለመነጠል ሊውል ይችላል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ የህወሃት ስሪት እንደመሆናቸው መጠን … የካፒታል ምንጭን ከህዝብ ሰውረው ፍንጭ ለማሳጣት ይቸግራቸዋል ብዪ አላምንም። ከጥቂት ኣመታት በፊት ዶ/ር ቴድሮስ አድሀኖም የዘረፉንን ገንዘብ ከአቶ አባ ዱላ ገመዳ ጋር በመመሳጠር … በሐረር እጅግ በጣም ልዩ ትምህርት ቤት ለመገንባት "ከኣውስትራሊያ መንግስት (ትምህር ቤት) የተለገሰ ስጦታ" በማለት … በላቀ የትምህርት ችሎታዋ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ የተሸለመች ሚጢጢ ኢንቨስተር ይዘውልን መጥተው እንደነበር ማን ይዘነጋል? ለህወሃትም ሆነ ለዚህ መንግስት፦ ካፒታልን በእጃዙር ብቻ ሳይሆን ናላንም በሚያዞር ድብቅ መረብ ማዘዋወር ብርቅ አይደለም። ስለዚህ የነ አቶ ስብሐት ነጋና ግብረ ኣበሮቻቸው ብር ... በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ... ትግራይን ብቻ ሳይሆን መላ ሀገሪቷን ለመገንባት ጥቅም ላይ ቢውል እኔ ብቻ ሳልሆንም Sarcasm እራሱም የሚቃወም አይመስለኝም 8)



Post Reply