Page 1 of 1

የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 13:33
by Revelations

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:05
by Revelations
Horus, don't be shy. It seems that you have cut your pro Abiy posts since these folks started speaking out. Did you get a condo, land ... as they allege?

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:11
by Horus
ሪቮ እርሳቸው! አንተና ኢቲዮ360 'ጸረ ብርሃኑ ፓርቲ' ብለሽ ዋሽንግተን ለበሰበሰው ህይወት ትርጉም ፍለጋ የመሸበት ድራማ ነው። ያንተ ግብረ ሃይል የሃብታሙ አያሌው አሻንጉሊቶች ናቸው ። ሌኒን ኢንፋንታል ዲስ ኦርደር ይላቸው ነበር ። ጽጉራቸው ሸብቶ እንደ ህጻን ያለቃቅሳሉ ! ላቅመ አዳም የደረሱ ለቆሙለት አላማ እና ለሰሩት ስራ እንደ ወንድ ቆመው ሃላፊነት ይወስዳሉ !! እነዚህ የሸመገሉ ህጻናት ናቸው ። ህይወታቸው ትርጉም አልባ አንዳይሆን የሆነ ቅዋሜ ማሰማት አለባቸው፣ መሰልፍ እንደ ሱስ መያዝ መድረሻው ያ ነው ። ፖለቲካ እግጅ ውስብስብና ለጠጣሮች እንደ ላስቲክ ተስበው እንደ ጠጠር ከረው እንደ ሽቦ ለሚጠመዘዙ የተፈጠረ ሙያ ነው! ፖለቲካ ለህጻናቶች አልተሰራም ። አንተ ብርሃኑ ስትቃወም እዚያው ዲ ሲ ሞተህ ትቀበራለህ!! አስታወስክ? መቼ ነው ይህን ነገር የጀመርነው? ከህይወትህ ተማር! እኔ አንተን ልጅ ሆነህ ሎስ አንጀለስ ነው የማውቅህ! ለፖለቲካ አልተፈጠርክምና ተወው! የኔ ምክር ነው ኬር!

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:24
by Horus
ረቨሌሽን፤
አጎትህ በህይወት ቢሆኑ (ነፍሳቸው ይማርና) ይህችን ስንኜ ምንኛ በወደዱት!? ኢትዮጵያ ቅኔ ነች! እንዳትረሳ!!

ሃባይ አቢ አባት አባይ
ያለም ፈጣሪ ብርሃነ ፀሃይ
አባይ የኢትዮጵያ ኩራዝ
አይነ ኩሉ ያገር መቅረዝ
የእናታችን ነዳጅ እንጨት
ከሰል ቅጠል ፈሳሽ እሳት
የማግኔት ልጅ አባ ንደት፤
እመ ሙቀት ነፍሰ ፍጡር
የስልጣኔ ነጂ ሹፌር
አባ ብርሃን ያለም ኢምር፤
የምድራችን ዕጹብ ፈፋ
ሃይለ ነገር ፍካተ ፏ ፋ
አባይ የጽልመት ጽኑ ጠላት
የሰማየ ሰማያት በራት።

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:26
by kibramlak
Ezema was wishy-Washy and that's why it got bear zero vote. I gave up on it to think as a credible political alternative when they were silent on all what happened in Addis and elsewhere in the country, to finally ally with the Abiy opdo adminstration for sharing left over power rather than serving for the bigger and noble purpose - stuggle with the people for the people. Very sad indeed. As organization, ezema is no different from opdo based on what I watched the so called ",presidential candidates debate. According to the horse's mouth (Birhanu nega) answers (and no answers) for the questions he was asked was in perfect alignment with that of ODPA aka OPDO.

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:38
by Selam/
I can’t stand 360. Period!
Revelations wrote:
20 Feb 2022, 13:33

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:40
by Revelations
ኧረ በወላዲቷ! አብዬ ከርሱ!

በብስጭት የጻፉት ምንም ፍሬ የለውም:: እውን እነኝህ የምናያቸውን በእድሜ ከእርሶ በጣም የሚያንሱ ጎልማሶች ሽማግሌዎች ብለው ሲጠሩ ጃጁ ያስብሎታልና ያስቡበት::

ግና አሁን ካሉት የተረዳሁት ነገር እርሶ የተቀበሉት የመቃብሮትን ቦታ ነው:: ዲሲ ኖረው ኢትዮጵያ እንዲቀበሩ ተፈቀደለዎት ማለት ነው:: አሁንም የዲሲ ነዋሪ ኖትና!

ሌላው የመጃጀቶት ምልክት ደግሞ ባለውፈው ተፈሪ መኮንን ትምሕርት ቤት እንተዋውቃለን ያሉትን ረስተው አሁን ደግሞ ሎስ አንጀለስ ነው የምንተዋወቀው ብለው ዘባረቁ:: ምነው አያ! ሃይ ባይ የሎትም ማለት ነው?!

Horus wrote:
20 Feb 2022, 14:11
ሪቮ እርሳቸው! አንተና ኢቲዮ360 'ጸረ ብርሃኑ ፓርቲ' ብለሽ ዋሽንግተን ለበሰበሰው ህይወት ትርጉም ፍለጋ የመሸበት ድራማ ነው። ያንተ ግብረ ሃይል የሃብታሙ አያሌው አሻንጉሊቶች ናቸው ። ሌኒን ኢንፋንታል ዲስ ኦርደር ይላቸው ነበር ። ጽጉራቸው ሸብቶ እንደ ህጻን ያለቃቅሳሉ ! ላቅመ አዳም የደረሱ ለቆሙለት አላማ እና ለሰሩት ስራ እንደ ወንድ ቆመው ሃላፊነት ይወስዳሉ !! እነዚህ የሸመገሉ ህጻናት ናቸው ። ህይወታቸው ትርጉም አልባ አንዳይሆን የሆነ ቅዋሜ ማሰማት አለባቸው፣ መሰልፍ እንደ ሱስ መያዝ መድረሻው ያ ነው ። ፖለቲካ እግጅ ውስብስብና ለጠጣሮች እንደ ላስቲክ ተስበው እንደ ጠጠር ከረው እንደ ሽቦ ለሚጠመዘዙ የተፈጠረ ሙያ ነው! ፖለቲካ ለህጻናቶች አልተሰራም ። አንተ ብርሃኑ ስትቃወም እዚያው ዲ ሲ ሞተህ ትቀበራለህ!! አስታወስክ? መቼ ነው ይህን ነገር የጀመርነው? ከህይወትህ ተማር! እኔ አንተን ልጅ ሆነህ ሎስ አንጀለስ ነው የማውቅህ! ለፖለቲካ አልተፈጠርክምና ተወው! የኔ ምክር ነው ኬር!

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 14:50
by Horus
kibramlak wrote:
20 Feb 2022, 14:26
Ezema was wishy-Washy and that's why it got bear zero vote. I gave up on it to think as a credible political alternative when they were silent on all what happened in Addis and elsewhere in the country, to finally ally with the Abiy opdo adminstration for sharing left over power rather than serving for the bigger and noble purpose - stuggle with the people for the people. Very sad indeed. As organization, ezema is no different from opdo based on what I watched the so called ",presidential candidates debate. According to the horse's mouth (Birhanu nega) answers (and no answers) for the questions he was asked was in perfect alignment with that of ODPA aka OPDO.
ክብራምላክ፣
እሺ አንተ ባልከው መሰረት ኢዜማ ዊሺ ዋሺ ስለሆነ በምርጫው ተሸነፈ (መሸነፉ ትክክል ነው በደምብ ተሸንፏል)፤ የኢዜማ ተቃዋሚው 'ዊሺ ዋሺ' ያልሆነው ባልደራስ ለምን በተመሳሳይ ተሸነፈ? ስለዚህ ወንድሜ መልሱ ያለው ሌላ ቦታ ነው? ያዲስ አበባ ህዝብ ደደብ እንዳይመስልህ? ህዝቡን እመን! ፖለቲካ የህዝብ ፍላጎት ማደራጃ መሳሪያ ነው እንጂ የኔና አንተ ስሜት ማስተናገጃ አይደለም ። በተረፈ እስቲ ውሺ ዋሺ ያልሆኑ ምን እንደ ሚፈይዱ እናያለን!! ባለም ላይ አንድ የማይለወጥ ነገር አለ፣ እሱም ለውጥ ነው!! ሁሉም ነገር ይለወጣል! ደግም ነግሮች በተለወጡ ልክ እንደ ድሮ ይቀጥላሉ ይባላል። ይህ ነው ዲያሌክቲኩ ቅኔው!! አትቸኩል እንዳትሳሳት! በስሜት የሚወስኑ ሁሉ በስህተት ያበቃሉ ይባላልና! ኬር

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 15:10
by Horus
በጣም ጥሩ! አሁን ነገሩ ስለኔና አንተ ሆነ ማለት ነው። እኔና አንተ ሎስ አንጀለስ እንተዋወቃለን አላልኩም! እኔ ሎስ አንጀልስ አውቅሃለሁ ነው ያልኩት!!!እኔ አንተ ተፈሪ መኮንን ባጠገቡም ስላልደረስክ እዚያ ላውቅህ እንዴት እችላለሁ? ከዚያ በተረፈ ሃሳብ ከምናበ ነፋስ እያወጣህ እዚህ ነው ምትኖረው እዚያ ነው ምታድረው ጥንቆላ አቁም !!! አይሰራም!! በነገራችን ላይ የሚቀጥለው 'ዳውን ዳውን ብርሃኑ' !!! ሰልፍ መቼ ነው? !!!!!!!!!!!!!

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 15:18
by kibramlak
ሆረስ፣
ባልደራስ ላይ ከፍተኛ የሆነ የእንግልት ዘመቻ መደረጉ እና በመጨረሻም በመሪነት የተሰየመው እስክንድርን ማሰር በተከታዮቹ ላይ የተስፋ መቁረጥ ደረጃ እንዲደርሱ ፣ ከዛም ወይ አለመምረጥ ካለዛ በአብይ ምላስ ተታለው መምረጥ፣፣ ይህ እኮ ቀላል ሳይኮሎጂ ነው፣፣ መሪ የተባለው ሳይኖር ተከታዮቹ እንደሚፈለገው ማስተባበር አይቻልም ነበር፣፣ ከዛ ባሻገር ባልደራስ አርቲኩሌት መሪ ያስፈልገው ነበር፣፣ እስክንድር ሀሳቡን በቃል አርቲኩሌት ማድረጉ ላይ ብዙም አይስብም፣፣ አካሄዱም የመሪነት ሳይሆን የአክቲቪስትነት ነበር አሁንም እንደዛው ነው፣፣ በተጨማሪም የባልደራስ የፖለቲካ ድንበር በአዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ ነው ተብሎ ተስሎ ስለነበር መራጮች አማራጭ ሲያጡ ወደ አብይ ሄደው እንደነበር ከአንዳንድ ሰወች ተገንዝቤያለሁ፣፣ የአዲሳባ ህዝብ ኡዜማን በቁጣ እና በንዴት ሲሆን የቀጣው፣ ባልደራስን ደግሞ ድንበር አሻጋሪ ነው ብሎ ባለማመን እና መሪው ባለመኖሩ በተስፋ መቁረጥ ወደጎን ስላሉት ነው፣፣ የሁለቱ የአወዳደቅ ሁኔታ ለማመዛዘን አይሆንም፣፣
Horus wrote:
20 Feb 2022, 14:50
kibramlak wrote:
20 Feb 2022, 14:26
Ezema was wishy-Washy and that's why it got bear zero vote. I gave up on it to think as a credible political alternative when they were silent on all what happened in Addis and elsewhere in the country, to finally ally with the Abiy opdo adminstration for sharing left over power rather than serving for the bigger and noble purpose - stuggle with the people for the people. Very sad indeed. As organization, ezema is no different from opdo based on what I watched the so called ",presidential candidates debate. According to the horse's mouth (Birhanu nega) answers (and no answers) for the questions he was asked was in perfect alignment with that of ODPA aka OPDO.
ክብራምላክ፣
እሺ አንተ ባልከው መሰረት ኢዜማ ዊሺ ዋሺ ስለሆነ በምርጫው ተሸነፈ (መሸነፉ ትክክል ነው በደምብ ተሸንፏል)፤ የኢዜማ ተቃዋሚው 'ዊሺ ዋሺ' ያልሆነው ባልደራስ ለምን በተመሳሳይ ተሸነፈ? ስለዚህ ወንድሜ መልሱ ያለው ሌላ ቦታ ነው? ያዲስ አበባ ህዝብ ደደብ እንዳይመስልህ? ህዝቡን እመን! ፖለቲካ የህዝብ ፍላጎት ማደራጃ መሳሪያ ነው እንጂ የኔና አንተ ስሜት ማስተናገጃ አይደለም ። በተረፈ እስቲ ውሺ ዋሺ ያልሆኑ ምን እንደ ሚፈይዱ እናያለን!! ባለም ላይ አንድ የማይለወጥ ነገር አለ፣ እሱም ለውጥ ነው!! ሁሉም ነገር ይለወጣል! ደግም ነግሮች በተለወጡ ልክ እንደ ድሮ ይቀጥላሉ ይባላል። ይህ ነው ዲያሌክቲኩ ቅኔው!! አትቸኩል እንዳትሳሳት! በስሜት የሚወስኑ ሁሉ በስህተት ያበቃሉ ይባላልና! ኬር

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 15:48
by Horus
ክብራምላክ፣
የኢትዮጵያን የፖለቲካ ሚዛን በትክክል የምታየው አይመስለኝ ። ኢዜማ በአገር አቀፍ ደረጃ ሰዎች ሁሉ ይገደሉበት ነበር፣ አይደለም ስብሰባ እና ቅስቀሳ መከልከል ። አገሪቱ አሁንም በጎሳዎች ሃይል ነው እየተገዛች ያለችው ። የኢዜማ ትልቅ ስህተት እስከ ተወሰነ ድረስ በጎሳዎች ውስጥ የህዝብ መሰረት ለማግኘት የክሎሎች ጥቅም አለማስተጋባቱ ነው፣ አሁን ከሚከሰስበት በተቃራኔው ማለት ነው ። ለምን በለኝ? እንደ አማራ፣ እንደ ጉራጌ ያሉ በኢትዮጵያዊነት ዙሪያ ንቅንቅ የማይሉት ህዝቦች የነበራቸው የራሳቸው ጎሳ መብትና ጉዳይ የሚያነሳላቸው ድርጅት ይፈልጉ ነበር። ማለትም አንድ የዜጋ ፓርቲ አላማው በግለሰን መብት የቆመ ሰርዓት ሆኖ አያይዞም የጎሳው ፖለቲካል እስፔስ ከብልጽኛዎች ጋር ኮንቴስት ማድረግ ሲገባው ያን ወሳኝና ግዙፍ ጉዳይ ለዘረኞቹ መተዉ ነው ሁለቱንም ወደ ሽንፈት የዳረጋቸው ። ምሳሌ ልስጥህ! የጉራጌ ህዝብ በየከተማው ያለውም ባላገር ያለውም ጉዳዩ በዜጋ ፓርቲዎች እንዲወከልለት ይፈልግ ነበር ። ብርሃኑ ለቅስቀሳ አገር ቤት ሄዶ ለጉራጌ ህዝብ ምን ለማድረግ ሃሳብ አለህ ብለው ሲጠይቁት ከእኔ የብሄረሰብ ጉዳይ በሚመለከት ምንም ነገር አትጠብቁ ብሎ እቅጩን ነገራቸው ። በ1987ቱ ምርጫ በድፍን የመረጠው ጉራጌ አንዲት ወምበር እንኳ ከለከሉት ። ይህ የሆነው ባላገር ነው። አዲሣባም ዜጋ፣ ኢትዮጵያ የሚሉት በአንድ የምርጫ ካርድ እንደ መቅረብ የባሰ ጠላቶች ሆኑ ። ዛሬም የምታየው ይህ ነው ። ይህን ሁሉ ያየው ህዝብ ኢዜማም ሆነ ሌላው የመንግስት ስልጣን ይዘው አገር ማረጋጋት እንደ ማይችሉ የማወቅ ዊዝደም ስለነበራቸው ለሁሉም ድምጽ ከለከሉ ፣ ያገር ህልውና ለመጠበቅ ሲሉ ማለት ነው ። ዛሬም ይህው እነኤርሚያስና ሃብታሙ ዋና ጠላታቸው የጎሳው ሰርዓት ሳይሆን ኢዜማ ነው ብለዋል ። እነሱም ለጥቂት ግዜ ተንጫጭተው ይከስማሉ፣ የፖለቲካ ዳይናሚክሱ በስሚታቸው ስለተጋረደ !

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 16:30
by Abere
ሆረስ ለክብረአምላክ ከሰጠው ማብርሪያ ውስጥ የሚከተለው አረፍተ-ነገር ግራ ገባኝ።

<...ያዲስ አበባ ህዝብ ደደብ እንዳይመስልህ? ህዝቡን እመን! >

ህዝብ መድፈር እንዳይሆንብኝ እንጅ ለእኔ የአዲስ አበባ ሰው በሆዱ እንጅ በጭንቅላቱ የሚያስብ አይመስለኝም። ለምን? አንድም ከፍርሃት ሁለትም ከሆድ አደርነት በመነጨ ምክንያት ከአገሪቱ መብቱን በማስከበር ረገድ እጅግ ኋላቀር እና ሌሎች ከጠርዝ ወይም ከአግሪቱ ዳርቻ መጥተው ነጻ እንዱያወጡት የሚፈልግ ህዝብ ነው። ምርጫ የሚመርጠው ልቡ የሚፈልገውን ሳይሆን በሆዱ ወይም በፍርሃቱ ተገዶ የማይፈልገውን መርጦ ይገባል። እንደ አህያ ይህኛው ባለ ጉልበት ይጫነው ሌላ ባለ ጉልበት ጭነት ያው ጭነት ነው ብሎ የሚኖር ህዝብ ነው። የአዲስ አበባ ህዝብ አንድ ነገር ላይ ግን ሪኮርድ የሰብራል - የድጋፍ ሰለፍ አለ ከተባለ ምድር ቀውጢ ትሆናለች - ምክንያቱም ይች መስዋዕት አታስከፍልም። የተማረውም ያልተማረውም የአዲስ አበባ ህዝብ አንድ ነው - ፈሪ ፥ ሆድ አደር። የኢትዮጵያ ህዝብ የነጻነት ቀን የራቀው በዋና ከተማዋ አድስ አበባ ፈሪ እና አድር ባይነት ነው። በአፍሪካ አገራት ዋና ከተሞች ታሪክ ፈሪ እና አድር ባይ ሆዳምነት ሪኮርድ ሰባሪ የኢትዮጵያው አድስ አበባ ነው - የዲክታተሮች የእግር ጫማ የሆነ ህዝብ። ሌሎች የአፍሪካ ከተሞች ህዝብ እኮ የዳቦ ሂሳብ ለምን ሶስት ሳንቲም ጭማሬ ለውጥ አመጣ ብሎ የሚጠይቅ የገባው እና የሰለጠነ ህዝብ ነው ያለው። እባካችሁ የአድስ አበባ ከተማ ህዝብ ምርጫ ትርጉም የለውም - invalid ነው::

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 17:43
by kibramlak
@Horus,
አዎ ኢዜማ ሰው ታሰረ ወይም ተገደለ ብሏል ግን ያ የሆነው ከእዲስ አበባ ውጭ ነው፣ በግልፅ የሆነው ደግሞ በኦሮሞ ጎሰኞች በሚተዳደር ወይም በእነዚሁ ትፅእኖ በሆነ አካባቢ ነው፣፣ አዲሳባ ለምን ኡዜማ በዜሮ ወጣ ብለህ ብትጠይቅ መልሱ እላይ ያልኩህ ነው፣፣ ሌላው በአማራ ክልል ኢዜማ መሰናክል ያጋጠመው ግንቦት ሰባት እያለ ከሰራው ስህተት ነው፣፣ ተዋጊወችን እና የጦር ጉዳተኞቹን ያለምንም ድርድር (ከመንግስት ጋር ማለቴ ነው) በሜዳ ትቷቸው አዲስ አበባ ከአብይ ጋር መሞዳሞዱ ጥርስ አስነክሶበታል፣፣ ያም ሆኖ ግን በኦሮሞ ጎሰኞች እንደተደረገው የግድያ እና የእስር እክል በአማራ ክልል አላጋጠመውም፣፣ አሁንም ልድገምልህ፣ ኢዜማ ከኦሮሞ ጎሰኞች የተገለለው በፖለቲካ አቋም ሲሆን ከአማራ ክልል ደግሞ (ልክ እንደ አዲሳባ) በሰራው ስህተት በተፈጠረ ቁጣ ነው፣፣ እኔ የምልህ የሆነውን እና እሁንም እየሆነ ያለውን ነው፣፣ ልዩነታችን አንተ ትንቢት እና መላምት ላይ ታተኩራለህ እኔ ደግሞ በወቅቱ እና መሬት ላይ ባለው ሁኔታ ተመርኩዤ ነው፣፣ የፖልፕቲካውን ሁኔታ አለመገንዘብ አደለም፣፣ ስለ አብይ እና ስለኦሮሙማ በተፈጠርፕው ምስቅልቅል እስካሁን አልተሳሳትኩም፣፣ እስኪ ቆም በልና እያንዳንዳቸውን ነጥቦች ለማያያዝ ሞክር፣፣ መላምት ላይ ሳይሆን ስለሆኑት ነገሮች እና እየሆኑ ስላሉት፣፣ የዛኔ የፖለቲካውን አሰላለፍ እና አቅጣጫ በተሻለ ታስተውላለህ፣፣

@Abere
አዎ የአዲሳባ ህዝብ የተሰለበ ነው፣፣ ይመስለኛል በ97ቱ እስራት እና ግድያ በዛው ተደናግጦ የቀረ ህዝብ ይመስለኛል፣፣ እሁን አዱሳባ የትም ቦታ ብትሄድ የማንም ሰገጤ እበሩ ላይ ሲሸናበት እና ሲያራበት ዝም ብሎ የማይተነፍስ ህዝብ ነው የሆነው፣፣

እንደ እውነት ከሆነ አሁን ያለው አዲሳባ ሳይሆን እዲገጤ ነው

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 19:40
by Horus
ታሪክን የሚሰሩ ህዝቦች ብቻ ናቸው፣ ፖለቲክኞች አይደሉም። ፖለቲከኞች የህዝብ ጥቅም በማስጠበቅ ሰበብ ማግኘት የሚፈልጉት ስልጣን፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ወይ እስታተስ ነው ። የህዝቦች ፍላጎትና ፍርሃት ከፖለቲከኞች የሃይል ጥማት ጋር አብሮ አልሄድ ሲል ህዝቡ ይንቃሉ፣ ህዝቡን ይሰድባሉ። ህዝቡ እንደ በግ እሺ እያለ ሲከተላቸው ሰማይ ያደርሱታል።

የትግሬ ህዝብ እንደ በግ ፖለቲከኞችን በመከትል በመቶ ሺና በሚልዮን ለእርድና መስዋዕትነት ይቀርባል ። አው ያ እንደ እንሰሳ ለጥቂቶች ስልጣንና ክብር እንደ ሙጃ የሚታጨደው ጀሌ ደፋር እና ሆዱን የካደ ተብሎ ይዘፈንለታል ። የህልውናውና የፖለቲካ ተካፍሎው ምክንያት ምን እንደ ሆነ የሳተ ያ ለዕርድ የሚነዳው እንጂ አዲስ አበቤ አይደለም።

ሕዝብ ትልቅ ስህተት በታሪክ የሚሰራው በእብዶች፣ በዴማጎጎች እና በስልጣን ሰካራሞ ሲነዳ ብቻ ነው ። የጀርመን፣ የጃፓን፣ የትግሬ ታሪክ ምሳሌዎች ናቸው ። በቀሩት የህዝብ ሎሌክቲቭ ሶሺያል ባህሪያት ሁሉ ብዙሃን ኮሌክቲቭ ዊዝደም አላቸው ። ከነዚህ ዊዝደሞች አንዱ ህዝብ ከምንም ነገር መጀምሪያ የሚፈልገው ሰላም ነው ። በዚህ የህዝብ ተቀዳሚ ፍላጎት የማይስማማ ሰው ፖለቲካ አጠገብ መድረስ የለበትም እንኳንስ የሰዎች መሪ ሊሆን ቀርቶ ። ህልውና የሰው አይደለም የፍጡር ሁሉ የመጀሪያ ጥቅም ነው ።

የሰው ልጅ ከህልውናው ቀጥሎ በልቶ ካሎሪ በማግኘት እራሱን ከረሃብና ሞት መከላከል አለበት ። ይህን የፍጥረትና ኢቮሉሽን ህግ የማያውቅ ሰው እንኳንስ ሕዝብ ሊመራ ፖለቲካ አጠገብ መድረስ የለበትም ። የህዝብ አላማ አንድን ስልጣን ፈላጊ ማንገስ ወይም እሱን እንደ እግዚአብሄር በመከተል ለመሰዋት አይደልም ። ሕዝብ አንድን ፖለቲከኛ እንዲመራቸው የሚቀበሉት እነሱ የሚፈልጉትን ነገር ፣ ጥቅማቸውን ለማስፈጸም ነው ።

ሶስተኛ አንድ ህዝብ ፍርሃት ካለው እና ፈሪ ከሆነ ያ ህዝብ አለብኝ የሚለው አደጋ አለ ማለት ነው ። ይህን ህዝብ አለብኝ የሚለውን አደጋ (ፍርሃት የአደጋ መኖር አመልካች ስለሆነ) የፖለቲካ መሪዎች ማየት ካልቻሉና ከዚያ አደጋ ተመጣጣኝ መሪነት መስጠት ካልችሉ ፖለቲካ አጠገብ መድረስ የለባቸውም እንኳንስ መሪ ሊሆኑ ።

የፖለቲካ ፓርቲዎችና መሪዎች አይደሉም ህዝብን ነጻ የሚያወጡት! ሰው እራሱ፣ ሕዝብ እራሱ ነው ነጻ የሚያወጣ! ሕዝቡን ነጻ መውጣት አትፈልግም ብለው የሚገስጹ ህዝብ ለምን በፖለቲካ እንደ ሚደራጅና የፖለቲካ ፐርፐዝ ምን እንደ ሆነ ያልገባቸው ናቸው ። ፖለቲካ የህዝቦችን ጥቅም ማለትም ህልውና፣ ሆድ፣ ምግብ፣ ቤት፣ መንገድ፣ አደጋ፣ ፍርሃት ችግሮች ለመፍታት ነው። ይህ የፖለቲካ ሳይንስ ሃ ሁ ነው!

ጎበዝና ብልህ የሆኑ ብቁ የፖለቲካ መሪዎች እነዚህን የህዝቦች መሰረታዊ ፍላጎቶች፣ የነጻነትና መብት ፍላጎቶች ጭምር ከራሳቸው የሃይልና ዝና ፍላጎት በማጣጣም ሲያካሂዱ ስኬታማ፣ ታላቅ መሪ ይባላሉ። ያን ማጣጣም ሲያቅታቸው ይወድቁና ሕዝቡን ወደ መውቀስ፣ ሕዝቡን ወደ መስደብ ይወርዳሉ ። ያ ደሞ ፍጹም ፍጹም ስህተት ነው ። ያውም አንድ ህዝብ ያልመረጠው ሰው ህዝብን ለምን ያልኩት አልተከትልክም ብሎ የሚቆጣ ከሆነ ጤማና ነገር አይደለም።

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 22:18
by Revelations
ኧረ አንቱዬ! ምነዋ?!

"ፅድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ" አሉ የአገሬ ሰዎች! ግጥሙ ቀርቶብን የተቀበሉትን ቢነግሩን ይሻላል:: ግን ለማንኛውም የመቅብር ቦታ ሲቀበሉ የሬሳ ማጓጓዣ ቲከት አስጨምረዋል ወይ?! ግን ግን ከኦህዴድ የተዋዋሉት ነገር ይታመናል ወይ?! ለማንኛውም የመርካቶ ኪዎስክ ዛሬውኑ ተቀብለው ቢሸቅሉ ይሻሎት ነበር:: ብርሃኑ ነጋ አገር ተመልሰው እንዲኖሩ ከፈቀደለዎት ማለቴ ነው::

Horus wrote:
20 Feb 2022, 14:24
ረቨሌሽን፤
አጎትህ በህይወት ቢሆኑ (ነፍሳቸው ይማርና) ይህችን ስንኜ ምንኛ በወደዱት!? ኢትዮጵያ ቅኔ ነች! እንዳትረሳ!!

ሃባይ አቢ አባት አባይ
ያለም ፈጣሪ ብርሃነ ፀሃይ
አባይ የኢትዮጵያ ኩራዝ
አይነ ኩሉ ያገር መቅረዝ
የእናታችን ነዳጅ እንጨት
ከሰል ቅጠል ፈሳሽ እሳት
የማግኔት ልጅ አባ ንደት፤
እመ ሙቀት ነፍሰ ፍጡር
የስልጣኔ ነጂ ሹፌር
አባ ብርሃን ያለም ኢምር፤
የምድራችን ዕጹብ ፈፋ
ሃይለ ነገር ፍካተ ፏ ፋ
አባይ የጽልመት ጽኑ ጠላት
የሰማየ ሰማያት በራት።

Re: የዲሲ ግብረሀይል አዲሱ የትግል ምዕራፍ [VIDEO] - Horus come in

Posted: 20 Feb 2022, 23:43
by Revelations