Page 1 of 1

ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል ማለት ምን ማለት ነው?

Posted: 19 Feb 2022, 12:47
by Horus
sarcasm,
አንተና ዴቭ ዳዊት የምትባሉ ሰዎች በደምብ ያልገባችሁን ተረት አላግባብ በመጠቀም አበላሻችሁት! ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል የሚባለው ተረት ለዚህ አይሰራም። እናንተ እንደ ምትሉት ነው እንበልና አቢይ ይህን ሁሉ ፎቶ የሚለጥፈው ለራሱ ዝና፣ ለመታወቅ፣ ለፓፕሊክ ሪሌሽን ትርፍ ነው እንበል ። ያ ደሞ ሊሆን ይችላል። በጣም ትክክል ነው። ይህ ፓፕሊክ ሪሌዝን ኦፕቲክስ ይባላል፣ የራስን ጉዳይ ፕሮሞት ማድረጊያ የታወቀ ብልሃት ነው ። ይህ ሁሉ ከተረቱ ጋር ምንም ግንኙነት የለውም ። ተረቱን ካቢይ ፎቶች ጋር ያዛማደው ሰው ያማራኛ ቋንቋ ምሳሌና አግብዎ አያቅም። ይህ ተረት የሚሰራው ለሚከተለው ሁኔታ ነው ። ለዚህ ተረት ተመሳሳዩ ያልዘሩት አይበቅልም የሚለው ነው ። ያም ማለት አንተ አንድ ነገር እንዲደረግልህ የምትጠብቅ ከሆነ፣ ኤክስፔክት የምታደርግ ከሆነ አንተ እራስህ ተመሳሳይ ዉለታ ወይም መልካምነት ለዚያ ሰው ማድረግ አለብህ ማለት ነው ። ሰውነትህ በጥንካሬ ዳገት እንዲያወጣህ የምትፈልግ ከሆነ ሰውነትክን ተንከባክበህ ጎመን ሳይሆን ክትፎ በቆጮ መመገብ አለብህ ማለት ነው ። ያላደረከው ዉለታ ልታገኝ አትችልም ማለት ነው ። ይህ ምሳሌ አቢይ ያገኘው እድል ተጠቅሞ ፒ አር መስራቱ ጭርሶ ከዚህ አይገናኝም። ለምሳሌ ጥናት ማጥናት የማይወድ ተማሪ ኮሌጅ ልገባ እፈልጋለሁ ሲል ያ ተረት ይተረትበታል። ያልዘሩት አይበቅልም፤ ጎመን ብቻ የሚበላ ጉልበት ዳገት አይወጣም ማለት ነው! ቋንቋ አታበላሹ!!!!

Re: ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል ማለት ምን ማለት ነው?

Posted: 19 Feb 2022, 13:01
by Abere
ዐብይ አህድ የሌሎች መሪዎችን ፎቶ አብዝቶ ሲለጥፍ እነርሱ ባጸፋው እርሱን ለጥፈውት ይሆን? በእውነት አንዳቸውም ከእርሱ ጋር የተነሱትን ፎቶ በመለጠፍ ትንሽ ነገር ከጻፉ ዐብይ አህመድን ከቁብ ቆጥረውታል ማለት ነው። ከምን ጋር የዋለች ጊደር ምን ተምራ መጣች እንዳይባሉ ምንም ነገር እነርሱ ላይለጥፉ ይችላሉ የሚል የግል ግምት አለኝ።