በሁለቱ የጦር ወንጀለኞች መካከል እየተካረረ የመጣው አተካራ ጎልቶ የታየው፤ የትግራይ ሰራዊት ከሰሜን ሸዋ ከተመለሰበት ጊዜ ጀምሮ ነው የሚሉት እነዚህ ምንጮች፤ በተለይም ከሳምንት በፊት አብይ ወደ አስመራ ተጉዞ በነበረበት ወቅት ሁኔታው ይበልጥ መካረሩን ነው የገለፁት!
የትግራይ ጦር ወደ አዲስ አበባ በተጠጋበት ወቅት፤ ለእርዳታ ከኤርትራ የመጡት ክፍለጦሮች፤ የትግራይ ጦር ወደ ትግራይ መመለስ ማግስት ወደ ኤርትራ እንዲመለሱ ሲደረግ፤ በየአካባቢው ከእነሱ ጋር ተዳብሎ የነበረውን አዳዲስ የኢትዮጵያ ከባድ የጦር መሳሪያዎች ታንኮችንና ኦራል ተሽከርካሪዎችን በሙሉ ይዘው ለመሄድ ሲዘጋጁ ነው ንትርኩ ጎልቶ የወጣው::
የመከላከያ ሎጂስቲክስ፤ የኢትዮጵያ መከላከያ ንብረት አይሄድም፤ ብሎ በመቃወሙና ከኤርትራ የጦር አመራሮች ጋር በመነታረካቸው፤ ኢሳያስና አብይ በጉዳዩ ጣልቃ መግባታቸውን የሚገልፁት እነዚህ ምንጮች፤ በመጨረሻ በአብይ ትእዛዝ ኤርትራውያኑ የኢትዮጵያን ከባድ የጦር መሳሪያዎች ታንኮችና ኦራል ተሽከርካሪዎች ይዘው ወደ ኤርትራ እንዲሻገሩ ተደረገ::
ይህንን ተከታታይ የአገር ንብረት ዘረፋ ለተቃወሙ የመከላከያ ሎጂስቲክስ አመራሮች፤ አብይ አሕመድ ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ፤ «...በእነደዚህ ዓይነት ከኤርትራ ጦር ጋር ለሚፈጠር ማንኛውም መሳሳብ፤ እንደ ጦር ሃሎች ጠቅላይ አዛዥ እኔ ስለሆንኩ የምወስነው፤ ከእንግዲህ ለእኔ አሳውቁ እንጂ እጃችሁን እንዳታስገቡ...» የሚል ትእዛዝ እንደተሰጣቸው ነው ምንጮቻችን የገለፁት::
የሰላም ጭምጭምታ በስፋት መደመጥ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር፤ የኤርትራ ሰራዊት የመከላከያ ንብረት ዘረፋና የአገሪቱን ከባድ የጦር መሳሪያዎች ወደ ኤርትራ ማጓጓዙን በስፋት ቀጥሎበታል፤ የሚሉት ምንጮች በተለይም በምዕራብ ትግራይና በሰሜን ጎንደር የነበሩ በርካታ ወታደራዊ ንብረቶች ወደ ኤርትራ መሻገራቸውን ይገልፃሉ::
ከሰሞኑ የአብይ የኤርትራ ጉዞ በኋላ የተደመጠው ግን ለየት ያለ ነው የሚሉት ምንጮች፤ አብይ እራሱ «...ኢሳያስ የጠየቀኝ...» ብሎ ለቡድኑ እንደገለፀው፤ «...በስምምነታችን መሰረት እንደጀመርነው ወያኔን መቅበር አለብን:: ለምዕራባውያን ተንበርክከህ ይህንን ስምምነታችንን አልፈፅምም አቋርጣለሁ የምትል ከሆነ ግን፤ በዚህ ጦርነት ኤርትራ ለከሰረችው የህይወትና የንብረት ዋጋ ካሳ መክፈል አለብህ:: በተለይም በዚህ ጦርነት ለሞቱት የኤርትራ ሰራዊትና አመራር አባላት ለእያንዳንዳቸው የህይወት ዋጋ መክፈል አለብህ...» እንዳለው ነው::
ኢሳያስ ለአብይ ያቀረበው የካሳ ጥያቄ የገንዘብ ዋጋ ብቻም ሳይሆን፤ ድሮኖችን ጨምሮ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የሚያጠቃልል መሆኑን የገለፁት ምንጮች፤ ሁኔታውን ለማብረድ ዩናይትድ ዓረብ ኢምሬት ጣልቃ እንድትገባለት አብይ ኢምሬቶችን እየተማፀነ መሆኑን ገልፀዋል::
ትግራይ ትስዕር ኣላ!
ካሳ ሃይለማርያም
Please wait, video is loading...