ብራሰልስ በተደረገው ስብሰባ፥ የራሱን ፎቶ በመለጠፍ አብይ አህመድ በብቸኝነት እየመራ ነው።
በሁለት ቀናት ውስጥ እስካሁን ድረስ 38 ፎቶዎቹን ለጥፏል። በአለማቀፍ መድረክ አግኝቶ የጨበጣቸውን ሁሉ እንደዲፕሎማሲ ድል መቁጠሩ የሚነግረን ነገር ብዙ ነው።
በአለማቀፍ መድረክ ያገኘውን መሪ ሁሉ አብሮ ፎቶ እየተነሳ መለጠፍ፥ የቅቡልነት ድርቀት እንደመታው፣ የዲሲ ቦዘኔዎችን ሰብስቦ ፎቶ ሲነሳ የሚውለው ደመቀ መኮንን የሚመራው የውጭ ግንኙነትም በተለይ ከምዕራቡ ዓለም ጋር ያለው ግንኙነት ከዜሮ በታች የመወረዱና ያንን በፎቶ ፖለቲካ ለመሸፈን የሚደረግ desperation እንዳለ ግልፅ ማሳያ ነው።
ምናልባትም እኔ ይህንን ፅሑፍ እየፃፍሁ ባለሁበት ቅፅበት፥ "ከወንድሜ እገሌ ጋር..." አልያም "ከእህቴ እገሊት ጋር......" ብሎ ከአንዱ ሀገር መሪ ጋር በድንገት የተነሳውን ፎቶ ለጥፎ ቁጥሩን ከፍ ሊያደርገው ይችላል።
ነገሩ፥ "ሆድን በጎመን ቢደልሉት፥ ጉልበት በዳገት ይለግማል" ነው።
ዴቭ ዳዊት።


Please wait, video is loading...