Page 1 of 1

Current Life In Cursed-Land-Tigray.These Evil Ppl R Living In Hell Thanks 2 Halafi-Thomas-Eden-Aba-Sarc!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 19 Feb 2022, 10:07
by tarik
የቀይመስቀል የስልክ አገልግሎት ለትግራይ
በመቐለ እንደታዘብነው፥ በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች እና የትግራይ ክልል መንግስት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጭ የሆነ የቪሳት ኢንተርኔት አቅርቦት አላቸው። ከዚህ አገልግሎት ለማግኘት በሚል ተስፋ በርካታ ህዝብ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በራፍ ደጅ ሲጠና ይውላል።


አውዲዮውን ያዳምጡ።04:11
የዓለም ቀይ መስቀል ከ100ሺ በላይ ሰዎች በስልክ አገናኝቷል
የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ትግራይ ዉስጥ በተደረገዉ ጦርነት አንዳቸዉ ከሌላቸዉ የተለያዩ ቤተሰቦችን በስልክ ማገናኘቱን አስታወቀ።ካለፈዉ ሰኔ ማብቂያ ጀምሮ ትግራይ ዉስጥ የስልክ፣የኢንተርኔትና የፖስታ አገልግሎቶች እንደተቋረጡ ነዉ።የመገናኛ አገልግሎት ባለመኖሩ የሕዝቡ መደበኛ እንቅስቃሴ ክፉኛ ተቃዉሷል።በተለይ በጦርነቱ ሰበብ አንዳቸዉ ከሌላቸዉ የተለያዩ የቤተ-ሰብ አባላት፤ ዘመድና አዝማዶች መቸገራቸዉን እየገለፁ ነዉ።የዓለም ቀይ መስቀል ኮሚቴ ግን በቅርቡ 115 ሺሕ የተለያዩ ቤተ-ሰብ አባላትን በስልክ ማገናኘቱን አስታዉቋል።

የትግራይ ሐይሎች መቐለ ከተቆጣጠሩበት ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓመተምህረት በኃላ በትግራይ በተወሰነ ደረጃ የነበረው በመንግስታዊው ተቋም ኢትዮ ቴሌኮም የሚቀርብ ሁሉም የቴሌኮም አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንደተቋረጠ ይገኛል።
በትግራይ የመደበኛ እና ሞባይል ስልክ፣ ኢንተርኔት እና ሌላ የግንኙነት መስመር በመቋረጡ ህዝቡ ለማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግር መጋለጡ ይገለፃል። በትግራይ ያሉ ዜጎች ከትግራይ ውጭ ካሉ ቤተሰቦቻቸውና ወዳጆቻቸው ለረዥም ግዜ ተለያይተው ያለ ሲሆን፥ ከዚህ በተጨማሪ በውጭ ሀገር የትምህርት ዕድል አግኝተው

Äthiopien Rotes Kreuz in Tigray
ሂደት ላይ የነበሩ፣ ከዓለም አቀፍ ተቋማት ጋር ይሰሩ የነበሩ፣ ከኢንተርኔት ጋር በተገናኘ ስራ ይተዳደሩ የነበሩ እና ሌሎች ከስራ ውጭ ከሆኑ፣ ያገኙት የትምህርት እና ስራ ዕድል ከተደናቀፈ ወራት አልፈዋል።

በመቐለ እንደታዘብነው፥ በከተማዋ የሚገኙ አንዳንድ ዓለምአቀፍ ድርጅቶች እና የትግራይ ክልል መንግስት ከኢትዮ ቴሌኮም ውጭ የሆነ የቪሳት ኢንተርኔት አቅርቦት አላቸው። ከዚህ አገልግሎት ለማግኘት በሚል ተስፋ በርካታ ህዝብ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በራፍ ደጅ ሲጠና ይውላል። እጅግ በጣም የተወሰኑ የተሳካላቸው ከትግራይ ውጭ የሚኖሩ ቤተሰባቸው በዋትሳፕ፣ ቴሌግራይ አልያም ሌላ መተግበርያ አማካኝነት ያገኛሉ።

ከዚህ ውጭ አለምአቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በመቐለ ጨምሮ በተለያዩ በትግራይ ባሉ ማእከላቱ የተጠፋፉ ቤተሰቦች በሳተላይት ስልክ አማካኝነት የማገናኘት አገልግሎት ይሰጣል። በዓለምአቀፉ ቀይመስቀል ኮሚቴ የትግራይ መስክ ልዑክ ቭላዲስላቭ ፖዶሊያኑክ ለዶቼቬለ እንደገለፁት ቀይመስቀል እስካሁን በትግራይ ለ115 ሺህ ሰዎች ነፃ ስልክ የማስደወል አገልግሎት ሰጥቷል። ቭላዲስላቭ ፖዶሊያኑክ እንደሚሉት የቀይመስቀል ነፃ የስልክ ማስደወል አገልግሎቱ ቤተሰቦቻቸው የት፣ ምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለማያውቁ ሰዎች መልካም አጋጣሚ የፈጠረ ነው ሲሉ ይገልፃሉ።

Äthiopien Rotes Kreuz in Tigray
ዓለምአቀፉ ቀይመስቀል ማሕበር ተመሳሳይ የተጠፋፉ ቤተሰቦች የማገናኘት ስራ በተለያየ መንገድ ላለፉት በርካታ ዓመታት በመላው ዓለም መከወኑ የቀይመስቀል ልዑኩ ተናግረዋል።

የትግራይ ክልላዊ መንግስት የሞባይል ስልክ አገልግሎት በትግራይ ውስጥ ለማስጀመር ሞክሮ የነበረ ቢሆንም በቴክኒካዊ ችግሮች ምክንያት እንዳልተሳካ ከወራት በፊት ገልፆ ነበር። ከዚህ ውጭ ብዙ ተገልጋይ የሌለው የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ግን ወደ ስራ ማስገባቱ የክልሉ መንግስት ይገልጻል።

===============================================================================================
«በትግራይ የዜጎች ህይወት ለአደጋ እየተጋለጠ ነው»ነዋሪዎች
በትግራይ ከመስከረም ወር መጀመርያ ወዲህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሻሽሏል።ሆኖም ነዳጅና መድሐኒቶችን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ወደ ትግራይ ስለማይገቡ የዜጎች ሕይወት ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑን፤ የሸቀጦች ዋጋም እጅግ እየናረ መሄዱንም ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።


አውዲዮውን ያዳምጡ።03:39
በትግራይ ከመስከረም ወዲህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሻሽሏል


የባንክ፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት አገልግሎት እንዲሁም ከትግራይና ወደ ትግራይ የሚደረግ ጉዞ ሙሉ በሙሉ ከተቋረጠ አንድ መቶ ቀናት ማለፉን የመቀሌው ወኪላችን ሚሊዮን ኃይለ ሥላሱ ዘግቧል። ከመስከረም ወር መጀመርያ ወዲህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሻሽሏል።ሆኖም ነዳጅና መድሐኒቶች ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ወደ ትግራይ ስለማይገቡ የዜጎች ሕይወት ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑን፤ የሸቀጦች ዋጋም እጅግ እየናረ መሄዱንም ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።ሚሊዮን ኃይለ ስላሴ ከመቀሌ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።
«በትግራይ የዜጎች ህይወት ለአደጋ እየተጋለጠ ነው»ነዋሪዎች
በትግራይ ከመስከረም ወር መጀመርያ ወዲህ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተሻሽሏል።ሆኖም ነዳጅና መድሐኒቶችን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች ወደ ትግራይ ስለማይገቡ የዜጎች ሕይወት ለአደጋ እየተጋለጠ መሆኑን፤ የሸቀጦች ዋጋም እጅግ እየናረ መሄዱንም ነዋሪዎች ለዶቼቬለ ተናግረዋል።
===============================================================================================
የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ
በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ወጣቶች ጦርነት ሲቀሰቀስ ህልማቸው ተጨናግፏል። ከሌሎች አካባቢ ወደ ትግራይ አቅንተው በትምህርት ላይ የነበሩት ወደ ትውልድ ቀያቸው ከተመለሱ በኋላ ወደ ሌሎች ተቋማት እስኪመደቡ ድረስ መጠበቅ ነበረባቸው። የዛሬው የከወጣቶች ዓለም መሰናዶ በተማሪዎቹ ህልም፣ ስነ ልቦና እና ትምህርት ላይ ያሳደረውን ጫና ይዳስሳል


አውዲዮውን ያዳምጡ።09:56
ከወጣቶች ዓለም፦ ጦርነት በትግራይ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ
ትግራይ ክልል ውስጥ ተጀምሮ ከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወደ አማራ እና አፋር ክልሎችም ተስፋፍቶ ይሄን ያሕል ተብሎ በተጨባጭ ያልተገለፀ ንፁሃን ዜጎች እና በሁለቱም ተፋላሚ የፀጥታ ኃይላት ላይ ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ በመንግሥት እና የሕዝብ የንብረት ላይም ውድመት አስከትሏል።

ጦርነቱ የዜጎችን መደበኛ ሕይወት በእጅጉ አናግቷል። ከአፀደ ሕፃናት እስከ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ድረስ በመማር ላይ የነበሩትን ተማሪዎች እና መምህራንን ጨምሮ ከሥራቸው አደናቅፏቸዋል። የገንዘብ ሚኒስቴር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያሳየው 4120 የትምህርት ተቋማት በጦርነቱ ሳቢያ ውድመት ደርሶባቸዋል።

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትም ቢሆኑ ጦርነቱ ውስብስብ ችግር ካደረሰባቸው ተቋማት መካከል ናቸው። በተለይም በትግራይ ክልል ውስጥ በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው ሲማሩ ዓመታትን ያሳለፉ ተማሪዎች የጦርነቱን መባባስ ተከትሎ ከየተቋሞቻቸው እንዲወጡ የነበረው የወላጆች ጥያቄ፣ ጭንቀትና አቤቱታ ከፍተኛ ነበር። ተማሪዎቹም ቢሆን የቻሉት እና አቅም የነበራቸው በእግር ያላቸው ንብረት ማለትም ስልክ፣ ኮምፒውተር፣ ልብስ እና ጫማ በመሸጥ ከጦርነቱ ቀጣና ለመውጣት ጥረት አድርገው ሲሳካላቸው አብዛኛዎቹ ግን በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ድጋፍ ጭምር ነበር ወደየ ቤተሰቦቻቸው ለመቀላቀል የበቁት።

Äthiopien | Ehemalige Studenten der Tigray-Universität
ተማሪዎቹ ከትግራይ ከወጡ በኋላ ወደ ሌሎች የትምህርት ተቋማት ለመመደብ የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴርን ደጅ ሲጠቁ ቆይተዋል።

ጦርነቱ በእነዚህ ተማሪዎች ራእይ ላይ ትልቅ እንቅፋት እንደጋረጠባቸው ገልፀዋል። አንዳንዶቹ በማዕረግ ተመርቀው ሥራም ይዘው ሕይወትን ለመጀመር ወራቶች ብቻ ሲቀሩ ያንን ክስተት ማስተናገዳቸው አስከፍቷቸዋል።

ሌሎች በበኩላቸው በችግር ውስጥ ሆነው ያስተማሯቸውን ቤተሰቦቻቸውን የሚረዱበት ጊዜ መቃረቡን እያለሙ ባለበት ወቅት ለዚህ ችግር መዳረጋቸው አሁን ድረስ የቤተሰብ ጥገኛ የመሆን ከባድ የሥነ ልቦና ስሜት ፈጥሮባቸዋል።

እነዚህ ወጣት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ትግራይ ክልል ውስጥ እያሉ የመብራት፣ የስልክ ፣ የኢንተርኔት እና የባንክ አገልግሎቶች ባለመኖሩ ከመቸገራቸው በላይ የጦርነቱ አስፈሪ ድባብ የፈጠረባቸው ጭንቀት ከባድ እንደነበር ያስታውሳሉ።

ተማሪዎቹ ከክልሉ ከወጡ በኋላ ትምህርት ሚኒስቴር ወደ ሌሎች ተቋማት በፍጥነት ሊመድባቸው ባለመቻሉም ሌላ ያልጠበቁት ችግር እንደገጠማቸውና ለስምንት ወራት ያህል ያለምንም መፍትሔ መንገላታታቸው በራሱ ፈተና ሆኖባቸው እንደቆየ ተናግረዋል።

Äthiopien Studierende Tigray Universität
የኢትዮጵያ ኅምህርት ሚኒስቴር


ይህ ሁኔታ ብዙ ወጣቶች ወደማያውቁት ሱስ ውስጥ እንዲገቡ፣ የተስፋ ማጣት ሥሜት ውስጥ እንዲገቡም እንዳደረጋቸው ደጋግመው አስገንዝበዋል። ደረሰብን ያሉት የሥነ ልቦና ጫና ቀላል እንዳልሆነም በምሬት ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ከገቡ ጀምሮ እስካሁን የተማሩበት የትምህርት ማስረጃ ስለመኖር አለመኖሩ ከትምህርት ሚኒስቴር ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው ሰነድ አልባ ተማሪ የመሆን ስሜት ፈጥሮባቸዋል።

ጉዳቱ ከዚህም ተሻግሮ ቤተሰቦቻቸውን ለተጨማሪ ወጪ የዳረገ የኢኮኖሚ ጥያቄም ይዞባቸው የመጣ መሆኑን ገልፀዋል። ዝቅተኛ ገቢ ካላቸው ቤተሰቦች እንደወጣ የሚናገረውና መቀሌ ዩኒቨርሲቲ ይማር የነበረው ተመራቂ ተማሪ ዘርፉ ሸኖ ቤተሰቦቹን ተመርቆ ሥራም አፈላልጎ ለመርዳት የነበረው ውጥን ከመደናቀፉ በላይ ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በእግሩ በራያ በኩል አቆራርጦ የወጣ እና ከለበሰው ሸሚዝ ፣ ጫማ እና ሱሪ በቀር ሌላውን ዕቃውን ሸጦ ምንም ይዞ አልተመለሰም። "ይህንን ሁሉ ጨርሼ ከመጣሁ በኋላ ልብስ ለመግዛት ብር ያስፈልገኛል፣ ይህንንም እንደገና ከቤተሰብ ነው የማገኘው።ይህንን ለማሟላት አሁን ( ወደተመደበበት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለመመለስ ) እንደ አዲስ ተማሪ ሆኜ ነው የምገባው። አንሶላ ፣ ብርድ ልብስ፣ ልብስ፣ ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ስልክና ከተቻለም ኮምፒውተር ያስፈልጋል ፣ ግን ያንን ለማሟላት ለቤተሰብ ከባድ ሆኗል" በማለት ይገልፃል።

Äthiopien Studierende Tigray Universität
በጦርነት ምክንያት ትምህርታቸው የተስተጓጎለ ተማሪዎች ህልማቸው ከመቀጨቱ ባሻገር ለስነ ልቦናዊ ጫና መዳረጋቸውን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል።

የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ የነበረው ሌላኛው ወጣት ብስራት ፋንታሁን የደረሰበትን ዙሪያ መለስ ችግር ከተመለከተ በኃላ "ጦርነት አያስፈልግም። የእርስ በርስ ጦርነት መጨረሻው ሞት እና እልቂት ነው። ሁሉንም ነገር ነው የሚጎዳው። ስለዚህ ይህ ነገር ቆሞ ወደቀደመው ሰላም መመለስ አለብን " ይላል።

ትምህርት ሚኒስቴር ትግራይ ክልል ውስጥ ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ብዙ ተማሪዎችን ከብዙ መጉላላት በኋላ ወደ ሌሎች ክልሎች ሲመድብ አማራ ክልል ውስጥ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መድቤያችኋለሁ ብሏቸው የነበሩ ተማሪዎች የትምህርት ተቋሞቹ ከጦርነቱ ጋር በተያያዘ እና ከመቀበል አቅም ማነስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ሳይቀበሏቸው ለስምንት ወራት ሲጉላሉ ቆይተዋል። ይሁንና ከብዙ ውትወታ እና ጥያቄ በኋላ ተማሪዎቹ ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ወደ ተመደቡባቸው ተቋማት እንደሚጠሩ ዩኒቨርሲቲዎቹም፣ ትምህርት ሚኒስቴርም ለዶይቼ ቬለ አረጋግጠዋል።ተማሪዎቹም የዘገየ ውሳኔ ቢሆንም በዚህ ደስተኞች ሆነዋል።