Page 1 of 1

^^^(((!!WTF!!MY ERITREA BE CAREFULL)))^^^Russian Navy Post 2Day Met Ethiopia's Imaginary Navy Leader!!! WEEY GUUD !!!

Posted: 18 Feb 2022, 14:35
by tarik
Natnael Mekonnen
90h56Sp45ucmc1gfh1r6mu5da ·
የሩሲያ ባሕር ኃይል ልዑክ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ!
#Ethiopia : የሩሲያ ፌዴሬሽን ባሕር ኃይል ልዑክ የሁለቱን አገራት የዘለቀ ትብብር መነሻ በማድረግ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ጠቅላይ መምሪያን ጎበኘ፡፡ሁለቱ ሀገራት ለረጅም አመታት የዘለቀ ዲፕሎማሲያዊ ትብብር ያላቸው ሲሆን፤ የጉብኝቱ ዓላማም የትብብሩ አንድ አካል መሆኑ ተመልክቷል፡፡
የልዑኩ መሪና በኢትዮጵያ የሩሲያ ፌደሬሽን ተልዕኮ ኃላፊ ሜጀር ጀነራል ኦስትሪ ኮቭ በጉብኝታቸው የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል በመዋቅራዊ አደረጃጀቱ ይበልጥ እየዘመነ እንዲመጣና ኢትዮጵያዊያን የሚኮሩበት ጠንካራ ተቋም ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን መገንዘባቸውን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ላይ ጠንካራ ባሕር ኃይል ኢንዲኖራትና የመከላከል አቅሟን ይበልጥ ለመገንባት በምታደርገው ሁሉ ዐቀፍ እንቅስቃሴ ውስጥ በተለያዩ የሥልጠና መስኮች ላይ ሩሲያ ሚናዋን መጫወት ትችላለች ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ተወካይ ኮሞዶር ዋላፃ ዋቻ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል የዛሬ ሦስት ዓመት መቋቋሙን ገልፀው በተማረ የሰው ኃይል ለማደራጀት እየተሰራ ስለመሆኑ ለልዑካን ቡድኑ ገልፀዋል፡፡
"ከሌሎች አገራት የባሕር ኃይሎች አደረጃጀት እና ቀደም ሲል ከነበረ የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ልምድ በመውሰድ፤ የተሰጠንን አገራዊ ተልዕኮ በአግባቡ ለመፈፀም የሚያስችል የተሟላ አደረጃጀት ተሰርቶና በመከላከያ ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል"ም ብለዋል፡፡
ኮሞዶሩ አያይዘውም ኢትዮጵያ ከባሕር ኃይሏ ማግኘት የምትችለውን ጥቅምና ግልጋሎት እንድታገኝ ከሩሲያ ፌደሬሽን ባሕር ኃይል ጋር በተለያዩ የስልጠና ዘርፎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሰናል ማለታቸውን የመከላከያ ሠራዊት መረጃ አመላክቷል፡፡