Page 1 of 1

"ህገመንግስቱን እንለውጠዋለን" ሲሉ የነበሩ ዘራፎች፥ "ለህገመንግስቱ ታማኝ ነን" ብለው መሐላ በመፈፀም የመደለያ "ሹመት" ሲቀበሉ ስታይ ...

Posted: 16 Feb 2022, 10:32
by sarcasm
"እስተኒ-ያ-ዘራፍ! ባሩድ በምላስ አይበርድም"
ዴቭ ዳዊት።


ኢትዮጵያ እያለሁ በአንድ ወቅት ፥ አንድ የድሬዳዋ ተወላጅ፥ "አባቴ ነገረኝ" ብሎ የነገረኝ ታሪክ ነው።

የዚያድባሬ ጦር ኢትዮጵያን እየወረረ ወደ ድሬዳዋ ሲገባ፥ የዚህ ባለታሪክ አባትና ሌሎች ጓደኞቻቸው ተሰባስበው አንድ የአረብ ተወላጅ ባለሱቅ ቤት ይቀመጣሉ።

የዚያድባሬ ወታደሮች ታንኮቻቸውንና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎቻቸውን ይዘው ሲያልፉ፥ አንዱ ደመ-ሞቃት "ዘራፍ! እኔ ወንዱ! ወጥቼ እፋለማለሁ" እያለ ለያዥ ለገላጋይ ያስቸግራል። አረቡ ባለሱቅም፥ በባዶ ፉከራ የሚፎገላውን ሰውዬ፥ "እስተኒ ያ ዘራፍ! ባሩድ በምላስ አይበርድም" እያለ ይለምነዋል። ባሩድ በባሩድ እንጂ፥ ባሩድ በምላስ እንደማይመከት ሲነገረው ያልሰማው ፎካሪ፥ ከመካሪው ጋር እልህ ተያያዘና የግቢውን በር ከፍቶ "ዘራፍ! እያለ ወደ ዚያድባሬ ወታደሮች እየጮኸ ሲሄድ፥ ሦስት እርምጃ ሳይሄድ ተኩሰው ገደሉት። ያንን ያየው አረቡ ሰውዬም "ዘራፍ ነግሬህ ነበር እኮ" አለው ይባላል።

"ህገመንግስቱን እንለውጠዋለን" ሲሉ የነበሩ ዘራፎች፥ "ለህገመንግስቱ ታማኝ ነን" ብለው መሐላ በመፈፀም የመደለያ "ሹመት" ሲቀበሉ ስታይ፣ "ከእንግዲህ አማራ አይዘለፍም" ሲሉ የነበሩ ዘራፎች፥ ዋነኛ ዘላፊና ከፋፋይ ሲሆኑ ስታይ.................እስተኒ ያ ዘራፍ፥ ላትጨርሰው ትናንት ላይ ምን አሰፎከረህ፣ እስተኒ ያ ዘራፍ፥ ዛሬ ላይ ላታደርገው ትናንት ደርሰህ የፅንፈኝነት ምልክት ካልሆንሁ ለምን አልህ፣ እስተኒ ያ ዘራፍ! ባሩድ በምላስ አይበርድም፣እስተኒ ያ ዘራፍ.......እንድንል ያደርገናል።

ተው ዘራፍ! እስተኒ ያ ዘራፍ!!!

ዴቭ ዳዊት።
Please wait, video is loading...