የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የነበረውን ግንኝነት ማቋረጡን አስታወቀ።
Posted: 14 Feb 2022, 19:01
የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክርቤት ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው በትግራይ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ አስመልክቶ ባካሄደው ምክክር ነው።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማትና መሪዎች በትግራይ ህዝብ ላይ የተፈፀመወን ጄኖሳይድ ከመኮነን፣ከማሸማገል ይልቅ ጦርነቱ ባርከው ከማስጀመር በተጨማሪ በገንዘብም በመንፈስም ድጋፍ ማድረጋቸ በውይይት የዳሰሰው ምክርቤቱ ይህ ተግባር ከእስልምና ህግና ስርዓት ያፈነገጠ በመሆኑ ከእስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ጋር የነበረውን ግንኙነት ማቋረጡን አስታውቋል።
በመድርኩ የተገኙት የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ዋና ፀሓፊ ሓጂ መሓመድ ካሕሳይ እንደተናገሩት ፋሽስታውያንን ወራሪ ሃይሎች ትግራይን ህዝብ ለማጥፋት እምነትን ሳይለዩ ጄኖሳይድ ፈፅመዋል።
በርካታ ቁጥር ያላቸው የእስልምና እምነት ተከታዮች በነዚህ ፋሺስታውያን ወራሪ ሃይሎች ተገድለዋል ብለዋል ሓጂ መሓመድ ።
ይህ ሁሉ ግፍ በትግራይ ህዝብ ላይ ሲፈፀም የኢ/ያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ወንጀሉን ከማውገዝ ይልቅ ተባባሪ መሆኑን የሚኮነን ተግባር ነው ያሉት ሓጂ መሓመድ የትግራይ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጄኖሳይድ ወንጀል ተባባሪ ከሆነው የኢ/ያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የነበረውን ግንኙነት ለማቋረጥ ተገዷል ሲሉ ተናግረዋል።
የካቲት7/ 2014 ዓም
ድምፂ ወያነ ትግራይ

https://www.facebook.com/dimtsiweyane1/ ... 6037912421