Too Expensive: ECB paid $303.5m for its new skyscraper while similar buildings cost $70m in Kenya
Posted: 14 Feb 2022, 09:38
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ የግንባታ ዋጋው ከመሰል ህንጻዎች አንጻር በጣም ብዙ ነው፤ ሚስጥሩ ምን ይሆን?!
By Andinet Zeleke Bekele
**************************************
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (ECB) በ303.5 ሚሊዮን ዶላር ያስገነባው ግዙፍ ሕንፃ ተመረቀ ተብሎ ሲነገር ደስ ነው ያለኝ፡፡ ሆኖም ይህ ከ15 ቢሊዮን ብር በላይ የሚፈጅ ዋጋ ያለው ህንጻ እድሜው የሰው ያክል መሆኑን ሳውቅ ደሞ አዝኛለሁ፡፡ ትላልቅ ህንጻዎች (skyscrapers) ከብረት እና ከመስታወት ብቻ በአብዛኛው ስለሚሰሩ እድሜያቸው ቢበዛ ከ80 እስከ 150 አመት እንደሆነ ሳይንሱ ያስረዳል፤ ያውም በየወቅቱ እየተጠገኑ ከሆነ ብቻ ነው፡፡
በእርግጥ በአርማታ የሚሰሩ አነስተኛ ከፍታ ያላቸው (እስከ 25 ወለል) ህንጻዎች አስተማማኝ የእስትራክቸራል ዲዛይን ካላቸው እና በቂ stability ውስጥ የሚገኙ ከሆነ በርከት ላሉ መቶ አመታት ይቆያሉ፡፡ በዚህ ጹሁፍ ዋናው ቁምነገር፤ የህንጻውን አዋጪነት ለመናገር አይደለም፡፡ በዛሬው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ህንጻ ምርቃት አዋጪነቱ እማ ሳይሰላ በራሱ አክሳሪ እንደሚሆን ግልጽ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ያሉ ሜጋ ፕሮጀክቶች በሙሉ ለግንባታ የዋለውን እዳቸውን መክፈል እንደማይችሉ ይታወቃል፡፡
ሆኖም በንግድ ባንክ መገንባቱ ብዙ ተጓዳኝ ጠቀሜታ ስላለው አይከፋም፡፡ መቼም ቢሆን በህንጻው እድሜ ውስጥ (in the life expectancy of the Skyscraper) በኪራይ ታሳቢ ተደርጎ የሚገባው ገቢ፤ ከግንባታው ወጪ ጋር ሊወዳደር አይችልም፤ ገቢው አነስተኛ ይሆናል፡፡ ይህ ማለት አንድ ግለሰብ ህንጻውን አስገንብቶ ቢያከራየው፤ የገነባበትን ዋናውን ወጪ እና በየወሩ ያለበትን operational cost አይሸፍንም ለማለት ያክል ነው፤ ባጭሩ ሳያተርፍ በመቅረት ይከስራል፡፡ በእርግጥ ንግድ ባንክ ከገቢው በላይ ለስሙ እና ለግርማ-ሞገሱ ዋጋ የሚሰጥ ከሆነ፤ አትራፊ ነኝ ብሎ መቁጠር ይችላል፡፡
የሆኖ ሆኖ የህንጻው ግንባታ 303.5 ሚሊዮን ዶለር መሆኑን ስሰማ፤ ከሱ ጋር ተቀራራቢ የሆኑ ህንጻዎችን ለማነጻጸር ሞክሪያለው፡፡ ሁሉም ከ25 ፎቅ ወለል በላይ ያላቸው ህንጻዎች በሙሉ በብረት፤ በአልሙኒየም እና በመስታወት እንደሚሰሩ አውቃለሁ፡፡ እነዚህ የግንባታ ግብአቶች ናቸው በዋናነት ለfinishing and structural parts የሚውሉት፡፡ አርማታ (Reinforced concrete) ከ25 ወለል በላይ መሸከም አይችልም፤ ይሰበራል ወይም Column ከመወፈሩ የተነሳ ህንጻውን አስቀያሚ እና ከባድ ስለሚያደርገው አይመከርም፡፡
በዚህ መሰረት በአፍሪካ ውስጥ ተቀራራቢ እና ረዘም ያሉ ሶስት ህንጻዎችን በመውሰድ ዋጋቸውን አወዳድሪያለው፡፡ ዋጋቸውን ለማነጻጸር ከግምት ያስገባሁት የኬንያን እረዥሙን ህንጻ፤ የደቡብ አፍሪካን እረዥሙን ህንጻ እና የኢትዮጵያን እረዥሙን ህንጻ ናቸው፡፡ ሶስቱም ህንጻዎች ተቀራራቢ ቁመት ያላቸውና ባለፉት 5 አመታት የተገነቡ ሲሆን በውጭ ኮንትራክተሮች የተሰሩ ናቸው፡፡ በዚህም መሰረት የኬንያው 70 ሚሊዮን ዶላር፤ የደቡብ አፍሪካው 150 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን የኢትዮያው ደግሞ 303 ሚሊዮን ዶላር ፈጅተዋል::
ሶስቱም ህንፃዎች; የተሰሩበት የግንባታ ግብአቶች; የግንባታ ስፋታቸው እና ከፍታቸው የተቀራረበ ነው፤ እንደውም የደቡብ አፍሪካው ከአፍሪካ ሁለተኛው እረዥሙ ሲሆን የኢትዮጵያ ደግሞ ሶስተኛው ነው፡፡
ይሁን እንጂ ዋጋቸውን ስናነጻጽር የኢትዮጵያው የደቡብ አፍሪካውን በሁለት እጥፍ የበለጠ ሲሆን የኬንያውን ደግሞ ከ4 እጥፍ በላይ የሚበልጥ ነው፡፡ ይገርማል!! የሆኖ ሆኖ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለቻይና መንግስታዊ ኮንትራክተር በመስጠት የተገነባው በdesign-bulid የኮንትራት ማእቀፍ ነው፤ ይህ አካሄድ ለኢትዮጵያ አዲስ በመሆኑ ለብክነት ሳይዳርግ አልቀረም!!

Please wait, video is loading...