Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰማይ ጠቀስ ምርቃት ሙሉ ፕሮግራም !!! 34 ሚሊዮን ደምበኞች አሉት! 50% - 60% አዋቂዎች ቁጥር ማለት ነው

Post by sarcasm » 13 Feb 2022, 17:56

አቶ በረከት ስምኦን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ ዛሬ ይመረቃል! እስከ አሁን የወያኔ ፕሮጀክቶች እየመረቁ ነው ያሉት!



Abere
Senior Member
Posts: 15488
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሰማይ ጠቀስ ምርቃት ሙሉ ፕሮግራም !!! 34 ሚሊዮን ደምበኞች አሉት! 50% - 60% አዋቂዎች ቁጥር ማለት ነው

Post by Abere » 13 Feb 2022, 18:19

እስከ አሁን የተፈናቀሉት እና የሞቱት ቁጥር ግን አይታወቅም። ትግራይ ውስጥ ግልጽ የሆነው 900,000 ሰው ሙቷል፥ ከአማራ እና አፋር በኩል ስንት እንደሞተ አይታወቅም። የሚታወቀው ግን ወለጋ ክፍለ ሀገር ደንበኛ ቄራ ሁኗል። በወያኔ ዘመን አንድ ቀበሌ ይዞ የማያውቀው ኦነግ አሁን የባንክ ቤት ዘራፊ፥የነዳጅ ንግድ ስራ አስኪያጅ ነው። ኦነግ በወያኔ ተተክቷል። ሰገጤዎች በቀን ጅብ ተተክተው አገር በጠራራ ጸሃይ ይመዘበራል - የትውልድ ህይወት እንደ ቅጠል ይረግፋል። ወያኔን እናስወግዳላን ይላሉ፥ የወያኔ የበላይ ጠባቂ ሁነው በህዝብ ቁማር ይጫወታሉ።

በእርግጥም ወያኔ የጀመረቻቸውን ፕሮጀክቶች ቀለም መቀባት ብቻ ሁኗል እንጅ ምንም ለውጥ የለም።

በ17 መርፌ በጠቆመው -ቁምጣ፥
ሌላ ንጉስ እንጅ መቸ ለውጥ መጣ።

ወያኔ እንኳን 17 አመት ታግሎ ነው፥ ዜሮ አመት የታገለ ኦሮሙማ በስርቆት ስልጣን ሲያጭበረብር አያፍርም። ውጊያ ላይ እንደ ሰንጋ ፈረስ ይፈረጥጣል፥ ጀግኖቹ ሲዋደቁ አፈግፍጉ ይላል። ይምሰለኛል አሁን የኢትዮጵያ ህዝብ የብልጽግና ኦሮሙማ ዜና መስማት ያቅለሸለሸው ይመስለኛል። ደርግ ሊወድቅ ሲል ህዝብ የመንጌን ድምጽ መስማት ሰልችቶት ነበር። በወያኔ ዘመንም መለስ ዜናን መስማት ያስታውክ ነበር - ብዙ ውጭ የወጡ ሰዎች የመጀመሪያው እፎይታቸውን መለስ ዜናዊን ከመስማት መላቀቃቸው ነው። አሁን ዐብይ አህመድን መስማት አለርጅክ ወይም የሚያቅለሸልሽ ሁኗል - የስልጣን ኡዴቱን ጨርሷል።

Post Reply