Page 1 of 1
አዳነች አቤቤ፣ ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ
Posted: 11 Feb 2022, 15:41
by Horus
Re: አዳነች አቤቤ፣ ብርሌ ከነቃ አይሆንም ዕቃ
Posted: 11 Feb 2022, 16:49
by Horus
የአንድ ሰው እውነተኝ ባህሪ (ካራክተር) የሚታወቀው በሰው ፊት በሚያደርገው ተግባር፣ ተገዶ በሚሰራው ስራ ሳይሆን ሰው በሌለበት፣ ማንም በአያየው ግዜ በራሱ እምነት ተገፍቶ በሚያደርገው ነገር ነው ። አዳነች አቤቤ እውነተኛ ባህሪዋን አሳይታለች ፤ ከዚህ ቀጥሎ የሚታየው ድርድርና ፖለቲካል ኮሬክትነት ትክክለኛ ባህሪዋ ሳይሆን የፖለቲካ ጌም ይባላል! ያ ነው ብርሌ ከነቃ የሚባለው! ለኢትዮጵያ ሰንደቅ እና ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክብር እንደሌላት አስመስክራለች! የሚገርመው ግን ትግሬ ከስልጣን ሊያወርዳት ደብረ ብርሃን ሲደር እውነተኛው የኢትዮጵያ ሰንደቅ አሲዛ በሺዎች ሰብስባ ኢትዮጵያ፣ ኢትዮጵያ፣ አድዋ ስትል ነበር!!! ለሷ ህዝቡን በስስ ስሜቱ የቀሰቀሰች፣ ያታለለች ሊመስላት ይችላል! ያን ስብከት ዛሬ በተግባር መሻሯ ነው የፖለቲካ ነጋዴ አድርጎ የህዝብ አመኔታዋን የሚንደው ። ካራክተር እንደ ልብስ እንደየ ሁኔታው የሚቀየር ቀሚስ አይደለም! የሰው ትክክለኛ ማንነት መለኪያው ሳይንስ ነው ። ማለትም ይህች ሴት 6 ወር እንኳ በአስተዋይነት አለ ውዝግብ መምራት አልቻለችም። አሁን የያዘችው ማስተባብለ፣ ማፈግፈግ ወዘተርፈ ነው! ትክክለጋው ለህዝብ ማሳየት ያለባት ለድክመቷ ይቅርታ መጠየቅ እንጂ አንዴ መርጣችሁኛልና ተጋቱት የሚለው ያው የለመድነው የወያነ ቋንቋ ነው!