Page 1 of 1

በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። BBC

Posted: 09 Feb 2022, 11:05
by sarcasm
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ አዲስ አበባ ውስጥ ዛሬው ረቡዕ የካቲት 02/2014 ዓ.ም ከጋዜጠኞች ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ይህንን የተናገሩት።

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ በጦርነቱ የተጎዱትን የትግራይ፣ የአማራና የአፋር ክልሎችን ከጎበኙ በኋላ ለሰላም ተስፋ እንዳለ የገለጹ ሲሆን "በእርግጥ የሚስተዋለው ከጥቂት ወራት በፊት ከነበሩ ግጭቶች ያነሰ ነው" ብለዋል።

ከትግራይ አመራሮች፣ ከአማራ እንዲሁም ከፌደራል መንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ውይይት ያደረጉት አሚና መሐመድ ግጭቱ እንዲቆም ጥሪ አቅርበዋል።

ምክትል ዋና ፀሐፊዋ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ "በአሁኑ ወቅት በእርግጠኛነት የተሻለ ቦታ ላይ ነን። ተጨማሪ ውይይቶችም አሉ" ብለዋል።

ለአስራ አምስት ወራት የዘለቀውን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ተፋላሚ ወገኖች በቅርቡ ለሰላም ያሳዩትን እርምጃ በበጎ እንደሚያዩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከቀናት በፊትም መግለጻቸው ይታወሳል።

ሰላም ለማስፈን ግጭቱን እንዲሁም ተኩስ ማቆም ወሳኝ እርምጃ እንደሆነ የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ተፋላሚ ወገኖች ይህንን እርምጃ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።

አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከዚህ ቀደምም ጦርነቱን ለማብቃትና ሰላም ለማውረድ የሚያስችል የሚታይ ጥረት እየተደረገ መሆኑ እንዳስደሰታቸው መግለጻቸው ይታወሳል።

ዋና ፀሐፊው የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ከሆኑት ከኦሉሴጎን ኦባሳንጆ ጋር ባደረጉት የስልክ ውይይት፣ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ለማስቆም የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት እያደረጉት ስላላው ጥረት ከሕብረቱ ተወካይ መረዳታቸውን በወቅቱ አስታውቀው ነበር።

በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ዋና ፀሐፊውን በመወከል የመንግሥታቱ ድርጅት ምክትል ዋና ፀሐፊ አሚና መሐመድ የተገኙ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የትግራይ ክልል ከተሞችን ጎብኝተዋል። እንዲሁም ከክልል አመራሮችም ጋር ተገናኝተዋል።

Continue reading https://www.bbc.com/amharic/news-60319702


Re: በኢትዮጵያ መንግሥት እና በትግራይ አመራሮች መካከል ያለው ውይይት መቀጠሉን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታወቀ። BBC

Posted: 09 Feb 2022, 11:17
by Abdisa
The UN is facilitating an exit plan for TPLF terrorist leaders to be exiled to Canada. That's the least the UN can do for its TPLF servants who sacrificed 900,000 of their own agame people within a one year period desperately trying to bring Neo-colonialism back to Ethiopia, but failed. :mrgreen: :mrgreen: :mrgreen: