Page 1 of 1

በምዕራብ ጎንደር በመተማ " ዲቢኮ ቀበሌ " የ6 ዓመት ህፃን አግተው ብር የጠየቁ 4 የኢ-ደመበኛ ፋኖዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል - ፋና ብሮድካስቲንግ

Posted: 09 Feb 2022, 09:50
by sarcasm
በመተማ ወረዳ የ6 ዓመት ህፃን ያገቱ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ዲቢኮ ቀበሌ የ6 ዓመት ህፃን ያገቱ 4 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የወረዳው ሰላምና ደህንነት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የመተማ ወረዳ አስተዳደር የፀረ ሽምቅ ጋንታ አመራር ፶ አለቃ ባየ ደጉ እንደገለጹት፥ ከዲቢኮ የጸጥታ አካላት እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር በቅንጅት በተካሄደ ኦፕሬሽን የማገት ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ድርጊቱን ያወገዙት ፶ አለቃ ባየ፥ ማህበረሰቡ በንቃት አካባቢውን እና ቤተሰቡን እንዲጠብቅ አሳስበው፥ ችግሮች ሲኖሩም ከጸጥታ አካላት ጋር በጋራ የጸጥታ ስራ መስራት እንዳለበት ማሳሰባቸውን ከመተማ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በአካባቢው ገንዘብ ለመቀበዕል ሲሉ አንዳንድ ሰዎች በዚህ የወንጀል ድርጊት እየገቡና ህብረተሰቡን እያስመረሩ መሆኑ በተለያየ ጊዜ ሲነሳ ይስተዋላል፡፡


https://www.fanabc.com/%E1%89%A0%E1%88% ... %2589%25a6