''ድንገት በመሃል ጨዋታ ላይ ፌስቡኩን ከፍቶ እየጎረጎረ - 'ስብሃት ነጋ ተፈታ እኮ!' አይለኝም? ይኸው ተናድጄ፣ ተቃጥዬ፣ አብጄ፣ ጨጓራዬ ተነስቶብኝ በአምቡላንስ ነው ሆስፒታል የሄድኩት።
Posted: 06 Feb 2022, 20:32
By Eyob Mihreteab Yohannes
·
(100% እውነተኛ ታሪክ ነው)
∞ ∞ ∞ ∞ ∞ ∞
አንድ ውጪ የምትኖር የማውቃት ሴትዮ በስንት ጊዜዋ በWhatsApp ደውላልኝ የባጥ የቆጡን ስናወራ ስናወራ፣ አፌ ላይ እንዴት እንደመጣልኝ አላውቀውም፤ 'የገናን በአል ዶሮ ሰርተሽ አከበርሽው ወይ?' አልኳት።
(እሷ) - ''ኧረ ተወኝ። ገናንማ ታምሜ፣ ሆስፒታል ገብቼ ነው ያሳለፍኩት''
(እኔ) - ''ምን ሆንሽብኝ?''
(እሷ) - ''እኔማ በአል ነው ብዬ፣ ዶሮ ክትፎ ሰርቼ ዘመድ ተሰብስቦ እየበላ እየጠጣ ሳለ ያ ጉደኛው ባሌ መርዶዬን አረዳኛ!''
(እኔ) - ''ማለት?''
(እሷ) - ''ድንገት በመሃል ጨዋታ ላይ ፌስቡኩን ከፍቶ እየጎረጎረ - 'ስብሃት ነጋ ተፈታ እኮ!' አይለኝም? ይኸው ተናድጄ፣ ተቃጥዬ፣ አብጄ፣ ጨጓራዬ ተነስቶብኝ በአምቡላንስ ነው ሆስፒታል የሄድኩት። . . . በበአል ቀን አዋረደኝ የገዛ ባሌ።''
(እኔ፣ ከምር አዝኜ) - ''ውይ ሲደብር። ምን ስብሃት ዘመድ ምናምን ገድሎብሽ ነበር ወይ?''
(እሷ) - ''እንዴ?! ዋናው የጥፋት ስትራቴጂስት እሱ ነው አልተባለም እንዴ? የህወሃት ስትራቴጂስት ነው ሲባል አልነበር ወይ? . . . ዘመዶቼንማ የታባቱ አግኝቶ ይገድልብኛል!''
(ተናድጄ) - ''አንቺ ግን በሽተኛ ነሽ ጤነኛ?!''
(እሷ) - ''ለነገሩ አንተም ትግሬ አይደለህ? ያው ናችሁ። ያው ናችሁ እኮ!''

¤
. . . በነገራችን ላይ ልክ ነች፣ ትግሬ ነኝ። (ነኛ!)
ያው ሐማሴን ከሠራዬ፣ ከአከለጉዛይ፣ ከአጋመና ከአድዋ ከፍ ያለ ምርጥ ዘር ስለሆነ ብዙም አናወራውም። እንጂ የጠራ የኮራ ትግሬ ሐማሴን ነው። ኤቲስትነቴን ይንሳኝን ከምሬን ነው!

Please wait, video is loading...