Page 1 of 1

ርምጃ ሊወሰድ የሚገባ: አዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ ያለው ሙስና እና ትርምስ...... ጌጅ ኮሌጅ እና የመሳሰሉት ማን ፍቃድ ሰጣቸው?

Posted: 06 Feb 2022, 04:22
by Abaymado
1) በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ስር ያሉ ፖሊስ መምርያ ውስጥ ያሉ የጣብያ ኃላፊዎች የሚኖሩት የተቀማጠለ ኑሮ ጉድ ነው:: እንዴት እንዲህ ሊሆን ይችላል::

ከሁለት ሚልዮን ብር በላይ የሚያወጣ የናጠጠ መኪና ይነዳሉ: ደሞዛቸው ከ 15000 - 20000 ነው:: ልዩ ጥቅም ምናምን ሌላ ነው:: የዋይ ፋይ አገልግሎት ሁሉን ችሎ ፖሊስ ኮሚሺን ይከፍላል:: በወር 2000 ብር ነበር::



ሌላው ፖሊስ ግን የሚኖረው ኑሮ ይገርማል::: በዛ ላይ በአስሩ ክፍለ ከተሞች ያሉት ፖሊስ ጣብያዎች ማድቤት ወይም ወፍጮ ቤት መስለው
ነው ያሉት:: ይህ ሁሉ ወጪ ለምን?

በዛ ላይ እርስ በእርስ በብሄር በዘመድ መጠቃቀም በጣም ነው የሚታየው


2) ይህ ጌጅ ኮሌጅ የሚባል እንዲዘጋ ካልተደረገ የሚያመጣው መዘዝ ቀላል አይደለም::

ጌጅ ብቻ አይደለም: በጣም ብዙ ናቸው SRI SAI COLLEGE የሚባል የህንድ ኮሌጅም አንዱ ነው::

ለምን አዲስ አበባ ፖሊስ ምልምሎቹን እነዚህ ኮሌጆች ውስጥ ማስመረቅ አስፈለገው?


Re: ርምጃ ሊወሰድ የሚገባ: አዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ ያለው ሙስና እና ትርምስ ጌጅ ኮሌጅ እና የመሳሰሉት ማን ፍቃድ ሰጣቸው?

Posted: 06 Feb 2022, 04:44
by Abaymado
እኔ እንዴት ብዬ እንደምገልፀው አላቅም : ከዚህ በፊትም ስለ ጌጅ ኮሌጅ ፅፌ ነበር:: እንዴት ነው ፍቃድ ያገኘው?
ደሞ እኮ የሚገርመው ማስትሬት መስጠቱ ነው:: ማስትሬቱ ባጠቃላይ በሚባል መልኩ ከፌክ የተለየ አይደለም:: የመመረቅያ ፁሁፍ ባጠቃላይ የተሰረቀ እና ያልተለፋበት ነው::

እነዚህ ኮሌጆች ለ ዲፕሎማ እንኩዋን በቂ አይደሉም: እናም ከዛ ባለፈ እንዲቀጥሉ መፈቀድ የለበትም::

እኔን የገረመኝ በኩረጃ ማስትሬቱን የጨረሰ አንድ ፖሊስ PHD መቀጠል እፈልጋለሁ ሲለኝ ነው:: የት ነው phd ለእሱ የሚሰጠው?

የሚገርመው እኮ እነዚህ ማስትሬት አለን የሚሉ ሁሉ ስማቸውን በቅጡ በእንግሊዘኛ መፃፍ አይችሉም::

ለምንድነው አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እነዚህን ኮሌጆች ለአባላቱ የሚመርጠው ?

አንዱ ቦታ የሰማሁት ደሞ አንዱ ፖሊስ እንዲህ አለ: "አንድ ፖሊስ ዲግሪ ገዝቶ እድገት አግኝቶ ሌላ ቦታ ተመደበ" የሚል ::

እንዴት ያለ ነገር ነው? ወያኔ ጥሎብን የሄደው ጉድ ቀላል አይደለም:: እነሱ ዲግሪ እየገዙ ህዝቡንም በፌክ ዲግሪ አንበሻበሹት::

SRI SAI የሚባለው ኮሌጅ ከህንድ ሲሆን: ተማሪዎቹ የሰሩትን የማስትሬት thesis አይቼዋለሁ:: ሁሉም ከሌላ ሰው ላይ የተሰረቀ ሆኖ እንዳለቀ ሆኖ ቀርቧል::
ኮሌጁ የጠየቃቸው: plagiarism test በሶፍትዌር ቼክ አድርጉ እና ውጤቱን ላኩልን ብቻ ነው ያሉዋቸው:: እና መሰርቁን አያቁም ማለት ነው::

ተማሪዎቹ thesis ለሚያዩት ፈታኞች ስራቸውን አቅርበው የሰጡዋቸውን ኮመንት አይቼዋለሁ:: የሰጧቸው ኮመንት እንግሊዘኛው አንድ የተማረ ሰው የማይፅፈው ነው:: የቃላት ስህተቱ አይጣል ነው::
"እናም ይህ እንግሊዘኛ ቃላቱ ትክክል አይደለም" ብዬ ተማሪዎቹን ስላቸው:"እሱ እኮ ፕሮፌሰር" ነው አሉኝ:: ሰውየው ረዳት ፕሮፌሰር ነው::

ባጠቃላይ ስናየው እነዚህ ኮሌጆች ባጠቃላይ ተማሪዎቻቸው የሚመረቁት ኮርጀው ወይም በግርግር ነው::
እናም፣ የሚመለከተው አካል ርምጃ ሊወስድ ይገባል:: ዲፕሎማ ብቻ እንዲሰጡ መደረግ አለበት::

ጌጅ ኮሌጅ ብቻ ሳይሆን እንደ አሸን የፈሉትን ኮሌጆች አደብ ማስገዛት ይገባል::

Re: ርምጃ ሊወሰድ የሚገባ: አዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ ያለው ሙስና እና ትርምስ...... ጌጅ ኮሌጅ እና የመሳሰሉት ማን ፍቃድ ሰጣቸው?

Posted: 06 Feb 2022, 05:32
by Abaymado

በቅርቡ ከትግራይ ጋር እየተደረገ ባለው ጦርነት የተነሳ ማንም ፖሊስ ወደ ቤቱ እንዳይሄድ ታዞ ነበር: እናም እዛው ነበር የሚያድሩት:: እናም ለተወሰኑ የፖሊስ አባላት ምግብ ተሰርቶ ሆቴል ከሚባል አይነት ነገር ለቁርስ ምሳ እራት በደንብ ታሽጎ ይቀርብ ነበር::

ችግሩ ያለው ይህን አቅርቦት እንዲያገኙ የተደረጉት የማይገባቸው ሲሆኑ ማግኘት የሚገባቸው ሳያገኙ ቀርተዋል:: በሳጅን ደረጃ ያሉ ሲያገኙ ኮማንደር የሆኑት ይህ ምግብ መኖሩን እንኩዋን አያቁም ነበር::

እናም ይህ ለምን ሆነ ብዬ አንዱን ስጠይቀው:
"የመምርያ ኃላፊው እጁ ረጅም ነው ነው" ያለኝ:: ለሚፈልጉት ሰው በዘመድ ምናምን የሚሰራ ነገር የተለመደ ነው::

ሰውየውም ቀጥሎ እንዲህ አለኝ" ሰውየው ሲበዛ ባለጌ ነው " አለኝ::
እንዴት ስለው:
"ሴት አይምርም "አለኝ::

ምን ማለት ነው ስለው?

"ሆቴል እየገባ ነው ሴቶቹን የሚጨፈጭፈው " አለኝ::

Re: ርምጃ ሊወሰድ የሚገባ: አዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ ያለው ሙስና እና ትርምስ...... ጌጅ ኮሌጅ እና የመሳሰሉት ማን ፍቃድ ሰጣቸው?

Posted: 06 Feb 2022, 07:38
by Abaymado
የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽንን በተመለከተ የሚመለከተው የአዲስ አበባ መስተዳድር ይመስለኛል:: አዲስ አበባ ደሞ ከፍተኛ በጀት ያላት ከተማ ናት:: ግን ብሩ የት ነው የሚገባው?

እንዴት መስተዳድሩ ለፖሊስ ኮሚሽኑ ራሱን የቻሉ ህንፃዎች መገንባት ያቅተዋል?:

አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በስሩ በአስሩ ክፍለ ከተሞች አስር ፖሊስ ጣብያዎች ያሉት ይመስለኛል:: ዋናው ኮሚሽኑ ብቻ ነው ያማረ ህንፃ ያለው:: ሌሎቹ ግን በቆርቆሮና በገንዳ/ container ውስጥ ናቸው ያሉት ማለት ይቻላል:: ለምን?
አንድ ህንፅ ለመገንባት 17 ሚልዮን ቢፈጅ ለአስሩመምሪያዎች ደሞ 170 ሚልዮን ብር ማለት ነው::

እያንዳንዱ መምሪያ ደሞ ወደ ስድስት ጣብያዎች አሉት:: እነሱም የራሳቸው ህንፃ ያስፈልጋቸውል::

መከላከያ ላይ እንዲህ ያለ ችግር አይታይም ግን ለምን አዲስ አበባ ፖሊስ ላይ ይህ ሆነ?

Re: ርምጃ ሊወሰድ የሚገባ: አዲስ አበባ ፖሊስ ውስጥ ያለው ሙስና እና ትርምስ...... ጌጅ ኮሌጅ እና የመሳሰሉት ማን ፍቃድ ሰጣቸው?

Posted: 06 Feb 2022, 10:45
by Abaymado
እንደ እኔ እነዚህ ቢፈፀሙ እላለሁ:

1) በእያንዳንዱ ፖሊስ መምሪያ ጣብያ የሚገኙ ኃላፊዎች በየግዜው ወደ ሌላ ጣብያ መቀያየር: ይህ ያለውን በዘመድ የተሳሰረ አካሄድ ልበፅ ይችላል:: አንድ ብሔር ብቻ አብረው የሚሰሩበትን ያስቆማል:: ሙስናንም ጭምር

በተጨማሪም የትማውንም አመራር ላይ ያለ ወይም አባል እንዲሁ ወደ ሌላ ጣብያ መቀያየሩ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ


2) ደረጃቸውን የጠበቁ ህንፃዎች በያንዳንዱ ጣብያ መገንባት :መብራት ሲጠፋ አገልግሎት የሚሰጥ ጀነሬተር እንዲኖር ማረግ

3) መደበኛ ፖሊሶች 2000 ብር የሚያገኙ አቃለሁ : ይህንን ቢስተካከል ጥሩ ይመስለኛል:: መነሻው 5000 ቢሆን ይሻላል::

4) ኮለጆቹን ቤተመለከተ የትምህርት ሚንስቴር እንደገና ሊገመገማቸው ይገባል: ምን እየተካሄደ እንደሆነ ሊያውቅ ይገባል:: እስከምን ድረስ ሊያስመርቁ እንደሚችሉ በጥናት ላይ ተመስርቶ ሊሰጥ ይገባል::